Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​ ፍቅር ይ | የግጥም ቃላቶች ✍

​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​ ፍቅር

ይንገሩሽ ብዬ ነው

መጠው ይነግሩሻል ይነግሩሻል ሁሉን
በጀሮአቸው ሰምተው በአይናቸው ያዩትን
ይንገሩሽ ብየ ነው ይችኛዋን አቅፏት
ያችንም ጠቀሳት ይችን ሰላም ብሏት
ያችኛዋን ሳማት
ከዚች ጋር አውካካ
ያችን ጡቷን ነካ

ይነግሩሻል ሁሉን በጀሮአቸው ሰምተው
በአይናቸው ያዩትን ይንገሩሽ ብየ ነው

እግርሽ ስር ያኖረኝ
ልክ እንደ ጅራትሽ
አብሮ እሚያዞረኝ
ፍቅር ነበር እንጅ
ሴት እማ አልቸገረኝ

ይንገሩሽ ብየ ነው እንደማልወድ ጥቃት
በናፍቆት መታመም ናፍቆት መቀጣት

ይንገሩሽ ብየ ነው
ፍቅሬን ስትገፊው
እኔን ስትጠይኝ
ከጎኔ እሚቆሙ
ሺ ሴቶች እንዳሉኝ።

ብርሃኑ ዘላለም


ከወደዱት አጋሩ

@yegetemkalat

ፍቅር ብቻ