ቁርአንን ለመሀፈዝና በደንብ ለማድቀቅ የሚረዱን 5 መሰረታዊ ነጥቦች ስንሀፈዝ የአላህን ፊት ብቻ መፈለግ በእርግጥም ነብያችን صلى الله عليه وسلم አላህ ይጠብቀንና 3 ሰዎች የጀሀነም እሳት ማቀጣጠያ ናቸው ካሏቸው ሰዎች መካከል አንዱ ለእዩልኝና ለሙገሳ ብሎ ቁርአን የሀፈዘ በሀፈዘው የማይሰራ ሰው መሆኑ መናገራቸውን አለመዘንጋትና ሁሌም ንያን ማስተካከልና ነፍስያን መተሳሰብ ። በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ አላህን መለማመጥና ሁሌም ወደ እርሱ መዋደቅ ፣ ሂፍዝ ከመጀመርህ በፊት ቁርአኑን ያስተካከለ ሸይኽ ዘንድ መቅራትና አቀራርህ ለሂፍዝ ብቁ መሆኑ ማረጋገጥ መሀፈዝ ያለብህን መጠን አቅምህን አይተህ መወሰንና በዚያው ላይ መፅናት ፣ ከጊዜህ ላይ ቁርአኑን ምትሀፍዝበት ራሱ የቻለ የተወሰነለት ጊዜም ሊኖረው ይገባል በጭራሽ ቁርአን ለመሀፈዣ ትርፍ ጊዜህን እንዳትሰጥ ካለህ ጊዜ ለሰእርሱ የተቀመጠ ወቅት ሊኖርህ ይገባል ያኔ የጊዜ በረካህንም ታየዋለህ። ◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈ ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል https://t.me/furqan_school 743 viewsFurqan Online Quran, 14:48