Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል 25 ወንጌልን ስናዳርስ ከእኛ ጋር ተጎዋዳኝ ሆነው የሚሰሩት እነማን ናቸው? 4,ቅዱሳን መላ | የመዝሙር ጥናት ደብተር Yemezmur tenat debter App

ክፍል 25
ወንጌልን ስናዳርስ ከእኛ ጋር ተጎዋዳኝ ሆነው የሚሰሩት እነማን ናቸው?
4,ቅዱሳን መላእክት

ወንጌል ማለት የምስራች ነው ። የምስራች የሚባለው ደሞ ላልሰማ ሰው ቀድሞ ማብሰር ከተቻለ ነው ። በዚህ ረገድ መላእክትን ስንመለከት ➣በሉቃስ 1፥26-30 ለማርያም የጌታን መፀነስ ያበሰረ መለአክ ነው ። ➣በሉቃስ2፥8-15 የጌታን መወለድ ለእረኞች ያበሰረ መለአክ ነው። ➢በሉቃስ 24፥1-4 የጌታን ትንሳኤ ለነመግደላዊት ያበሰረ መለአክ ነው። ➢በሐዋ1፥10 የጌታ ኢየሱስን እርገትንና ምፃቱን ያበሰሩ መላእክት ናቸው።
ከዚህም በተጨማሪ ➢በሐዋ 10፥1-6 ቆርኔሌዎስ ወንጌል እንዲሰማ ወደ ጴጥሮስ የመራው እንዲሁም ➢በሐዋ 8፥26 ፊልጶስ ደህንነት ወደ ሚያስፈልገው ኢትዩጵያዊው ጃንደረባ የመራው መለአክ እንደሆን መፅሀፍ ይነግረናል።

እንግዲህ በወንጌል አገልግልት ስንሰማራ ጌታ ኢየሱስ ፣ እግዚአብሔር አብ ፣ መንፈስ ቅዱስና ቅዱሳን መላእክት ከእኛ እንደሚሰሩ ከተገነዘብን፤ እጅግ የታደልን መሆናችንን አውቀን አገልግሎታችንን በትጋት ልንፈፅም ይጠበቅብናል ።

@yemezmurtenatdebter
@yemezmurtenatdebter
Share and join

ለምድራችን ኢትዮጲያ በያለንበት ወደ እግዚአብሔር እንጩህ
ሰላም ለኢትዮጵያ
በኢየሱስ ስም አሜን