Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም እና የhane ደብዳቤ❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ yehanedebdabe — ግጥም እና የhane ደብዳቤ❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ yehanedebdabe — ግጥም እና የhane ደብዳቤ❤️
የሰርጥ አድራሻ: @yehanedebdabe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 93

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-01-15 14:45:29 #አንቺ ባለ ዶሮ

እስቲ ልጠይቅሽ ንገሪኝ ግድ የለም
ይሄ ሞያሽ ምንጩ ከእናትሽ አይደለም

መመጠን መከለስ
ማጠብ ማቁላላቱን በሙሉ ትተሽው
ማረዱን ብቻ
መገንጠሉን ብቻ.......ከወዴት ተማርሽው?


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
75 viewsLiul-ze ማርያም, 11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-04 12:00:33
አበበና ጫላ


አጀንዳ ስታጣ ፣ በስም አትጣላ!
አንተም ጩቤ ጨብጥ ፣ አንተም በሶ ብላ
ጨቡዴ ሁን ሀጎስ ፣ አቶቴም ሁን ሺፋ
ማንም ይበሉህ ማን ፣ ሲጠሩህ አትጥፋ
አቤት በል በኩራት ፣ ክብርህን አትጣው
መልአክ ቢሆንም ፣ ስምን የሚያወጣው
እኛ ግን እኛ ነን ፣ ሀያል ያልበገረን
አለማወቅ እንጂ ፣ የሚያከራክረን
እንዳልተገዛን ነው ፣ ስማችን ሚነግረን።
።።።
አሁን ለምሳሌ
ምኒሊክ ተወልዶ ፣ ባይጠገን ቅስሜ
ምኒልክ ተወልዶ ፣ ባይፈታ ህልሜ
በላቶቪች ነበር ፣ በላይ ሚሉት ስሜ!


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
71 viewsLiul-ze ማርያም, 09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-26 12:07:35 ትናንትና ማታ
(በዕውቀቱ ሥዩም)
ላሟሟሽ ሲገባኝ፣እንዳሞሌ አጥቤሽ
በመጨረስ ፋንታ
ለነገ ቆጥቤሽ
አስተርፌሽ ለሰው
የጸጸት ሱናሚ ፤ዓለሜን አመሰው፡፡
ምነው ቢቻል ኖሮ
ፈገግታሽን ቋጥሮ
ሙዳይ ውስጥ መደበቅ
ጃንደረባ ቀጥሮ
ጭንሽን ማስጠበቅ
ክፍት ልቤን ይዤ፤ ዝግ ደጅሽን ጠናሁ
በሰበብ ወድጄሽ ፤ያለሰበብ ቀናሁ፡፡
ፍቅር በተባለ፤ ግራ- ገቢ ነገር
ከጨመተው አገር
ከሰከነው ቀየ
መናፍቅ ይመስል፤ ባዋጅ ተነጥየ
እንደካፖርቴ ቁልፍ፤ ልቤን የትም ጥየ
የትም ስከተልሽ
የትም ሆኖ እድልሽ፤
ሁሉ ያንች ወዳጅ
ሁሉ ባላንጣየ
መፈቀር ሆኖ ጣሽ፤ መቅናት ሆኖ ጣየ
ላንቺ ብስል ፍሬ፤ ለኔ ገለባ ግርድ
ላንቺ እቅፍ አበባ፤ ለኔ እቅፍ ሙሉ ብርድ
ማነው የበየነው ፣ይህን ግፈኛ ፍርድ፡፡




➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
57 viewsLiul-ze ማርያም, 09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-19 13:40:53 #ለካስ

ማበጠር ቸግሮኝ ገለባን ከፍሬ፣
እንዲው እንደባከንኩ መልስ አጥቼ ኖሬ፣
ለዚው ጥያቄዬ ለሚወብቅና ለሚያንቀጠቅጠኝ፣
ተመስገን ነው ዛሬ ግዜ ምላሽ ሰጠኝ።


ይኸው የግዜው መልስ ...


ስንዴን ከእንክርዳዱ የምንለይባቸው
ገንዘብና ዝናም ለካስ ወንፊት ናቸው።

#ሄኖክ_ብርሃኑ.....

➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
52 viewsLiul-ze ማርያም, 10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-05 12:39:02 ትንሳኤሽ ናፍቆናል

ልዑል


ድንቅ ሀገራዊ ግጥም ነው ተጋበዙልኝ



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
59 viewsLiul-ze ማርያም, 09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-25 12:16:40 ነጽር(ተመልከት)

ልዑል

ልክ እንደ ዛፍ ፍሬ ነፍስ እየረገፈ
እህልና እንስሳ እየተረፈረፈ
አድባሬው በሞላ ሬሳ ታቀፈ።

እናቶች አነቡ
ህፃናት ተራቡ
ምድርህ ረሰረሰች
በደም አየታጠበች።

ሰሜኑ ታጠነ በባሩዱ ሽታ
ቦረና ተራበ በጥም ተንገላታ
ወለጋ ረገፈ የሰው ዘር በጅምላ
ሬሳም ቀባሪ አጣ በአውሬ አየተበላ።

ነፍሰጡር እናቶች በግፍ ተገደሉ
ጨቅላ ህፃናቶች በእሳት ተቃጠሉ
ረገፉ እንደ ቅጠል በእርሃብ ጠኔ
አልባሽ አጉራሽ አቶ አለቀ ወገኔ።

በበቀል ሴስነው ፀብን ያረገዙ
የጥልን ጦር ታጥቀው ክፋት እየነዙ
የጦቢያን መከራ ስቃዮን አበዙ

አቤቱ

ታዲያ እስከ መቼ ግራህን ትሰጠን?
ታዲያ እስከ መቼ ፊትህን ትነፍገን?
እስከመቼ ታዲያ ሬሳ ታቅፈን?
በረሃብ ቸነፈር በጥም እናልቃለን?

መንሹ በእጅህ ነው ሁሉን ልታጠራ
ነጽር(ተመልከት) አቤቱ ታደገን ሀደራ!



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
77 viewsLiul-ze ማርያም, 09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-21 12:50:07 ይድረስ ..ለማይደርስልን መንግስት


እንደምነህ መንግስት ፥ እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልን ፥ የለውጥ ጎዳና
ሺዎችን ገብረን ፣ ለአንድ ብልፅግና
ከሶስት አመት በላይ
እየተሰበርን ፣ " ሰበር" በሚል ዜና
ተራ እየጠበቅን ፣ ለሞት ተሰልፈን
ግፍኛን ተቃውመን ፣ ግፈኛን ደግፈን
ደብዳቤ እየላክን ፣ በደማችን ፅፈን
እኛ አለን በስጋት ፣ እኛ አለን በተድላ
በቀን ሶስት ግዜ
ቁርስ ምሳና ራት ፣ መከራ ስንበላ
አንተ ግን እንዴት ነህ?
እንደምነህልን ፣ ካልንህስ በኋላ?!
እኛ አለን በድሎት
እኛ አለን በፀሎት
ከገዳያችን ጋር ፣ ቀብር ስናስፈጥም
ስንኖር ኢትዮጵያዊ
ስንሞት ምን እንደሆንን ፣ ባናረጋግጥም
እኛ አለን በተአምር ፣ እኛ አለን በደህና
እየተገደልን
"ስልታዊ ማፈግፈግ" ፣ በሚል ፍልስፍና
አንተ ግን እንዴት ነህ?
እልፎች ሚቃወሙህ ፣ እልፎች ሚደግፉህ
እልፎች ሚያወድሱህ ፣ እልፎች የሚነቅፉህ
እንዴት ነው መንግስትህ
ከአዲስ ምእራፍ ጋር ፣ የተመሰረተው?
አንድ አንተን ለማፅናት ፣ ስንቶች ነን ምንሞተው?



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
71 viewsLiul-ze ማርያም, 09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-14 11:02:01 #ኑ ሰማይ እንስራ

ከጡት የነጠቁት ጨቅላ ልጅ ይመስል
ማኩረፍ ነው አባዜው የሀገሬ ምስል
ያኮረፈ አንጀት
አይመለስ ላንገት፡፡
አባወራውም ዝም
እማወራውም ዝም
አይነቅዝም
እየተባባሉ
የዚህ ቤት ስለቶች ስንቱን በጎች በሉ፡፡
ይልቅስ
ለማረስ ቢሳሉ
ለማጨድ ቢሳሉ
ለማረም ቢሳሉ በወጉ በወጉ
የምስኪን በጎችን አንገቶች ባልወጉ፡፡
እየተብሰልኩ
እየተንገበገብኩ
የምለማመነው
ቆይ ሀገር ምንደነው?
ቆይ አድባር ምንድነው?
በሚል ጥያቄ ነው?

ከአክሱም የረዘመ
ቃየልን ያረመ
ከአባይ የዘለቀ
ሰዶምን የናቀ
አዋሽን ያከለ
ፅዮንን ያከለ
ጊቤን የሸሸገ
ጣናን ላይ ያረገ
ባሮን የከበበ
ፍቅራችን የት ገባ
ልባችን እንደምን ከድብ ጋር አደባ?
ይናፍቃል አይደል
የፀጋዬ ሀገር
ይናፍቃል አይደል
የደበበ ሀገር
ዘመን ተከትለን
ወደላይ ሰርተናት
ከሰው አይን ገብታ በዘር እንዳያጥሯት
የኔና አንቺን ሀገር
እንደላሊበላ ወደታች በሰሯት፡፡

ወደስምጡ
ይምጡ
ይምጡ
ይቀመጡ
ሀሳብ ይቁምና
መንዙማ ይጠጡ ቅዳሴ ይጠጡ፡፡
ህምም እና መዝመም
እንጂማ
ደመና ነን ያሉ
መዝነብም እንዳለ ለምን ይረሳሉ?
የትኛው ደመና
ዘላለም ቆየና፡፡
ሊቁ ምን ሆኖ ነው ደመና ሚያብራራ
ይልቅስ እንዲያውም
ሀገር ሚያስጠልል ኑ ሰማይ እንስራ፡፡

* * * * * * *


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
74 viewsLiul-ze ማርያም, 08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-26 19:31:13 እምዬ ኢትዮጵያ ፣ ብትደላም ብትከፋም
ምላስ ናት ለህዝቧ ፣ ከአፋችን አትጠፋም።
።።።
አፍ በሚባል ዋሻ...
ምላስን የሚያህል ፣ ስጋ ተሸክሞ
ስጋ ባለመብላት ፣ ማንስ ያውቃል ፆሞ?!
:::::::::
ፍስክ ምላስሽን ፣ ባፍሽ ተሸክመሽ
ከዋናው የደም ምንጭ ፣ ልቤ ላይ ታትመሽ
ፆመኛ ነኝ ስትይ ፣ ታስገርሚኛለሽ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ወደ ነፍሴ ገዳም ፣ ስትገቢ መንነሽ
ዓለም በቃኝ ስትይ ፣ የኔው ዓለም ሆነሽ
ታስገርሚኛለሽ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

(በላይ በቀለ ወያ )


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
78 viewsLiul-ze ማርያም, 16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-25 09:54:43 "ሠርግ አማረኝ"
(absurd wedding)
እንዳልኩሽ አልቀረሁም፡፡
አገባሁ እኮ፡፡
ያውም ላንቺ በገዛሁት ቀለበት፡፡(ዕምነት)
ያውም ላንቺ በገዛሁት ነጭ ሱፍ፡፡(ተስፋ)
ያውም ላንቺ ለጫጉላ በተከራየሁት ቤት፡፡(ፍቅር)
:
:
እና ከመጣሽ ....ሠርግ ልጠራሽ ነበር፡፡
ብቻዬን የደገስኩት፡፡
ብቻዬን ...ሠርግ፡፡
የራሴን ጉልበት ስሜ
ከራሴ ቤት ወጥቼ ራሴ አልቅሼ ራሴን አባብዬ
("ወግ ነው ሲዳሩ ማለቀስ" ብዬ)፡፡
ወግ ላይ ነኝ፡፡
ሰው ይታያሻል አይደለ?
ሲያረግድልኝ፡፡
የኔ ሠርግ ለየት የሚለው ጥቁር በጥቁር ያልለበሰ አለመግባቱ ነው፡፡
(ሞትና ሠርግ አንድ ነው)
የዚህ ሠርግ ልዩ መሆኑ ሙዚቃ የለም፡፡ በቃ የቀጥታ ስርጭት ሙሾ ነው፡፡ ሙሉ ባንድም አለ፡፡
የእናቴ እጅ እና ደረት፡፡ (ሲደቃ)
ይሰማሻል?
እናቴ:- "ለኔ ያርገው"
ሕዝቡ:- "እሰይ"
እናቴ:- "እኔ ልውደቅልህ"
ሕዝቡ:- "እሰይ"
እናቴ:- "ካልገባሁ ከመቃብር"
ሕዝቡ :- "አናስገባም ለቅሶኛ (እናቴን) እደጅ ተኛ፡፡ "
ያው
ከሠርጌ በፊት በላኩልሽ ጽሑፍ
"ብቻሰው ይኑር ብዬሽ የለ"
(ረሳሽው እንዴ)
ሠርጌ ላይ
የሚያለቅሱ
የሚያላቅሱ
የሚያለቃቅሱ
የሞተባቸው ትዝ ያላቸው
"የኔስ ቢሞትብኝ ምን ይውጥኝ?" የሚሉ
አዛኞች
እነ እማማ ድንቁ
እነ እማማ ሰልፌ
አጽናኞች
እነ ዘዉዱ
እነ ነስሓ አባት
አስመሳዮች
በሠርጉ የቀኑ
እነ "የቀድሞ ፍቅረኛ ነን" ባይ
"ቀመሶናል" ባይ
"አናቀውም እንዴ" ባይ
ሁሉም ለሠርጉ የበኩሉን አዋጥቷል፡፡
ሁሉም ገምቷል የቻለውን፡፡
እንዲያውም መዳፌን ላስነበብ ሄጄ የሆነ ቀን ሰውየው እጄን ቢያየው አነሰችበትና፡፡ "ይህ መዳፍ ለመነበብ አልደረሰም" አለኝ፡፡ "እና ዕድሌን እንዴት ልወቅ?" አልኩት
"እጅህ እንዲህ ካነሰ ዕድልህን ገምተው" ያለኝን ትዝ አለሽ፡፡
በቃ እሱ እንደገመተው ሆነ፡፡
የዛሬ....
ግምት ወ ሐሜት
"ትናንት እኮ አይቼው ነበር"
"ስንት ነገር አብረን ልንሰራ ነበር"
"ያው የሴት ጣጣ ነው"
"ሱስ ነው መቼም"
"ያስታውቅ ነበረ፡፡ ስለሞት ያወራ ነበር"
"ሰይጣን ነው"
ሌላም ሌላም....
ትመጫለሽ ሠርጌ ነው
:
:
:
አንገቴን ከገመድ የዳረኩበት ቀን፡፡

* * * * * * * * *
(ነፍስ ይማር አይባልም ራሱን ላልማረ)


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
76 viewsLiul-ze ማርያም, 06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ