Get Mystery Box with random crypto!

የመስጠት ትርጉም የአለማችን ቀዳሚ ባለጠጋ በአንድ ኢንተርቪው እንዲህ ተጠየቀ ከአንተ የሚበልጥ ባ | የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

የመስጠት ትርጉም

የአለማችን ቀዳሚ ባለጠጋ በአንድ ኢንተርቪው እንዲህ ተጠየቀ ከአንተ የሚበልጥ ባለጠጋ ማን ነው ?
ከአንተ የሚበልጥህ ባለጠጋ አለ ?

‹‹አዎ የሚበልጠኝ ሰው አለ፡፡ የሚበልጠኝ አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡ ከብዙ ዓመት በፊት ወደ ኒውዮርክ መሄድ ነበረብኝ፡፡ ወደ ኒውዮርክ ለመሄድ አየር መንገድ ላይ ሳለሁ የተለያዩ ጋዜጦችን የጋዜጣ አዟሪዎች እጅ ላይ አየሁ፡፡ ካየኋቸው ጋዜጦች መካከል አንዱን ወደድኩት ለመግዛት አስቤ ኪሴ ስገባ ዝርዝር ስላጣሁ ሳልገዛው መልሼ ተውኩት፡፡

በድንገትም አንድ ጥቁር ጋዜጣ አዟሪ ልጅ መጣና ጋዜጣውን ሰጠኝ፡፡ ዝርዝር የለኝም አልወስደውም አልኩት እርሱም ችግር የለውም በነጻ ውሰደው አለኝና በነጻ ሰጠኝ፡፡

ከሦስት ወር በኋላ ተመልሼ በዚያው አየር መንገድ ማለፍ ነበረብኝና በዚያ አየር መንገድ ሳልፍ አሁንም አጋጣሚ ሆነና ያንን ጋዜጣ አዟሪ ጥቁር ልጅ አገኘሁት፡፡ አሁንም በነፃ ጋዜጣ ሰጠኝ፡፡ እኔም በነፃ አልቀበልህም አልኩት እርሱም ግድየለም ከትርፌ ላይ እቀንሳለሁ ውሰድ አለኝና በነጻ ሰጠኝ፡፡

ከ19 አመትም በኋላ ባለጠጋ ከሆንኩ በኋላ ያንን ልጅ ፈልጌ ለማግኘት ወሰንኩና ፈለኩት ከአንድ ወር ተኩል ፍለጋም በኋላ አገኘሁት፡፡ ከዚያም አወቅከኝ ብዬ ጠየኩት ፡፡ አዎ አውቅሃለሁ ዝነኛው ቢልጌት አይደለህም አለኝ፡፡ ከብዙ አመት በፊት ሁለት ጊዜ ጋዜጣ በነጻ ሰጥተኸኛል፡፡ ያንን ውለታህን አካክሼ መመለስ እፈልጋለሁና የፈለከውን የትኛውንም ነገር እሰጥሃለሁ ጠይቀኝ አልኩት፡፡

ያም ጥቁር ሰው በምንም መካካሻ ልትሰጠኝ አትችልም አለኝ
እኔም ለምን አልኩት
እኔ የሰጠሁህ ደሃ በነበርኩ ጊዜ ከድህነቴ ነው፡፡ አንተ ግን ልትሰጠኝ የመጣኸው ባለጠጋ በሆንክ ጊዜ ነው፡፡ እነዚህን ሁለቱን እንዴት አካክሰህ ልትሰጠኝ ትችላለህ፡፡

ቢልጌትም ያጥቁር ወጣት በርግጥም ከእኔ የሚበልጥ ባለጠጋ ነው፡፡
ለመስጠት ባለጠጋ መሆንህን ወይም ባለጠጋ እስክትሆን ድረስ አትጠብቅ ፡፡ መስጠት የልብ ጉዳይ ነው እንጂ የአቅም ጉዳይ አይደለም፡፡

THANK YOU FOR READING.
ELODIA READING
ኤሎድያ ንባብ!

    #share and join for more

@Elodia_G ንባብ @Elodia_G READING
@Elodia_G ንባብ @Elodia_G READING
@Elodia_G ንባብ @Elodia_G READING