Get Mystery Box with random crypto!

ከአሏህ መልካም ነገር እንጂ አታስብ ለአንድ የአረብ ዘላን: አንተኮ ሟች ነህ አሉት… አርሱም አለ | حيات سحبا የምርጦች ትውልድ ታሪክ

ከአሏህ መልካም ነገር እንጂ አታስብ

ለአንድ የአረብ ዘላን: አንተኮ ሟች ነህ አሉት…
አርሱም አለ: ከዚያስ ወዴት እሄዳለሁ?
ወደ አሏህ አሉት
እርሱም: ኸይርን ከአሏህ እንጂ አግኝተን አናውቅ… ታዲያ ከርሱ ጋር መገናኘትን እንፈራለን እንዴ!

ከአሏህ መልካምን ማሰብ ምነኛ ያማረ ነው!!

ከሰለፎች አንዱ ተጠየቀ: ዱዓው ተቀባይነት ያለውን ሰው ታውቃለህን?

እርሱም አላቸው: አላውቅም። ግን ዱዓን የሚቀበለውን አውቃለሁ!

ከአሏህ መልካምን ማሰብ ምነኛ ያማረ ነው!!

አንዱ ኢብኑ ዐባስን ጠየቃቸው: ለቂያም ለት ማን ነው ሰውን የሚመረምረው?
ኢብን ዐባስ: አሏህ ብለው መለሱለት።
ሰውየውም አለ: በከዕባ ጌታ እምላለሁ ዳንን!!

ከአሏህ መልካምን ማሰብ ምነኛ ያማረ ነው!!

አንድ ወጣት ሞትን ሲያጣጥር እናቱ አለቀሰች…

ወጣቱ: አማዬ የኔን ስራ አንቺ የምትመረምሪው ቢሆን እንዴት ታደርጊ ነበር?
እናት: አዝንልክ ነበር።
ወጣቱም አላት: አሏህ ካንቺ የበለጠ ለኔ አዛኝ ነው!!

ከአሏህ መልካምን ማሰብ ምነኛ ያማረ ነው!