Get Mystery Box with random crypto!

አልሀምዱሊላህ በሰላም ተጠናቋል ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር ደሴ ቅርንጫፍ በወሎዋ መና ገ | ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

አልሀምዱሊላህ በሰላም ተጠናቋል

ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር ደሴ ቅርንጫፍ በወሎዋ መና ገሻ በደሴ ከተማ በወሎ ባህል አምባ አዳራሽ ያዘጋጀው የደአዋ ፕሮግራም የሚያምርና የተሳካ ነበር።

በዛሬው እለት መጋቢት 3 /2015 በወሎዋ መናገሻ በደሴ ከተማ ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር ደሴ ቅርንጫፍ ያዘጋጀው የደአዋ ፕሮግራም እጅግ በጣም የሚያምርና አስደሳች ፕሮግራም ነው።

በዛሬው እለት በወሎ ባህል አምባ አዳራሽ የተዘጋጁ የደአዋ ፕሮግራሞች

በኡስታዝ ሙሀመድ አረብ
ተምሳሌቶቻችን

በኡስታዝ ኑረድን ቃሲም
ወጣትነት: እንከኖቹና መሻገሪያዎቻቸው

በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር
ስንቀ–ረመዷን የሚሉ ነበሩ።

በሶስቱም ኡስታዞች የተሰጡ ዳዕዋዎች እጅግ በጣም ውስጥን የሚያናግሩ ፣ማንነትን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ወጣቱ፣ሴቱ፣ወንዱ እና ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ትክክለኛ የሆነውን ቁርአንና ሀድስን እንድከተል፣ ነብዩ(ሰዐወ) ምን እና እነዛን ምርጥ ትውልዶች አርአያ ሞደሉ አድርጎ እንድይዝና መጤ ከሸሪአ ውጭ የሆኑ አስተሳሰቦችን እንድርቅ በሚያምር አንድበት ተናግረዋል።

ወሏህ በሱናና በተውሂድ ጀግኖች እንድህ አይነት ከቁርአንና ከሀድስ ንፁህ የሆነን ደአዋ እንደመስማት አስደሳች ነገር የለም። የደሴ ከተማ ሙስሊም ማህበረሰብ ሴቱም ወንዱም ንፁህ ደአዋ ለማዳመጥ ያለው ጉጉት እጅግ በጣም ያስደስታል።

አዘጋጅ : ወሎ ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ደሴ ቅርንጫፍ

https://t.me/merkezunadessie