Get Mystery Box with random crypto!

#የሰው ልጅ የአዕምሮውን እምቅ አቅም እንዲጠቀም ነገሮችን የመከወን ተነሳሽነት ይፈልጋል። ለስራ ያ | የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

#የሰው ልጅ የአዕምሮውን እምቅ አቅም እንዲጠቀም ነገሮችን የመከወን ተነሳሽነት ይፈልጋል። ለስራ ያለን ተነሳሽነት ደግሞ የህይወት ግባችን ላይ ለመድረስና ደስተኛ ህይወትን ለመኖር ቁልፍ ሚና ይጫወታል።

አምሥቱ የስኬት ምስጢሮች ብለን ያስቀመጥነው

1ኛ. ትኩረተ አመክንዮ :-ጠንካራ የሆነ አመክንዮ ካለን ፡ ፈታኝ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙን እንኳ መስመራችንን እንዳንስት ያግዘናል።

ምናልባት ፡ እኛ የምንፈልገውን ውጤት ለማሳካት ስንል የምናከናውናቸውን ተግባራት ላንወዳቸው እንችል ይሆናል። እንደተራራ የገዘፉና አይነኬ የሚመስሉ መሰናክሎች ሆነውብንም ይሆናል። ነገር ግን የምንፈልገውን የስኬት ማማ ስናስብ  በቀላሉ እናልፋቸዋለን።

2ኛ. ተግባራትን መከፋፈል :-አንድን ተግባር በትናንሽ የድርጊት ክፍሎች መበተን ለዚያ ተግባር ያለን አመለካከት እንዲለወጥ የሚያደርግና አስገራሚ ውጤቶችን እንዲናገኝ የሚያግዝ ጥሩ ዘዴ ነው::

3ኛ. እንደምንችል ለራሳችን ማረጋገጥ!

ለሌሎች ሰዎች ስለራሳችን የምንናገርበት መንገድ በህይወታችን ማድረግ በምንችላለውና በማንችላቸው ነገሮች ላይ ይልቅ ተፅእኖ አለው።

4ኛ. ስራዎችን እንደመዝናኛ ቆጥረን ማከናወን!

የሚያዝናናንን ስራ መስራት ያስደስተናል። ውጥረት ውስጥ የሚከተንንና የማያስደስተንን ስራ መስራት ደግሞ ውጤቱ በተቃራኒው ነው።

ለምሳሌ፡- እኔ አንድን ስራ ለማከናወን ከሚያስፈልገኝ ጊዜ 5 ደቂቃ ቀድሜ ተግባሩን ለመጨረስ ከጣርኩ ፡ ከስራው በኋላ ለመዝናናት የሚሆን ጊዜ እንደሚኖረኝ ስለማስብ ፡ ስራው ጫና ሳይሆን መዝናኛ ይሆንልኛል። ስራን እንደ መዝናኛ የሚመለከቱ ሰዎች አጋጥመዋችሁ ያውቁ ይሆናል። እነዚህ ሰዎች በስራቸው ደስተኞች ናቸው ፡ ምክንያቱን ስራቸውን እንደመዝናኛ ቆጥረውት እየተዝናኑ ስለሚሰሩ ፡ ስልቹ አይደሉም ፤ ከፍ ያለ ተነሳሽነትም አላቸው።

5ኛ. በራስ የመተማመን ስሜትን መገንባት!

ራሳችሁን በነዚህ ሁለት ሁኔታዎች ውስጥ አድርጋችሁ አስቡ፡፡ ለራሳችሁ የህይወት ግብ ለማስቀመጥ የተቸገራችሁበትን አጋጣሚ አስቡ። ምን ተሰማችሁ? ሽንፈት ፣ ድካም ፣ ተስፋ መቁረጥ ፣ መውደቅ ወዘተርፈ አይዴል? እስኪ አሁን ደግሞ የህይወት ግባችሁን ጥርት ባለ መልኩ አስቀምጣችሁ አስቡ፡፡ ይህ በራስ የመተማመን ስሜት ተነሳሽነታችንን በመጨመር ወደምንፈልገው ስኬት የሚያደርሱንን ተግባራት እንድናከናውን አቅም ይሰጠናል::

ELODIA READING
ኤሎድያ ንባብ!

    #share and join for more

@Elodia_G ንባብ @Elodia_G READING
@Elodia_G ንባብ @Elodia_G READING
@Elodia_G ንባብ @Elodia_G READING