Get Mystery Box with random crypto!

የክብ.....ካብ ''''''''''''''''''''''' እንጀራችን ክቡ፥ ዕድላችን ክቡ፥ መንገዳችን | የግጥም ምሽት በቴሌግራም

የክብ.....ካብ
"""""""''''''''''''''""
እንጀራችን ክቡ፥
ዕድላችን ክቡ፥
መንገዳችን ክቡ...
በመከበብ ዕጣ፥ዕድል ተለውሶ፤
ከቶ አይደርስም ያሉት
እየተቃበዘ ይመጣል መልሶ...

በል ስራህን መርምር
አላማህን መትር እጆችህን አጥና፤
አርምጃህ ሀቅ ይሁን
ከሰው ጫንቃ ውረድ ውልህ ይሁን ቀና...

ዕቅድህን እየው...

ዕቅድህን እየው
አይምሮህን ቃኘው
በማጥ አትዳክር ህልም አለምህ ጠቦ፤
ህይወት አዙሪት ነው
የግፍ እንባ እንደ እባብ ይመጣል ተስቦ...

ተው
ተው እስቲ እረፍ
ነፍስያህን በእውነት ግረፍ

አትድንም
አትተርፍም
ከህዝብ ዕንባ ከሰው ደም ጦስ፤
ቢታጠብስ መቼ ፀዳ
ከኢየሱስ ደም ያ ጲላጦስ?

አፅዳ...
ፈትግ....
አንፃ ሀሳብህ ህሊናህን ቃኘው፤
ባሰብከው ልክ ነው
የሰማይ ቤት ዕዳህ ፍርድህ የሚዳኘው....

አስብ አለምህን
አስብ ህይወትህን
አስብ እምነትህን
አስብ...
አስብ...
አስብ...
ከመኖርህ ጉድጓድ መልካምነት ሰብስብ...!
ሸፍን ገመናህን
ህሊናህን ገንባ በፍቅር ምሰሶ፤
የክብ ነው ነፍስህ
የሰራኸው ሁሉ ይደርሳል መልሶ!

#አስብ!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@HAKiKA1
@HAKiKA1