Get Mystery Box with random crypto!

ይድረስ ..ለማይደርስልን መንግስት ። ። እንደምነህ መንግስት ፥ እኛ አለን በደህና ባመቻቸህልን | ግጥም እና የhane ደብዳቤ❤️

ይድረስ ..ለማይደርስልን መንግስት


እንደምነህ መንግስት ፥ እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልን ፥ የለውጥ ጎዳና
ሺዎችን ገብረን ፣ ለአንድ ብልፅግና
ከሶስት አመት በላይ
እየተሰበርን ፣ " ሰበር" በሚል ዜና
ተራ እየጠበቅን ፣ ለሞት ተሰልፈን
ግፍኛን ተቃውመን ፣ ግፈኛን ደግፈን
ደብዳቤ እየላክን ፣ በደማችን ፅፈን
እኛ አለን በስጋት ፣ እኛ አለን በተድላ
በቀን ሶስት ግዜ
ቁርስ ምሳና ራት ፣ መከራ ስንበላ
አንተ ግን እንዴት ነህ?
እንደምነህልን ፣ ካልንህስ በኋላ?!
እኛ አለን በድሎት
እኛ አለን በፀሎት
ከገዳያችን ጋር ፣ ቀብር ስናስፈጥም
ስንኖር ኢትዮጵያዊ
ስንሞት ምን እንደሆንን ፣ ባናረጋግጥም
እኛ አለን በተአምር ፣ እኛ አለን በደህና
እየተገደልን
"ስልታዊ ማፈግፈግ" ፣ በሚል ፍልስፍና
አንተ ግን እንዴት ነህ?
እልፎች ሚቃወሙህ ፣ እልፎች ሚደግፉህ
እልፎች ሚያወድሱህ ፣ እልፎች የሚነቅፉህ
እንዴት ነው መንግስትህ
ከአዲስ ምእራፍ ጋር ፣ የተመሰረተው?
አንድ አንተን ለማፅናት ፣ ስንቶች ነን ምንሞተው?



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam