Get Mystery Box with random crypto!

#ኑ ሰማይ እንስራ ከጡት የነጠቁት ጨቅላ ልጅ ይመስል ማኩረፍ ነው አባዜው የሀገሬ ምስል ያኮረፈ | ግጥም እና የhane ደብዳቤ❤️

#ኑ ሰማይ እንስራ

ከጡት የነጠቁት ጨቅላ ልጅ ይመስል
ማኩረፍ ነው አባዜው የሀገሬ ምስል
ያኮረፈ አንጀት
አይመለስ ላንገት፡፡
አባወራውም ዝም
እማወራውም ዝም
አይነቅዝም
እየተባባሉ
የዚህ ቤት ስለቶች ስንቱን በጎች በሉ፡፡
ይልቅስ
ለማረስ ቢሳሉ
ለማጨድ ቢሳሉ
ለማረም ቢሳሉ በወጉ በወጉ
የምስኪን በጎችን አንገቶች ባልወጉ፡፡
እየተብሰልኩ
እየተንገበገብኩ
የምለማመነው
ቆይ ሀገር ምንደነው?
ቆይ አድባር ምንድነው?
በሚል ጥያቄ ነው?

ከአክሱም የረዘመ
ቃየልን ያረመ
ከአባይ የዘለቀ
ሰዶምን የናቀ
አዋሽን ያከለ
ፅዮንን ያከለ
ጊቤን የሸሸገ
ጣናን ላይ ያረገ
ባሮን የከበበ
ፍቅራችን የት ገባ
ልባችን እንደምን ከድብ ጋር አደባ?
ይናፍቃል አይደል
የፀጋዬ ሀገር
ይናፍቃል አይደል
የደበበ ሀገር
ዘመን ተከትለን
ወደላይ ሰርተናት
ከሰው አይን ገብታ በዘር እንዳያጥሯት
የኔና አንቺን ሀገር
እንደላሊበላ ወደታች በሰሯት፡፡

ወደስምጡ
ይምጡ
ይምጡ
ይቀመጡ
ሀሳብ ይቁምና
መንዙማ ይጠጡ ቅዳሴ ይጠጡ፡፡
ህምም እና መዝመም
እንጂማ
ደመና ነን ያሉ
መዝነብም እንዳለ ለምን ይረሳሉ?
የትኛው ደመና
ዘላለም ቆየና፡፡
ሊቁ ምን ሆኖ ነው ደመና ሚያብራራ
ይልቅስ እንዲያውም
ሀገር ሚያስጠልል ኑ ሰማይ እንስራ፡፡

* * * * * * *


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam