Get Mystery Box with random crypto!

ልብ በቦርሳ ይች ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቷት ሴልቫ ሁሴን ትባላለች እድሜዋ 39 ሲ | የማለዳ ብስራት

ልብ በቦርሳ

ይች ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቷት ሴልቫ ሁሴን ትባላለች እድሜዋ 39 ሲሆን የሁለት ልጆች እናት ናት። ምስሉ ላይ እንደምታዩት ልቧን በዚህ ቦርሳ ውስጥ ይዛ ነው የምትዞረው።

ነገሩ እንዲህ ነው፤ የዛሬ 3 አመት አካባቢ ልቧ በአርቴፊሻል ልብ በቀዶ ህክምና ተተካ። ግን አርቲፊሻል ልቧ የሚገኘው በዚህ ቦርሳ ውስጥ ነው። እናም በሄደችበት ቦታ ሁሉ ትይዘዋለች። የሴልቫ ሁሴን ቦርሳ ውስጥ ያለው የሰውነቷን ደም የሚገፋ ሞተር ሲሆን ይህን ሞተር የሚያንቀሳቅሱ ሁለት ባትሪዎች አሏት። ሴልቫ በሁለተኛው ቦርሳ ውስጥ ተጠባባቂ ባትሪ ስላላት የመጀመርያው በድንገት በችግር ምክንያት ስራውን ቢያቆም ወዲያው በሌላ ባትሪ ይተካል ማለት ነው።

እንዲህም ባለ ሁኔታ ውስጥ ሰው ይኖራል በረከታችንን እንቁጠርና ፈጣሪያችንን እናመስግን

@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
@yemaledabisrat