Get Mystery Box with random crypto!

የቅድስት ሥላሴ ልጆች ማህበር

የቴሌግራም ቻናል አርማ yekdset_selase_lejoch — የቅድስት ሥላሴ ልጆች ማህበር
የቴሌግራም ቻናል አርማ yekdset_selase_lejoch — የቅድስት ሥላሴ ልጆች ማህበር
የሰርጥ አድራሻ: @yekdset_selase_lejoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.25K
የሰርጥ መግለጫ

ቅድስት ሥላሴ
#ማህበሩ አላማዉ
፩.ኦርቶዶክስአዊ ስርአትን የጠበቁ አስተማሪ ትምህርቶች፣ መዝሙር፣ጥያቄ እና መልሶችን ለተዋህዶ ልጆች ማቅረብ፤
፪.የሥላሴ ልጆችን ሰብስቦ ማህበር በመፍጠር ቅዱስ ስራዎችንመስራት …

የመወያያ ግሩፕ ላይ ቤተሰብ ለመሆን የምትፈልጉ
@enamsgen @enamsgen
ለማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት @kiya17 ያድርሱን

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-27 07:21:16 https://t.me/yekdset_selase_lejoch
160 views【kiya】, 04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 07:18:14 https://t.me/yekdset_selase_lejoch
160 views【kiya】, 04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 07:15:02 https://t.me/yekdset_selase_lejoch
159 views【kiya】, 04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 18:33:54
468 viewsባሕራን, 15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 18:33:50




ሞትን ስላለመፍራት !


" ሊፈራ የሚገባውንና ልክ እንደ እሳት አእምሮ የሚያሳጣውን ኃጢአትን ግን አንፈራም ! "

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


" “ ወንድሞች ሆይ ! በአእምሮ ሕፃናት አትኹኑ ፣ ለክፋት ነገር ሕፃናት ኹኑ እንጂ” ብዬ እናገር ዘንድ ፍቀዱልኝ [፩ኛ ቆሮ.፲፬፥፳]፡፡

ኃጢአትን ሳይኾን ሞትን የምንፈራ ከኾነ ፍርሐታችን የሕፃናት ፍርሐት ነውና፡፡ ጨቅላ ሕፃናት ጭምብል ያስፈራቸዋል ፤ እሳትን ግን አይፈሩም፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ድንገት ወደ በራ ሻማ ብንወስዳቸው ምንም ሳይፈሩ እጃቸውን ወደ ሻማውና ወደ እሳቱ ይዘረጋሉ ፤ ፈጽሞ የተናቀ ጭምብል ግን ያስፈራቸዋል። እኛን ሊስፈራን የሚገባው እሳት እነርሱን ምንም አያስፈራቸውም፡፡

እኛም ልክ እንደ እነርሱ እጅግ ሊናቅ የሚገባውን ጭምብል - ይኸውም ሞትን - እንፈራለን ፤ ሊፈራ የሚገባውንና ልክ እንደ እሳት አእምሮ የሚያሳጣውን ኃጢአትን ግን አንፈራም! እንዲህ እንድንኾን የሚያደርገንም የነገሮቹ ተፈጥሮ አስፈሪ ስለ ኾነ ሳይኾን የራሳችን ስንፍና ነው ፤ ሞት ምን እንደ ኾነ ብናስተውል ኖሮ በየትኛውም ጊዜ ባልፈራነው ነበርና፡፡

እንግዲህ እስኪ ንገረኝ ! ሞት ምንድን ነው?

ሞት ማለት ልብስ እንደ ማውለቅ ነው፡፡ ሥጋ የነፍስ ልብሷ ነውና ፤ ይህን ልብሳችንን ለጥቂት ጊዜ ካወለቅን በኋላም እጅግ ደስ በሚያሰኝ ውበት መልሰን እንለብሰዋለን፡፡ የሞት ትልቁ ነገርስ ምንድን ነው? ለተወሰነ ጊዜ መጓዝና ከተለመደው ሰዓት በላይ መተኛት ነው! ስለዚህ ሞትን የምትፈራው ከኾነ እንቅልፍንም ልትፈራው ይገባሃል!

ለሚሞቱ ሰዎች የምታዝንላቸው ከኾነ ለሚበሉና ለሚጠጡ ሰዎችም እዘንላቸው ፤ መብላት መጠጣት ባሕርያዊ እንደ ኾነ ኹሉ ሞትም እንደዚህ ነውና! ነገር ግን ባሕርያዊ የኾኑ ነገሮች አያሳዝኑህ ፤ ከክፉ ምርጫ የተነሣ የሚመጡ ነገሮች ያስለቅሱህ እንጂ፡፡

በሚሞተው ሰው አትዘን ፤ በኃጢአት በሚኖረው እንጂ!"


እውነተኛ መከራ ማለት በእግዚአብሔር ላይ ማመጽና እርሱን ደስ የማያሰኘውን ሥራ መሥራት ነው ፡፡

እስኪ ንገረኝ! ሞት ውስጥ ምን የሚያስፈራ ነገር አለ? ወደ ሰላማዊ ማረፊያና ሁከት ወደ ሌለበት ሕይወት ፈጥነህ እንድትኼድ ስላደረገህ ነውን? ምንም እንኳን ሰው እንድትሞት ሊያደርግህ ባይገባም የተፈጥሮ ሕግ ግን በቆይታ ይሰርቅሃል ፤ ነፍስህን ከሥጋህ ይለየዋል ፤ ይህ አሁን እያስፈራን ያለው ሞት አሁን ባይመጣብን እንኳን ወደፊት የማይቀር ነው።

ይህንንም የምናገረው [እንደ አሁኑ ያለ ሌላ] ስጋት ወይም የሚያሳዝን ድርጊት እንዲመጣ በመጠበቅ አይደለም - እግዚአብሔር ይህን ያርቅልኝ! ነገር ግን ይህንን የምለው ሞትን በሚፈሩ ሰዎች እጅግ ስለማፍር ነው። አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ! “ዓይን ያላየው ፣ ጆሮ ያልሰማው ፣ የሰውም ልብ ያልሰማው” በጎ በጎ ነገሮችን እየጠበቅህ እያለ በዚህ ደስታ ትጠራጠራለህን? [፩ኛ ቆሮ.፪፥፱]፡፡ ተጠራጥረህስ ቸልተኛና ሰነፍ ትኾናለህን? ሰነፍ ብቻ ሳትኾንስ ትፈራለህን? ትንቀጠቀጣለህምን?

ቅዱስ ጳውሎስ በአሁኑ ሕይወት ሲቃትትና ለሮሜ ሰዎችም ፦ “ፍጥረት ኹሉ በአንድነት ይቃትታል ፤ የመንፈስ በኵራት ያለን ራሳችንም እንቃትታለን” ብሎ ሲጽፍ አንተ ሞትን ፈርተህ ስትጨነቅ አታፍርምን? [ሮሜ.፰፥፳፪]፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ብሎ ሲናገር ሊመጡ ያሉ ነገሮችን በመናፈቁ እንጂ የአሁኑ ዓለም ነገሮችን ሲናቅፍ አይደለም፡፡

እንዲህ ማለቱ ነውና ፦ “ከዚያ ጸጋ ቀምሻለሁና እኔ ፈቅጄ ወደዚያ መኼድን አልዘገይም፡፡ የመንፈስ በኵራት አለኝ ፤ ይህንንም ለኹሉም አስተላልፋለሁ። እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጥቂያለሁ ፤ ማንም ሊናገርለት የማይቻለውንም ክብር አይቻለሁ ፤ እነዚያ አንጸባራቂ ቤቶችን ተመልክቻለሁ ፤ እዚህ ስቆይ ከምን ያህል ደስታ የራቅሁ እንደ ኾነ ተምሬያለሁ ፤ ስለዚህም እቃትታለሁ።”

እንበልና አንድ ሰው እጅግ ያማሩ የተወደዱ ቤቶችን አስጎበኘህ ፤ ግድግዳው በወርቅ ቅብ የተቀባና ኹሉነገሩ እጅግ አንጸባራቂ የኾነን ቤት አሳየህ፡፡ ይህን ካደረገ በኋላም አንዲት ደሳሳ ጎጆ ወዳለው ሰው ወሰደህ ፡ ይህን ሲያደርግ ግን በቅርብ ጊዜ አስቀድሞ ወዳሳየህ ወደ እነዚያ ቤተ መንግሥት ወደ መሰሉ ቤቶች እንደሚመልስህና ከእነርሱ አንዱም ለዘለዓለም ለአንተ እንደሚሰጥህ ቃል በመግባት ነው።

እንግዲህ ንገረኝ ! ወደዚያ ቤትህ እስክትገባ ድረስ ባሉት በእነዚህ ጥቂት ቀናት ውስጥ “መቼ በደረሰ” እያልህ አትናፍቅምን? አትቸኩልምን? ስለዚህ ስለ መንግሥተ ሰማያትና ስለ ምድር አስብና ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ኾነህ ቃትት ፤ ሞትን ፈርተህ ሳይኾን አሁን ያለውን ሕይወት እያሰብህ ቃትት !"

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]


421 viewsባሕራን, 15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 22:38:32
42 viewsባሕራን, 19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 22:38:30


✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

✞ እንኩዋን ለቅዱሳን ጻድቃን "እንድራኒቆስ ወአትናስያ" እና ለአቡነ "ፊልዾስ ዘደብረ ሊባኖስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞


† ጻድቃን እንድራኒቆስ ወአትናስያ †

ሁለቱ ቅዱሳን ባል እና ሚስት [ባለትዳር] ናቸው:: የነበረበት ዘመን ፬ [4] ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: እስኪ እግዚአብሔር የቀደሰው ጋብቻ ምን እንደሚመስል እንመልከት::

እንድራኒቆስና አትናስያ በዘመናቸው ከልጅነት ጀምረው ቃለ እግዚአብሔርን የሚሰሙ : ለወላጆቻቸው የሚታዘዙ ነበሩ:: ዘመኑ ደርሶ በሚገባው የተክሊል ሥርዓት ጋብቻቸውን ፈጸሙ:: ፵ [40] ቀን ከተፈጸመ በሁዋላ ከምንም ነገር በፊት ፪ [2] ቱ ቁጭ ብለው ተወያዩ::

የውይይታቸው ርዕስ ደግሞ "ፈጣሪያችን በምን እናስደስተው" የሚል ነበር:: ውይይታቸው የጠናቀቀው በእነዚህ ውሳኔዎች ነው::

፩. ሁልጊዜም እንግዳ መቀበል አለብን::

፪. ነዳያን ከቤታችን ሊጠፉ አይገባም::

፫. ጸሎት : ጾምና ስግደት በቤት ውስጥ አይቁዋረጥም::

፬. አብሮ ለመተኛት መቸኮል የለብንም::

እነርሱ መልካምን አስበዋልና አምላክ የሰጣቸውን ሃብት ሲመጸውቱ ኖሩ:: ከዘመናት የቅድስና ጉዞ በሁዋላ በፈቃደ እግዚአብሔር ፪ [2] ልጆችን አከታትለው ወለዱ:: ወንዱን "ዮሐንስ" : ሴቷን ደግሞ "ማርያም" አሏት::

እነርሱን ከወለዱ በሁዋላ እንደ ገና ሌላ ውሳኔ አሳለፉ:: "ይህንን ላደረገልን ጌታ ከዚህ በሁዋላ አልጋ እንለያለን" ብለው ለ፲፪ [12] ዓመታት በጾምና በጸሎት ተወሰኑ::

ሕጻናቱ ዮሐንስና ማርያም በቅንነት አድገው እድሜአቸው ፲፪ [12] ሲሆን ፪ [2] ቱም በአንድ ቀን ታመው ሞቱ:: ይህ ለአንድ ወላጅ የመጨረሻው አሰቃቂ ፈተና ነው:: ሁሉቱም [እንድራኒቆስና ሚስቱ አትናስያ] ልጆቻቸውን ታቅፈው ወስደው ቀበሩ::

እንድራኒቆስ ከቀብር በሁዋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ምርር ብሎ አለቀሰ:: ግን እንዲህ አለ :-
"አምላከ ኢዮብ! አንተ ሰጠኸኝ:: አንተም ነሳኸኝ:: ስምህ ለዘለዓለም ይባረክ" ብሎ ሔደ:: እናት አትናስያ ግን ከሐዘን ብዛት ልቡናዋ ሊሠወር ጥቂት ቀረው::

የልጆቿ መቃብር ላይ ተደፍታ ስታለቅስ ቅዱስ መልአክ ልቡናዋን ወደ ሰማይ አሳረገው:: ልጆቿ ዮሐንስና ማርያም በገነት ውስጥ ከቅዱሳን ጋር ሐሴትን ሲያደርጉም ተመለከተች:: ወዲያው ወደ ቤት ተመልሳ ለባሏ እንድራኒቆስ ያየችውን ነገረችውና ደስ አላቸው::

እዛው ላይ "ለዚህ ውለታው ከነፍሳችን ውጪ የምንሰጠው የለም" ብለው ሊመንኑ ተስማሙ:: እጅግ ሃብታሞች ነበሩና ነዳያንን ሰብስበው : ሃብት ንብረታቸውን : ቤት ርስታቸውን አካፍለው ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሔዱ::

እርሷ ከሴቶች ገዳም : እርሱ ደግሞ ከወንዶቹ ገቡ:: ለ፲፪ [12] ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ለፈጣሪያቸው ተገዙ:: በእነዚህ ዘመናት ተያይተው : አንዱ ስለ ሌላው ሰምቶ አያውቅም:: በጸሎት ግን ያለማቁዋረጥ ይተሣሠቡ ነበር::

ከ፲፪ [12] ዓመታት በሁዋላ የፍቅር አምላክ በሁለቱም ልቡና በተመሳሳይ ሰዓት : ተመሳሳይ ሐሳብን አመጣ:: እርሱ ከአበ ምኔቱ [ታላቁ_አባ_ዳንኤል] : እርሷም ከእመ ምኔቷ አስፈቅደው ወደ ኢየሩሳሌም ከቅዱሳት መካናት ለመባረክ ጉዞ ጀመሩ:: በየፊናቸው ጥቂት እንደተጉዋዙ እርስ በርስ ተያዩ::

እርሷ ለየችው:: እርሱ ግን ጭራሽ ሊለያት አልቻለም:: ይህም ጥበበ እግዚአብሔር ነው:: ፪ [2] ቱም እየተጫወቱ : እየጸለዩ በሰላም ተባርከው ወደ ግብጽ ተመለሱ:: በእነዚህ ጊዜያት ቅድስት አትናስያን የሚለያት አልነበረም:: አካሏ በገድል ከመለወጡ ባሻገር የለበሰችው እንደ ወንድ መነኮሳት ነበር::

ወደ ገዳመ_አስቄጥስ ሲደርሱ ጸጋው ተሰጥቶታልና አባ_ዳንኤል ባልና ሚስት መሆናቸውን አወቀ:: "ለምን አብራችሁ አትኖሩም?" አላቸው:: "እኛ ደስ ይለናል" አሉት:: ከዚያ እርሷ እያወቀችው: እርሱ ሳያውቃት ለ፲፪ [12] ዓመታት አብረው በቅድስና ኖሩ::

ከእነዚህ ዘመናት በሁዋላ ግን ሐምሌ ፳፰ [28] ቀን ቅድስት አትናስያ ታመመች:: አባ ዳንኤል ሥጋውን ደሙን አቀብሏትም ዐረፈች:: ሊገንዟት ሲቀርቡ ቅዱስ እንድራኒቆስ መልኩዋን ልብ ቢለው ሚስቱ ናት::

በአንድ ጊዜ ሚስቱንና የሚወደውን ባልንጀራ በማጣቱ አለቀሰ:: እርሷን ቀብረው ወደ በዓቱ ተመልሶ "ጌታ ሆይ! ውሰደኝ?" አለ:: እርሱም ተከትሏት ዐረፈ:: አባ ዳንኤል እርሱንም ቀብሮ ጥዑም ዜናቸውን ጻፈ::


† አባ ፊልዾስ ዘደብረ ሊባኖስ †

ታላቁ ኢትዮዽያዊ ጻድቅ: ሐዋርያና ሰማዕት አቡነ_ፊልዾስ የጻድቁ አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሲሆኑ የተወለዱት በምድረ ሽዋ በ፩ ሺህ ፪መቶ ፷፮ [1266] ዓ/ም ነው:: ከልጅነታቸው ጀምረው ምሥጢር ተመራማሪና መጻሕፍትን መርማሪ የነበሩት ጻድቁ የመነኑት ገና በ፲፭ [15] ዓመታቸው ነበር::

+በደብረ_ሊባኖስ በአሞክሮ ለ፫ [3] ዓመታት ቆይተው መንኩሰዋል:: ለ፳፪ [22] ዓመታትም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሆነው አገልግለዋል:: አቡነ ተክለ ሃይማኖት በ፲፻፫፻፮ [1306] ዓ/ም ነሐሴ ፳፬ [24] ቀን ሲያርፉ የተተኩት አባ ኤልሳዕ ቢሆኑም ለ፫ [3] ወራት ቆይተው ዐርፈዋል::

በ1307 ዓ/ም አቡነ ፊልዾስ የደብረ ሊባኖስ አበ ምኔት [እጨጌ] ሁነዋል:: ገዳሙንም ለ፳፰ [28] ዓመታት መርተዋል:: ከዚያም በዘመነ አፄ ዓምደ ጽዮንና በአፄ ሰይፈ አርዕድ ብዙ ስደት: መከራ: እሥራትና ግርፋት ደርሶባቸዋል:: ምክንያቱ ደግሞ እውነትን መናገራቸውና ነገሥታቱን መገሰጻቸው ነበር:: በስደትም ለ፮ [6] ዓመታት ከ፱ [9] ወራት ቆይተዋል::

ሃገሪቱን በስብከተ ወንጌል ካበሩ ፲፪ [12] ቱ_ንቡራነ_እድ አንዱ የሆኑት እጨጌ አባ ፊልዾስ በተወለዱ በ፸፬ [74] ዓመት ከ፱ [9] ወራቸው በ፲፻፫፻፵፩ [1341] ዓ/ም ዐርፈዋል:: የተቀበሩት በደብረ_ዕንቁ ሲሆን ካረፉ በ፻፵ [140] ዓመት አቡነ_መርሐ_ክርስቶስ ዐጽማቸውን አፍልሰዋል::

ከቅዱሳኑ እንድራኒቆስ ወአትናስያ እና ከጻድቁ አቡነ ፊልዾስ በረከትን ይክፈለን::



ሐምሌ ፳፰ [28] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

፩. ቅዱሳን ጻድቃን እንድራኒቆስና አትናስያ
፪. አቡነ ፊልዾስ ጻድቅ [ዘደብረ ሊባኖስ]

ወርኀዊ በዓላት

፩. አማኑኤል ቸር አምላካችን
፪. ቅዱሳን አበው [አብርሃም : ይስሐቅና ያዕቆብ]
፫. ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
፬. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ [ሰማዕት]

"ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል:: ከሚስቱም ጋር ይተባበራል:: ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ:: ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው:: እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርትስቲያን እላለሁ:: ሆኖም ከእናንተ ደግሞ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደ ራሱ አድርጐ ይውደዳት:: ሚስቱም ባሏን ትፍራ::" [ኤፌ.፭፥፴፩] (5:31)


† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †


[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


40 viewsባሕራን, 19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 18:44:33
83 viewsባሕራን, 15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 18:44:32


" ጠላት በየት በኩል ይገባል ? "

---------------------------------------------------




" ባሕታዊው ቴዎፋን የሰውን ነፍስ በንጉሥ የሚመስለው ሲሆን ሥጋውን ደግሞ በንጉሥ ቤተ መንግሥት ይመስለዋል፡፡ ይህ ቤተ መንግሥት አምስት መስኮቶችና አንድ በር አለው፡፡

እነዚህ አምስት መስኮቶች አምስቱ የስሜት ሕዋሳት ናቸው፡፡ በሩ ደግሞ አእምሮ ነው፡፡ ጠላት በመስኮትና በበር ካልሆነ በቀር በየትም ሊገባ አይችልም፡፡ እነዚህ ከተዘጉ ጠላት ለመግባት አይችልም፡፡

በእነዚህ መስኮቶች [የስሜት ሕዋሳት] የኃጢአት ነጋዴ ዲያብሎስ ልዩ ልዩ ልምምዶችንና ነፍስን የሚያስደስቱ ስሜቶችን ያመጣል፡፡ በነዚህ የተነሣ ነፍስ እርካታን ጠቅልላ ትይዛለች፡፡ ከዚያም ይህንን እርካታ እንደ ዋና መልካም ነገርና እንደ ግብ መቁጠር ትጀምራለች፡፡ በዚህ መንገድ ነገሩ ይገለበጥና ነፍስ እግዚአብሔርን መፈለግ ትታ ደስታን መሻት ትጀምራለች፡፡

ህዋሶቻችን ለክፉ ነገር የተዘጉ ከሆኑ ጠላት በየትም በኩል ወደ ውስጣችን ሊገባ አይቻለውም ! "


[ አቡነ አትናስዮስ እስክንድር ]


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


84 viewsባሕራን, 15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 22:43:52
114 viewsባሕራን, 19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ