Get Mystery Box with random crypto!

እወነት ጥያቄ፦ኦሾ ፣የምትነግረን ነገር በሙሉ እውነት ሆኖ ሳለ ስለምን ብዙኃኑ ይቃወሙሃል? | የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

እወነት

ጥያቄ፦ኦሾ ፣የምትነግረን ነገር በሙሉ እውነት ሆኖ ሳለ ስለምን ብዙኃኑ ይቃወሙሃል?

መልስ፦ትክክለኛ ምክንያት -የምናገረው እውነት መሆኑ ነው።እውነት አደገኛ ናት።

በተለይ ሐሰተኛ የሆነ ተምኔታዊ ሕይወታቸውን በተዋቡ ሕልሞች ሐሰቶች እና አስደሳች በሆኑ ሀሳባዊ ሕልሞች በመኖር ላይ ለምገኙ በሙሉ እዉነት በርግጥም አደገኛ ናት።
እነዚህን መሰል ሰዎች እውነትን በጠላትነት ይመለከቷታል።

ምክንያታቸው ደግሞ ዕድሜያቸውን በሙሉ ያመኑበትን ፣የኖሩበትን ሐሰተኛ አመለካከቶች ስለሚያፈርስባቸው ነው።
እውነት ማለት የሐሰቶች ሁሉ ሞት ናት።በተዋቡ ቃላት የተናገሩትን ሐሰቶች ጨምሮ የምትገድል ናት።
ብዙኃኑ ለምን ነበር ሶቅራጠስ ላይ የተነሡበት? ሃይማኖተኞችስ ለምን ነበር ኢየሱስን የተቃወሙት? የሁለቱም ጥፋት የብዙኃኑን እንቅልፍ እና ያማረ ሕልም መረበሻቸው ነበር።ማንም ከምቹ እንቅልፉ መቀስቀስ አይወድም።
              osho

ከንባብ ዳርቻ ለህይወት ጠኣም
#Share and join for more
@KenibabDaricha
@KenibabDaricha