Get Mystery Box with random crypto!

#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች አጅነቢይ ሴትን በቻት ማውራት እንዴት ይታያል ከዚህ | ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች

አጅነቢይ ሴትን በቻት ማውራት እንዴት ይታያል

ከዚህ በፊት በሴት ልጅ #ድምፅ ላይ በኡለሞች መካከል ያለው ልዩነት ማየት ያስፈልጋል። እሱም አመዛኙ ንግግር ድምፅን #ማጣፈጥና_ማማለል እስከሌለበት ድረስ የአጅነቢ ሴት ድምፅ ዓውረት (የተከለከለ ሀፍረት ነገር) አይሆንም። ምክንያቱም አላህ በቁርአኑ እንደሚለው "እናንተ የነብዩ ሴቶች ሆይ ... #ድምፃችሁን አታለስልሱ፣ ምክንያቱም በልቡ በሽታ ያለበት ሰው ይማረካልና።" (ሱረቱል አሕዛብ፣32)
ስለዚህ #አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝና ውስጡ ማማለልና ማለስለስ ከሌለበት የአጅነቢ ሴትን ድምፅ መስማቱ የሚከለከልና ወንጀለኛ የሚያደርገው አይደለም።
ከዚህ በመነሳት #በቻት ወይም #በፅሁፍ_መልእክት መገናኘት የግድና አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘና ውስጡ #ትርፍ_ወሬና #አማላይ ቃላት ከሌሉበት አሁንም የሚከለከል አይሆንም። እንኳን #ድምፅ_አልባው ፅሁፍ አይደለም ድምፅ ላይ እንኳን ቢበዛ በኡለሞች መካከል ልዩነት ቢኖረው ነው።
ነገር ግን ምንም ያክል ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ከግምት ውስጥ በማድረግና ሌላ ተጨማሪና ትርፍ ነገራቶችን ሳይጨምሩ #አስፈላጊና_አንገብጋቢ ጉዳይ ሲያጋጥም በፅሁፍ መልእክትን መቀያየር ካለመከልከሉ ጋር ከዛ ውጭ ግን #በላጩ_መራቁና አለማድረጉ ነው። ምክንያቱም ዲናችን ወደ መጥፎ ነገር የሚወስዱ መንገዶችን #በመዝጋት ላይ የተገነባ ነውና።
ሽህ ሙሀመድ ሷሊህ አል ሙነጂድ ሀፊዞሁሏህ

@yeilmkazna
@yeilmkazna