Get Mystery Box with random crypto!

9ኙ.ሚስጥሮች.tt ቁርኣንን ለመሓፈዝ 9 ሚስጥሮች 1ኛው ሚስጥር : ለቁርኣን ሒፍዝ ከፍተኛ | ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

9ኙ.ሚስጥሮች.tt

ቁርኣንን ለመሓፈዝ 9 ሚስጥሮች

1ኛው ሚስጥር : ለቁርኣን ሒፍዝ ከፍተኛ የሆነ ጉጉት ፣ ፍላጎትና ተነሳሽነት ሊኖርህ ይገባል ፣

2ኛው ሚስጥር : ኢኽላስ (ለአሏህ ብቻ ብሎ መሐፈዝና) አሏህ ቁርኣን ሂፍዝን እንዲያገራልህ ሁሌም ዱዓ ማድረግ ፣

3ኛው ሚስጥር : ሀላፊነቱን ራስህ ውሰድ ፣ ምክንያት አታብዙ (እድሜህ ቢገፋ ፣ የማስታወስ አቅምህ ቢያንስ...)

4ኛው ሚስጥር : በአቅምህ ልክ ሀፍዝ እንዲሁም በአንድ ሙስሓፍ (አንድ ተመሳሳይ ገፅ ያለው የቁርኣን እትም) ብቻ ተጠቀም።

5ኛው ሚስጥር : ለሒፍዝ ተስማሚማ ተዛማች ጊዜና ቦታ ምረጥ (ስሁርና ፈጅር ወቅቶች የተሻሉ ሲሆኑ ማታ አይመከርም ፣ ቦታም ፀጥታ ያለበት ብዙ ቀልብን ሳቢ የሆኑ ነገራቶች የሌሉበት ቢሆን ይመከራል)

6ኛው ሚስጥር : 3ቱንም ዋና የሒፍዝ ሞተሮችን አንቃቸው - አይንህን ጆሮህንና ልብህን ክፍትና ንቁ አድርገህ መሓፈዝ ይኖርብሀል ፣ አንድኛቸውንም ከተውካቸው መሀፈዝህ ትርጉም አልባ ይሆናል።

7ኛው ሚስጥር : በተደጋጋሚ ማጥናትና ሙራጀዓ ማድረግ አትዘንጋ ፣ (ቀኑን ሙሉ እና ከመኝታ በፊት በኦድዬ በማዳመጥ ፣ እንዲሁም በየ ትርፍ ሶላቶች ላይ በመቅራት ሙራጀዓ ላይ ተጠባከር)

8ኛው ሚስጥር : ቋሚማ ወጥ የሆነ ፕሮግራም ይኑርህ ፣ በየቀኑ ምን ያክል ተሀፍዛለህ? ምን ያክሉን ሙራጀኣ ታደርጋለህ? መቼ ሂፍዝ ትጨርሳለህ? ወጥ የሆነና ቋሚ ፕሮግራምና እቅድ ይኑርህ

9ኛው ሚስጥር : ከወንጀል ራስህን አርቅ እንዲሁም አሏህ እንዲያገራልህ ሁሌም ዱዓ በማድረግ ላይ አትስነፍ።

◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል

በOnline ተመዝግቦ ቁርኣን ለመማር በዚህ ሊንክ ያመልክቱ
@FurqanOnlineQuran
ስለ ቁርኣንና የመሳሰሉ ፅሁፎችን ፣ ምስሎችንና ቪዲዬዎችን ለመከታተል ይቀላቀሉን ፣ ለሌሎችም በማካፈል የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!!
https://t.me/furqan_school