Get Mystery Box with random crypto!

ሽውርር ተስፋ ''''''''''''''''' ያለፈው ክፋት ነው የሚመጣው እንጃ፤ | የግጥም ምሽት በቴሌግራም

ሽውርር ተስፋ
"""""""""""""""""
ያለፈው ክፋት ነው
የሚመጣው እንጃ፤
ዛሬን መዳከር ነው
የሀገሬው ፍርጃ...

ትላንትም ግፍ ነበር
የህይወት ልቅምቅም፤
ከገር ፊታችን ላይ
እንባን የሚያስለቅም...

ይመሻል?..... አናውቅም
ይነጋል?.....አናውቅም፤
ተስፋችን ቢቀበር
አይገርምም አይደንቅም፤
አሁን ሰላም ካለ
ነገን አ'ናፍቅም...
.
እንግዲህ
.
ልቦናህን መርምር
እርምጃህ ቀስ በቀስ፤
ልቦናሽን እዪ
መንገድሽን ቀነስ፤
የቂም ሾተል ይዞ
"ነገን አንጋ" ብሎ
በፀሎት ጌታ ፊት የምን ማለቃቀስ?

አንቅረው ሴራህን
ሽልሽን አራግፊ ክፋት ይጨናገፍ፤
ይህንን አርጎ ነው
ለአዲስ ንጋት ጀንበር አጥብቆ መንሰፍሰፍ...
.
አልያማ
.
በሆድ ክፉ አርግዞ
የነገር ሽል ይዞ
ከነፍስና ስጋ ሳይጠፋ በቅጡ፤
ለፍቅርና ሰላም
በህልም ቅዠት አድረው
በተስፋ ዓለም ላይ ነገን ቢቋምጡ፤
የነገ ቀን ነግቶ
ማርያም ማርያም ቢባል የሰይጣን ነው ምጡ፤
ስህተት ነው ንጋቱ...!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@HAKiKA1
@HAKiKA1