Get Mystery Box with random crypto!

ሹም ሽር ''''''''''' አንቺ እቴ ፔንዱለም ፌዝና የምርሽ የተደቃቀለ፤ እዚህ ሲሉ | የግጥም ምሽት በቴሌግራም

ሹም ሽር
"""""""""""
አንቺ እቴ ፔንዱለም
ፌዝና የምርሽ የተደቃቀለ፤
እዚህ ሲሉሽ እዛ
ነፍስሽና ስጋሽ ሁሌ እየዋለለ፤
በውበትሽ ግርማ
አፍቃሪ ከጉያሽ ሲገባ እየዋለ፤
ልቡ እየቀለለ፥
ሰርክ እየማለለ...
በሀሰት ግብርሽ ላይ
ሀቂቃዊ ፍቅሩን ገምዶና ጠቅልሎ፤
ስንቱ አዳም መሰለሽ
በዥዋዥዌሽ ክር የሞተው ተሰቅሎ!


አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
ለሌሎች ምርጥ ግጥሞች join በሉ....

@HAKiKA1
@HAKiKA1