Get Mystery Box with random crypto!

ምህራፍ 8 ክፍል 26 ፦ ክርስቲያኖች እንዳይመሰክሩ ሰበብ የሆኑባቸው ነገሮች ። ሰበብ ምክንያ | የመዝሙር ጥናት ደብተር Yemezmur tenat debter App

ምህራፍ 8
ክፍል 26 ፦ ክርስቲያኖች እንዳይመሰክሩ ሰበብ የሆኑባቸው ነገሮች ።
ሰበብ ምክንያት አይደለም ፣ ምክንያት አንድን ነገር ለማድረግም ሆነ ላለማድረግም በቂ የሆነ ጉዳይ ነው ።
ስለሆነም ስለክርስቶስ ላለመመስከር ሰበብ እንጂ ምክንያት ከቶውን ሊኖር አይችልም።
ሰበቦቹን ቀጥሎ እንመልከት ፦
❶, አጓጉል ፍርሀት
በሰማይና በምድር ስልጣን የተሰጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ነው፤ ይህንን ስንገነዘብ ወንጌል የማንመሰክርበት ፍርሀት አጉል መሆኑን እንገነዘባለን። ስለዚህ ወጥቶ እንዳይመሰክር ፍርሀት የከለከለው ካለ መመስከር ሲጀምር ያኔ ፍርሃት ለቆት እንደሚሄድ በተግባር ሊያረጋግጥ ይችላል።
❷, የሌሎች ስራ አድርጐ ማየት
ብዙ ክርስቲያኖች የወንጌል አገልግሎት የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ሀላፊነት አድርገው ይቆጥራሉ። ነገር ግን በክርስቶስ ደም የተዋጀን ሁሉ የወንጌል ባለአደራዎች ነን ። ባለአደራ ሀላፊነቱን ካልተወጣ ባለእዳ ይሆናል። ሀላፊነትን ለመወና ሰዎችን ከሲኦል ለመታደግ ክርስቲያኖች የሆንን ሁሉ ወንጌልን ልንመሰክር ይገባል።

@gospelisone
ለሌሎች share በማረግ የበኩላችንን እንወጣ ።
ለምድራችን ኢትዮጵያ እንፀልይ። ሰላም ለኢትዮጵያ
በኢየሱስ ስም አሜን