Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር ብቻ የሰከንድ እይታ ውዴ የኔ ቆንጆ የልቤ ነበልባል ሀቢብቲ ልበልሽ ወይስ ዝም | የግጥም ቃላቶች ✍

ፍቅር ብቻ


የሰከንድ እይታ

ውዴ የኔ ቆንጆ የልቤ ነበልባል
ሀቢብቲ ልበልሽ ወይስ ዝም ልበል?

ልጥራሽ ላቆላምጥሽ
ከፍ ከፍ ላድርግሽ
በጣም ልሰቃቅልሽ።
ጥፍርሽ ተረከዝሽ
አውራሪስ ባቶችሽ
ከፍ ስል ጋቢናሽ
ዝቅ ስል እንትንሽ
እያልኩኝ ልሰብሽ።
ከዛ በላይ ደግሞ ወገብሽ ሽንቃጣ
ጡትሽ ሎሚ መስሎኝ ልጨምቅሽ ብቃጣ
አንገትሽ ብርሌ ልጠመጠምበት በፍጥነት ብመጣ
ከንፈርሽ ወርቅ ቅብ ልመጥሽ ስወጣ
ልቤ ፈስሳ ቀረች በፍቅርሽ ተውጣ።

እኔም እንድህ አልኳት;
አንቺ የልብ ትንሽ ፈሪ የማትረቢ
ከውብ ልጃገረድ ሩጠሽ ብትቀርቢ
ምነው ተንዘፈዘፍሽ ሳትጠልቂ ሳትገቢ።

መቼ ጨረስኩና;
እንደጠራ ሰማይ ፊትሽ ተወልውሎ
አይንሽ መብራት ያለው ሲወጋኝ ፈልፍሎ
ፀጉርሽ ወርዶ ወርዶ ሳየው ተንዘፋሎ
ይኸው ገባሁልሽ ጠቅልየ ካንቺ ውስጥ
ማንም አያሶጣኝ ቢዘለል ቢቀወጥ።



አንቺየ፣
እኔን የገረመኝ የደነቀኝ ነገር
እንደዚህ ለመክነፍ ለመወደቅ በፍቅር
የፈጀብኝ ጊዜ በጣም አጭር ነበር።
አመት አልፈጀ ወር
ሳምንት ሳይቆጠር
ይህ ሁሉ እይታ በሰከንድ ነበር።


........... ● ●•........
ባር


ከወደዱት አጋሩ

@yegetemkalat

ፍቅር ብቻ