Get Mystery Box with random crypto!

#ከንስሐ_ርቀን_ይቅርታን_አናገኝም ንስሐ ለተጠመቁ ሰዎች ከጥምቀት በኋላ የተሰጠች ሀብት ናት። | የመዝሙር ደብተር™

#ከንስሐ_ርቀን_ይቅርታን_አናገኝም

ንስሐ ለተጠመቁ ሰዎች ከጥምቀት በኋላ የተሰጠች ሀብት ናት። ይህንንም የሚያስረዳ ነገር በጥምቀት ከእግዚአብሔር ከምትገኝ ልጅነት ሁለተኛ ማዕረግ ናት። በሃይማኖት ገንዘብ ያደረግነው የመንግስተ ሰማይ መያዣ ከናት።

በንስሐ ምክንያት የእግዚአብሔርን ቸርነት እናገኛለን። ንስሐ ለሚሿት ሰዎች የተከፈተች የይቅርታ በር ናት። በንስሐ በርነት ከፈጣሪ ወደሚገኝ ቸርነት እንቀርባለን። መከላከያ ከሚሆን ከንስሐ ርቀን ይቅርታን አናገኝም፡፡

አምላክ የጻፈው መጽሐፍ እንደተናገረ ሁላችን በድለናልና ያለ ዋጋ በይቅርታው ከኃጢአት እንነጻለን። ንስሐ እግዚአብሔርን በመፍራት፣ በሃይማኖትና በልቡና የምትገኝ ሁለተኛ ጸጋ ናት። ሀብታተ ምስጢራት ከሚገኙበት ከመንፈሳዊ ፍቅር እስክንደርስ ድረስ የሚጠብቀን መንፈሳዊ ዕውቀት ነው።

(ምክር ወተግሣጽ ዘማር ይስሐቅ)


ቻናላችንን በመቀላቀል አብረውን ይዘምሩ ተዋሕዶን ይደግፉ

@yemezmurdebiter
@yemezmurdebiter
@yemezmurdebiter
@yemezmurdebiter
#በወልደ_ዮሐንስ