Get Mystery Box with random crypto!

#ሁሉንም ጠይቅ - ሶቅራጠስ ለሶቅራጥስ “አለማወቅን ማወቅ” የፍልስፍና መጀመሪያ ነው፡፡ አለማወ | የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

#ሁሉንም ጠይቅ - ሶቅራጠስ

ለሶቅራጥስ “አለማወቅን ማወቅ” የፍልስፍና መጀመሪያ ነው፡፡ አለማወቃችንን ሳናውቅ የእውቀትን መንገድ መጀመር አንችልም፡፡

በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ “አላውቅም” ማለት የመሃይም ምልክት ሆኖ ቆይቷል። ልክ ኃጢአትን እንደሰራ ሰውም ትቆጠራለህ፤ ችግር እንዳለብህም ይታሰባል። መድኃኒትን ፍለጋም ወደ መምህራን ወይም አዋቂ ወደተባሉ ሰዎች እንድትሄድ ይነገርሃል።

ለሶቅራጥስ ሁለት አይነት አላዋቂነቶች አሉ።

1.አለማወቅን_አለማወቅ።
ይህ በሕይወትህ ላይ ምን እንደማታውቅ ሳታውቅ መኖር ማለት ነው። እነዚህ ራሳቸውን አይጠይቁም አውቃለሁ አላውቅም ብለውም አይመረምሩም፡፡ ሕይወታቸውንም በእንቅልፍ ውስጥ እንዳለ ሰው፣ ሁሉንም አውቃለሁ እያሉ ይኖራሉ፡፡ ሃሳባቸውን ለመመርመር ቆም ብለው አያስቡም፡፡

2.ሶቅራጥሳዊ አለማወቅ ።
ይህ ከእንቅልፋችን ነቅተን እና አይናችንን ገልጠን መጠየቅ ስንጀምር ያለውን ጊዜ ያመለክታል። የምናውቀውን ሁሉ እንጠረጥራለን::

ሁለተኛውን አለማወቅ ሶቅራጥስ የተቀደሰ አለማወቅ ይለዋል፡፡  የምናውቃት ጥቂት ናት፤ ከምናውቀውም የሆነ ጊዜ፣ የሆነ ቦታ ላይ ስህተት መኖሩን እንረዳለን፡፡
ሶቅራጥስ በዚህ አባባሉ ይታወቃል፤ “Unexamined life is not worth living' (ያልተመረመር ሕይወት ሊኖሩት ያልተገባ ነው።)

ምንጭ :- ፍልስፍና ከዘርዓ ያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ

THANK YOU FOR READING.
ELODIA READING
ኤሎድያ ንባብ!

    #share and join for more

@Elodia_G ንባብ @Elodia_G READING
@Elodia_G ንባብ @Elodia_G READING
@Elodia_G ንባብ @Elodia_G READING