Get Mystery Box with random crypto!

ስምና ኩነኔ '''''''''''''''' ለውሸትሽ ድጋፍ፥ በ.ማ.በ.ል.ሽ አፋፍ፥ እውነትን ቀብተሽ | የግጥም ምሽት በቴሌግራም

ስምና ኩነኔ
"""""""""'''''''
ለውሸትሽ ድጋፍ፥
በ.ማ.በ.ል.ሽ አፋፍ፥
እውነትን ቀብተሽ
በማስመሰል አንባ፥መዝለቅሽ ቢሰምርም፤
ስም ያለው ሞኝ ነው
'ክህደት' ባልኩኝ ቁጥር፥"ወይታሽ" አይቀርም...

አይቀርም

አክብሩልኝ ካለው
ከአስርቱ ትዕዛዝ፥ህግጋት ተላልፎ፤
እንዳትነኩ ካለው
ገነት ከፀደቀው፥እፀ በለስ ቀጥፎ፤
የውሸት ቅኔ ዘርፎ...
የሰው ልጅ በድክመት
በህይወቱ ምላስ፥ኃጥያትን ቢቀስም፤
ዘላለም አለሙን
"እመት'' ሲል ይኖራል
ተደባልቀውበት፥መኮነኛው ከስም!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
ለሌሎች ምርጥ ግጥሞች join በሉ....

@HAKiKA1
@HAKiKA1