Get Mystery Box with random crypto!

ሞት የምትመስል እንቅልፍ የለሁ ያህል ቅጣኝ በደል እንደረሳ ሺ ከሳሽ እንዲያጣኝ | የቃል ጠብታ

ሞት የምትመስል እንቅልፍ
የለሁ ያህል ቅጣኝ
በደል እንደረሳ ሺ ከሳሽ እንዲያጣኝ
አልንቃ አልቀስቀስ ሌላም ብታነቃ
እስከሚያንቀላፋ የምድሬ ሰቆቃ
ተው አትቀስቅሰኝ አታንቃኝ ግንድ የለም
ሃገሬን ልኑራት በዚህኛው የህልሜ አለም
ሰቆቃዋ አብቅቶ ደስታ ቀኗ ሲደርስ
አንቃኝ የዚያን ጊዜ ንቃቃቷ ሲርስ ።