Get Mystery Box with random crypto!

አሳዛኝ-መረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቀባይነቱን ያጣውና በዲፕሎማሲ የተረታው አሸባሪው ሕውሓት ከሰሞኑ | Habesha media

አሳዛኝ-መረጃ

ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቀባይነቱን ያጣውና በዲፕሎማሲ የተረታው አሸባሪው ሕውሓት ከሰሞኑ መከላከያ ሰራዊት እያሳረፈበት ያለውን ዱላ መቋቋም ሲያቅተው ወደ ተራ ውንብድና እንደገባ ተረጋግጧል።

የትግራይን ሕዝብ ማሰቃየት ጎረቤት ማሳጣቱ ሳያንሰው አሸባሪው ሕውሓት ከሰመኑ ደግሞ በሌላ ውንብድና ንጹሃን ሕዝቦች ተምረው እንዳይመረቁ፣ ዘርተው እንዳያጭዱ እክል እየሆነ ይገኛል ይለናል ከታማኝ ምንጭ ያገኘነው መረጃ

በዚህም ከሰሞኑ የአሸባሪው ሕውሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ ቤት ለቤት በመዞር ምልሻና ፋኖ የሆነ ማነው? የሚል ጥያቄ በመጠየቅ በርካታ ንጹሃንን በማሳቀቅና በማሰቃየት ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።

በውንብድና ተግባሩ ከቶም የማይጸጸተው ሕውሓት በቆቦ ከተማ ላይ ከእያንዳንዱ ቤት በትንሹ አስር ሺህ ብር አውጡ በማለት እያስገደደ እንዳለ ይፋ ሆኗል።

ከአሸባሪነት ወደ ተራ ወንበዴነት የተሸጋገረው ሕውሓት ለዕለት ቁርስ ለማግኘት ደፋ ቀና በሚሉ ምስኪኖች ላይ እንዲሁም የባጃጅ አሽከርካሪዎች ቁልፋቸውን እየተቀበለ እንደሚወስድ ተረጋግጧል።

Via #EBN