Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር ልብሽ አያመንታ መውደድሽ ከሆነ የእውነት ከልብሽ ሀሰት ከሌለበት የምትሰጪኝ ፍቅርሽ | የግጥም ቃላቶች ✍

ፍቅር

ልብሽ አያመንታ

መውደድሽ ከሆነ የእውነት ከልብሽ
ሀሰት ከሌለበት የምትሰጪኝ ፍቅርሽ
ከኔ ጋር ለመሆን ልብሽ አያመንታ
መኖር አትችልም ነፍሴ ካንቺ ተለይታ
አንበሳ ያለ ጥርስ ሞገስ እንደሌለው
የኔም ህይወት ያላንቺ ልክ እንደ
አንበሳው ነው
ውዴ!
መሆን ፈልጋለሁ ካንቺ ጋር ዘላለም
አንቺን ለማስደሰት የማልሆነው የለም
እስከ አለም ጥጋጥግ እስካለም ዳርቻ
ወድሻለሁ ፍቅሬ ልኑር ላንቺ ብቻ
ከኔ ጋር ለመሆን ልብሽ አያመንታ
ላኖርሽ ችላለው በደሜ ጠብታ
ለኔዋ ሄዋን

ከወደዱት አጋሩ

@yegetemkalat

ፍቅር ብቻ