Get Mystery Box with random crypto!

የቆጥ ውበት ''''''''''''''' ከውበትሽ፥ ከስብዕናሽ፥ ቅልውጥ ሄጄ ስስቀመቀም፤ ነግሰሽብኝ፥ | የግጥም ምሽት በቴሌግራም

የቆጥ ውበት
"""""""""""""""
ከውበትሽ፥
ከስብዕናሽ፥
ቅልውጥ ሄጄ ስስቀመቀም፤
ነግሰሽብኝ፥
ከልቤ ላይ፥
ማርከሻሽን ከምን ልልቀም...?

የአንጀት ደዌ
ልክፍት ነው
መወደድሽ ውስጥ ይንጣል፤
ሚቆጠቁጥ፥
የሰማይ ቆጥ፥
ሽቅብ ላይ ነው ልብሽ አይጣል፤
የሾህ ብቃይ፥
ሊሆን ስቃይ፥
በውበትሽ ጅራፍ ቀጣን፤
በአንቺ ሚዛን
ሲወዳደር
ክፉ አይደለም ከቶ ሰይጣን..!

አጃኢብ ነው
ፍቅርሽ ሲጥል
አይፎክርም... አያቅራራ፤
ማስታገሻ
ከቶ የለም
ሲፈጥርሽም እፁብ ስራ፤
ስንቱ አዳም
ለአንቺነትሽ እሱነቱን እየሰዋ፤
የብብቱን ክብር ጣለ
.....ለውበትሽ ሲንጠራራ!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@HAKiKA1
@HAKiKA1