Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር-መረጃ ሶስተኛ ዙር ጦርነትን በራሱ ቆስቋሽነት የጀመረው አሸባሪው ህውሓት በብዙ ግንባሮች ሽ | Habesha media

ሰበር-መረጃ

ሶስተኛ ዙር ጦርነትን በራሱ ቆስቋሽነት የጀመረው አሸባሪው ህውሓት በብዙ ግንባሮች ሽንፈትን ሲያስተናግድ እንደከረመ ይታወሳል።

በዛሬው የግንባር ውሎ ህወሃት ከፍተኛ ምት እንዳረፈበት ከታማኝ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በዚህም የወገን ጦር የጠላትን ምሽጎች በመስበር ወደ ትግራይ እየገሰገሰ ነው።

በተጨማሪም በዛሬው ዕለት መከላከያ በደረገው ውጊያ በራያ ቆቦ 020 ቆላበላጎ ቁጥጥር ስር እንደገባ ለማወቅ ተችሏል። እንዲሁም ሰቆጣ ዙርያ ልዩ ስሙ ፅፅሩን በመከላከያ ቁጥጥር ስር ገብቷል።

በተከታታይ ሽንፈትን እያስተናገደ የሚገኘው አሸባሪው ህውሓት ሰፍሮበት ከነበረው ከዋግኽምራ ግንባር ዝቋላ ወረዳ ቀዳሚት የተባለውን እስትራቴጂክ ተራራን ለመልቀቅ ተገዷል።

እንዲሁም በሱዳን ድንበር በረከት አካባቢ በተደረገ ጦርነት አሸባሪው ሕውሓት ከነበሩት አምስት ምሽጎች ውስጥ ሁለቱ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ገብቷል። በተጨመሪም መከላከያ ሰራዊት እያካሄደ ያለውን ትግል በመግፋቱ በነገው ዕለት አበርገሌን ሊቆጣጠር እንደሚችል ተገምቷል።

Via #EBN