Get Mystery Box with random crypto!

የፍቅር ለዛ (YEFKIR LEZA)

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefkir_leza — የፍቅር ለዛ (YEFKIR LEZA)
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefkir_leza — የፍቅር ለዛ (YEFKIR LEZA)
የሰርጥ አድራሻ: @yefkir_leza
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 732
የሰርጥ መግለጫ

አሪፍ ,ውብ እና መሳጭ የሆኑ ታሪኮችን አና ግጥሞችን ታገኛላችሁ።
For any comment @ABDU_EMRE

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-14 22:06:02 #ሀያትና_እና_የአይን_ፍቅር
#ክፍል_አስራሶስት

የአቡበከር ጓደኛ ነህ እንዴ? "አዎ የአቡበከር ጓደኛ ነኝ ግን እንዴት ... ብዬ ጥያቄዬን ሳልጨርስ ና በቃ እዚህ የማውቀው ሰው ስለሌለ አብረን ምሳ እንብላ አለችኝ እኔም በውስጤ አቡበከርን እንዴት ልታውቀው እንደቻለች እየሰብኩ ወደ ካፌ ሄደን አዘን ከበላን ቡሀላ ወደ መናፈሻ ሄደን ተቀመጥን በእውነቱ ሀዩን አይደለም እንደዚህ መቅረብ ማውራት አብሮ መብላት ይቅርነሰ አጠገቧ እቀርባለሁ ብዬም አስቤ አላውቅም...

እንደምወዳት በሷ ፍቅር ምን ያህል እንደተጎዳሁ ልነግራት ብፈልግም ገና በመጀመሪያ ቀን መናገሩ ተገቢ መስሎ ስላልታየኝ ከመናገር ተቆጥቤለሁ ምን አልባት ኢክራም ደብዳቤዋን ሰጥታት ከሆነ ብዬ "ኢክራም ስለ እኔ የነገረችሽ ወይም የሰጠችሽ እቃ አለ እንዴ?" አልኳት አንገቴን አቀርቅሬ <አረ ምንም አልነገረችኝም ከተገናኘን ቆይተናል ምነው ሰላም አይደለችም እንዴ?> " አረ ምንም አልሆነችም እኔም ካገኘሆት ቆይቻለሁ የተፈጠረ ነገር የለም ዝም ብዬ ነው የጠየቅኩሽ በቃ እኔ ልሂድ ቤት በጊዜ መድረስ አለብኝ ብዬ ተሰናብቼት ከጊቢ ወጣሁ ብችል ከሷ ጋር ባልለይ እና ሁሌም ከሷ ጋር ባሳልፍ ደስ ይለኝ ነበር ግን አጠገቧ ስሆን የማወራው ስለሚጠፋኝ ከዚ በላይ መቆየት አልቻልኩም...

ዛሬ በጣም ደስተኛ ሆኛለሁ ቤት ውስጥ ባይናገሩም የኔን ደስታ ማየት እንዳስደሰታቸው ግልፅ ነው አሁን ቤት ውስጥ የቀረነው አራት ልጆች ብቻ ነን ኑራ አግብታ ከቤት ከወጣች አመት አልፎታል... ምሽቱን በሙሉ የማስበው ሀያት እንዴት አቡበከር ልታውቀው እንደቻለች ሊገባኝ አልቻለም ያኔ መድረሳ ስልኳን ሊቀበልልኝ የነበረ ጊዜም ቢሆን ስሟን አልነገራትም ቢነግራት እንኳ ልታስታውሰው አትልችም የሆነ የተለየ ነገር እንዳለ ለማንም ግልፅ ነው ግን ምን እንደሆነ ማወቅ አልቻልኩም ስለዚህ ነገ ሀዩን መጠየቅ እንዳለብኝ አስቤ በጊዜ ተኛሁ....

ጠዋት ወደ ክላስ ለመሄድ እየተዘጋጀሁ ሳለ ስልኬ ጠራ አቡበከር ነበር ከአቡኪ ጋር ካወራን ቆይተናል አነሳሁትና ሰላምታ አቀረብኩለት ሰላምታዬን ከመለሰልኝ ቡሀላ ሰሞኑን አውርተን አናውቅም የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ አለኝ? እኔም ስለ ሀያት መንገር ስላልፈለግኩ አረ የለም ለምን ጠየቅከኝ አይ ከደወልክ ስለቆየህ ብዬ ነው ቤተሰብ ሁሉ ሰላም ናቸው አይደል አዎ አልሀምዱሊላህ ደህና ናቸው አንተ ጋርስ ቤተሰብ ሁሉ ደህና ናቸው "አዎ ደህና ናቸው በቃ ደህና ዋል በቅርቡ እንገናኛለን ብሎኝ ስልኩን ዘጋው...

እኔ እወድሻለሁ ልክ እንደ ድርሰቴ እንደ ሰውነቴ:
ልክ እንደ አቦጊዳ ልክ እንደ ቃላቴ:
ሀሳብ እንደሞላው እንደ ልብ ምቴ።

እኔ እወድሻለሁ ልክ እንደ ሀረጌ:
ልክ እንደ ስንኜ ልክ እንደ ማረጌ:
እኔ እወድሻለሁ ልክ እንደ ልቦለድ:
አስቦ አሰላስሎ ግጥም እንደመውለድ።

እኔ እወድሻለሁ ቤት እንደመምታት:
ሀያ መፅሀፎች ፃፍኩ እንደማለት:
ደራሲ ነህ ተብሎ እንደመጠራት:
እኔ እወድሻለሁ ለእናት እንደመግጠም:
ዶ/ር አብይ አንገት ልክ እንደመጠምጠም።

ይቀጥላል..........

@YEFKIR_LEZA
@YEFKIR_LEZA
80 viewsAbdu Emre (አብዱ ኤምሬ), 19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:59:32 #ሀያትና_እና_የአይን_ፍቅር
#ክፍል_አስራሁለት


አብዱ ኤምሬ

የዩኒቨርሲቲ ኢንትራንስ ፈተናዬን በጥሩ ውጤት አልፌ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢኮኖሚ ትምህርት ተመድቤለሁ ቤተሰቦቼም ሆነ ጓደኞቼ በጣም ተደስተዋል ይበልጥ እኔም ደስተኛ ሆኛለሁ ምክንያቱም ከቤተሰቦቼ እና ከለመድኩት አከባቢ ማህበረሰብ እና አኗኗር መራቅ ስለማልፈልግ ይሄ ለኔ ጥሩ እድል ነው...

ዛሬ የዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ቀኔ ነው በጊዜ ወደ ክፍል ገብቼ ከክፍሉ መሀል ባለ ወንበር ላይ ተቀምጬ የእለቱን ትምህርት እየተጠባበቅኩ ነው ሁሉም ተማሪዎች ወደ ክፍል መግባት ጀምረዋል እኔም በር በሩን እያየሁ በሀሳብ ስምጫለሁ በድንገት ሳላስበው ሳልገምተው ይሆናል ብዬ የማላስበው ነገር ተፈጠረ አንድ ሰው ወደ ክፍሉ እየገባ ነበር አይኔን ማመን አልቻልኩም የእውነት ሀያት ነች እንዴት ሊሆንስ ይችላል ይሄ አጋጣሚ ብቻ አይደለም የአላህ ተአምርም ነው..

ሀዩ ወደ ክፍል ገባች ሳላስበው ደስታ እና ሀዘን የተቀላቀለ እንባ ከአይኔ ይፈስ ጀመር አጠገቧ ሄጄ ባቅፋት እና የልቤን ሁሉ አውጥቼ ብነግራት ምን ያህል ደስ ባለኝ ነበር ግን እሷን ሳያት አይደለም መናገር የማደርገውን እንኳን አላውቅም ከዛም ሀዩ ከክፍሉ ፊት ለፊት ባለው ወንበር ሄዳ ተቀመጠች በእርግጥ በራሴ ተናድጃለሁ ምን አለ ፊት ተቀምጬ በነበረ አይኔን ከሀዩ ላይ መንቀል አልቻልኩም መቼም አያታለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር በዛ ላይ ካደረገችው ጥቁር ሂጃብ ጋር በፊት ከነበራት ውበት በላይ በጣም አምሮበታል ምን አልባት ፈጣሪዬ ያን ሁሉ ስቃይ እንዳሳልፍ እና አንድ አመት እንድደግም ያደረገው ለዛሬዋ ቀን ይሆናል.... ዛሬ ትምህርት ስላልነበር ትውውቅ ከተደረገ ቡሀላ ሁላችንም ከክፍል ወጣን ሀዩ ብቻዋን ነበር እየሄደች የነበረው ሲመስለኝ የምታውቀው ሰው የለም...

ሄጄ ከአጠገቧ ለመሆን እና በዚህ አጋጣሚ ጓደኛዋ መሆን እንዳለብኝ ወስኜ ወደ ሀዩ ጋር ሄድኩ ሀያት ብዬ ጠራሆት በቀስታ አቤት አለች ዞር ብላ... የእኔን መልስ ሳትጠብቅ ቀጥላ ከዚህ በፊት አውቅሀለሁ ልበል አለች "አዎ ሰሚር እባላለሁ አንድ መድረሳ ተምረናል አልኳት" አዎ አሁን አስታዋስኩህ "የአቡኪ ጓደኛ ነህ አይደል?" በድንጋጤ ቀጥ ብዬ ቀረሁ አቡኪ ነው ያለችው ግራ ተጋባሁ ደግሞ አቡኪን የት አውቃው ይሆን....

በነገርሽ መሀል አትስጊ ግድ የለም:
ዶሮ ጮኸ አልጮኸ መንጋቱ አይቀርም:
ይሄው ነው በእጅ ያሳደጉት ጅብ አጉራሽ እጁን ቢነክስ መልሶ:
ዘመኑ ይሆናል ወላጁን ሰውቶ ተሹሞ የሚኖር መንጎችን ገርስሶ:


ይሁና ከሆነ በመገርሰስ መሀል ራስ ሆኖ ከኖረ:
መስማቱን ዘንግቶ ወራጅ አለ እያሉት ዘግቶ ከበረረ:
ለምን እንዳትይ አትስጊ ግዴለም:
ዶሮ ጮኸ አልጮኸም መንጋቱ አይቀርም።

ይቀጥላል....

@YEFKIR_LEZA
@YEFKIR_LEZA
229 viewsAbdu Emre (አብዱ ኤምሬ), 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 23:33:33 #ሀያትና_እና_የአይን_ፍቅር
#ክፍል_አስራአንድ

አብዱ ኤምሬ


ዛሬ የዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ቀን ትምህርቴን ለመከታተል በዩኒቨርሲቲው ክፍል ውስጥ መሀል ላይ ተቀምጩ ሳለሁ በሀሳብ ያለፈውን ማስታወስ ጀመርኩ ያ ሁሉ ነገር መከራ እና ደስታ እንደዚህ በፍጥነት ማለፉ በጣም ገርሞኛል "ከሶስት አመታት በፊት ከወንድሜ ሙሀመድ ሰርግ ቡሀላ ራሴ ላይ የነበረው ጭንቀት ናፍቆት ድብርት እየጨመረ ሄደ ይባስ ብሎ ሰውነቴ ከቀን ወደ ቀን እየቀነሰ እና ነገሮችን በራሴ የማድረግ ጉልበት እንኳን አጣሁ ሆስፒታል ለሆስፒታል ብዞዞርም ምንም መፍትሔ ሊገኝ አልቻለም ቤተሰቦቼ ብዙ ገንዘብና ጊዜቸውን ቢያጠፉም ህመሜ እየባሰ እንጂ ልድን አልቻልኩም በየሆስፒታሉ የሚሰጡት መልስ የተለያየ ነበር ሀኪሞቹ እንኳን ሳይቀር በህመሜ ግራ ተጋብተዋል የኔ በሽታዬ ሀዩ ነበች መድሀኒቴ ልትሆን የምትችለው እሷ ብቻ እንደሆነች የሚያውቅ የለም...

ቤተሰቦቼ ሀኪም ቤት እየቀያየሩ ቢያሳክሙኝም ምንም ለውጥ ሊያገኙ ስላልቻሉ ወደ ቁርዐን ቤት ወስደውኝ ቁርዐን ይነበበልኝ ጀመር ከዛን ጊዜ ጀምሮ የውስጤ ህመም እና ጉዳት መፈወስ ጀመረ ቀን በቀን ኡስታዙ እየመጡ የተወሰነ የቁርዐን ክፍል ያነቡልኝ ነበር በእውነቱ ሀያ አራት ሰአት ሙሉ ባዳምጥም ደስተኛ ነኝ...

ቁርዐን ይነበበልኝ ከጀመረ ቡሀላ ሙሉ ለሙሉ ማገገም ቻልኩ ነገር ግን አሁንም የቤተሰቦቼ ጊዜ እና ገንዘብ በኔ ምክንያት መባከኑ ጭንቀት ፈጥሮብኛል በተጨማሪ በህመም ምክንያት ትምህርት በማቋቅኳረጤ ቤት ውስጥ ስለመውል እሱም አንድ ጭንቀት ነው በእርግጥ አቡኪ በእረፍት ጊዜው እኔ ጋር እየመጣ ያሳልፋል ያጫውተኛል ሀሳቤን እና ጭንቀቴን ከሱ ውጭ የምነግረውም ሰው የለም አቡኪ ሀዩን እያፈላለገልኝ ቢሆንም እስካሁን ሊያገኛት አልቻለም ሰዎች አፍቅረው ካለዩት በቀር በፍቅር ይሄን ያህል መጎዳት ቀልድ አድርገው ሊያዩትና ሊመስላቸው ይችላል እኔም በአንድ ወቅት እንደዚህ ነበር የማስበውና...

የአንደኛ ሴሚስተር ውጤቴ የተሻለ የነበረ ቢሆንም አንድ አመት ለመድገም ተገድጃለሁ አቡኪ አሁን ላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነው ከእሱ ጋር ብማር ለእኔ ጥሩ ይሆን ነበር ቢሆንም ግን እረፍት ሰአት እና ምሳ ሰአት አብረን ነው የምናሳልፈው በህይወቴ አንድ ልረሳው የምፈልገውና ባላስታውስ ደስ የሚለኝ ነገር ቢኖር ሀያት ነበረች ነገር ግን ልረሳት በሞከርኩ ቁጥር ፍቅሬ ናፍቆቴ እየጨመረ እና እየባሰ ነው...

ሀዩን ብናፍቃት እና ባስባትም አሁን ላይ ከአጠገቤ አለመኖሮ ላያት አለመቻሌ ለኔ ከባድ ህመም ነው አንድ የምፅናናበት ነገር ቢኖር አንድ ቀን ምሽት ከሀዩ ጋር ስጋባ ያየሁት ህልም ነው እሱን ባሰብኩ ቁጥር ተስፋዬ እና ምኞቴ ይጨምራል ምን አልባት ሀዩን በህልም አለም ከማግባት ውጪ በእውኑ አለም ከሷ ጋር የመሆንና እሷን የማግባት ተስፋ ያለኝ አይመስልም...

ገለጥ ሲልልኝ ድርብርቡ አፈና:
ጨለማው ተገፎ ሽኩቻ ለትግል
እንቅልፍ ሲነሳ በሀገሩ ለፍፎ
ምንም አትበይ ዛሬ ቃላት አጥተሽ
አፍሽ ቢቀየድም አትስጊ ግዴለም:
ዶሮ ጮኸ አልጮኸ መንጋቱ አይቀርም።

እንደነቃሁ ገና ሲነጋ ልነግርሽ:
ከንፈሬን ላልሼ ቃላት ፈልግና:
ሳስብ እፈራለው ሚስጥር እንዳይሾልከኝ ቃል እንዳላዛባ ሳላስብ ሆነና:
ምን አልባት በነገርሽ መሀል ሌላን:
ብተነፍስ ከመሀል ቆይቼ:
ቃል ግቢልኝ! አዝልቀሽ ላትሰጪኝ ላሳደኳቸው ነፍስ ወስደሽ ለጅቦቼ።

ይቀጥላል.........

@YEFKIR_LEZA
@YEFKIR_LEZA
450 viewsAbdu Emre, 20:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 23:14:39 #ሀያትና_እና_የአይን_ፍቅር

#ምዕራፍ_ሁለት_ነገ_ይጀምራል።
217 viewsAbdu Emre, edited  20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 21:25:26 #ኢድ_ሙባረክ
389 viewsAbdu Emre, 18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:43:48 #ሀያትና_የአይን_ፍቅር
#ክፍል_አስር

አብዱ ኤምሬ


በህይወቴ እንደዚህ ያዘንኩበት እንዲሁም እንደዚህ አዝናለሁ ብዬ የሰብኩት ቀን የለም ቤት እንዴት እንደመጣሁ እና እንደደረስኩ አላውቅም በእንባ ብዛት የአይኔ ቅላት በርበሬ መስሎል ቤት ከገባሁ ቡሀላ ቀጥታ ወደ መኝታ ክፍል ነበር የገባሁት እንባዬን አሁንም መቆጣጠር አልቻልኩም በሀሳቤ ላይ ብዙ ነገሮች ይመላለሳሉ የመኖሬን ትርጉም ያጣሁት መስሎ ታየኝ ራሴን ለማጥፋት ጫፍ ላይ ደርሻለሁ ግን ቤተሰቦቼስ ወንድሜ ሙሀመድ ሰርጉ ለቅሶ ሊሆን ነው ሀዩን ድጋሚ ባገኛትስ እነዚህ ሀሳቦች ስህተት ከመስራት ጠበቁኝ ቢያንስ በኔ ሀዘን ምክንያት የወንድሜን ደስታ ማበላሸት እንደሌለብኝ አውቃለሁ....

ቀናት አልፈው ዛሬ የሰርጉ ዋዜማ ላይ ደርሰናል ከሀገር ቤት የመጡት ዘመዶች ሚዜዎቹ ቤት ውስጥ ያለው ወከባ ልዩ ነው ሁሉም ላይ የሚታየው የደስታ ስሜት ልዩ ነው ጭፈራው ደርቷል በአባት እና እናቴ ፊት ላይ የሚታየውን ደስታ በህይወቴ አይቼው የማላውቅው ነበር። ሁሉም የለሊቱን ግማሽ በሙሉ በጭፈራ እና በወከባ ካሳለፈ ቡሀላ ሁሉም ቦታ ይዞ ተኝቶል። ቤታችንን ላየ ሀኪም ቤት ነበር የሚመስለው...

እሁድ ሁላችንም በጊዜ ተነስተናል እኔም ሻውር ወስጄላው ሙሽራው እና ሙዜዎች ዝግጅታቸውን ከጨረሱ ቡሀላ ስድስት ተኩል ላይ ወደ ሙሽራዋን ለማምጣት ወደ ቤቷ ሄድን እዛም ያለው ድባብ በጣም ደስ ይላል ቀጥሎ ሙሽራዋን ይዘን ወደ ሰርጉ ዝግጅቱ ቦታ ሄድን አዳራሽ ውስጥ ያለው ነገር ልዩ ነው ሁሉም ሰው ቦታውን ይዞል ሙሽራዎቹ ሲገቡ አዳራሹን በእልልታ አደመቁት ሰርጉን የሚያደምቁት የመንዙማ ጀመዐዎችም የሙሽሮቹ ማግባት ባየከ ጊዜ መንዙማ ማለት ጀምረዋል። በውስጤ የማስበው ግን ለራሴ ይሆናል ያልኩት ለወንድሜ ይሆን እንዴ ግራ ገብቶኛል...

በሚያምር መንገድ የሰርጉ ዝግጅት ካለቀ እና ሸራተን ፎቷ ከተነሱ ቡሀላ ወንድሜ ወደ ተከራየው ቤት አድርሰን ተመለስን..

ሰርጉ ካለፈ ቀናት ተቆጥረዋል ቤት ውስጥ የመጡት እንግዶች ሁሉ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል አሁን ሰርጉም መልሱ ሁሉ ነገር አልቋል ተጠናቋል" እኔስ ምን እሆን?"...


ልነግርሽ ያልኩ ለት አብሮ አደግ ጓደኛ ድፍረት ቢሰጠኝ:
ወደኋላ መጣው ወዳንቺ ሲገፉኝ:
ምን እድልሽ ነግረው ቃላትን ከሽነው:
ካጠገብሽ ስደርስ አንዱንም አላውቀው:
ልነግርሽ ያልኩለት
አፌ ተንቀጥቅጦ ላብ ገላዬን ጠምቆ:
ልቤ ግራ ቀኙ ለሁለት ተሰንጥቆ:


ሰው መክሮኝ ነበር አይዞህ ድፈር ብሎ:
ፍቅርሽ ባይነግስብኝ እንዳይሆነ ጥሎ:
ልነግርሽ ያልኩለት ዱኣ አድርጌ ለአምላኬ:
በእንባ ገርጥቶብኝ የልጅነት መልኬ:
እጅግ አይሎብኝ ፍቅር ያለ ልኬ:
አላህ ቢረዳኝ ለመንኩ ተንበርክኬ።

ፈርቼ አላውቅም ያኔ እንደፈራሁት:
ላንቺ ያለኝን ፍቅር ልነግርሽ ያልኩለት።

ይቀጥላል...

@YEFKIRLEZA
@YEFKIRLEZA
525 viewsAbdu Emre, 18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:59:36 #ሀያትና_የአይን_ፍቅር
#ክፍል_ዘጠኝ

አብዱ ኤምሬ


መድረሳ ብገባም ዛሬም አብኪ አልመጣም ሲመስለኝ የሀዩን ስልክ ለመቀበል ብቻ ነበር የመጣው የመቀጠል ፍላጎት ያለው አይመስለኝም... ከመድረሳ ከወጣን ቡሀላ እንደተለመደው ሀዩን ብጠብቃትም ዛሬም አልመጣችም ነበር... በእውነቱ ዛሬ ስለቀረች ምንም አልተሰማኝም ምክንያቱም ዛሬ በቀረች ብዬ ሳስብ ነበር በመቅረቷ ደስ ብሎኛል ግን ሁለት ቀን የቀረችው ምን አጋጥሞት ይሆን የሚለው ጭንቀት እና ፍርሀት ግን አሁንም አለለቀኝም...

ሰርጉ የቀረው አንድ ሳምንት ብቻ ነው ቀኑ በቀረበ ቁጥር ቤታችን ውስጥ ያለው ዝግጅትም በዛው ልክ ይጨምራል። አብዛኛው ጊዜዬን የማሳልፈው ቴሌግራም ላይ ነው ምክንያቱም ቴሌግራም ላይ የሚለቀቁትን ሀይማኖታዊ ሆና የፍቅር ታሪኮችን ማንበቤ ራሴ ላይ ያለውን ጭንቀት እንድረሳ ያደርገኛል በእውነቱ ሌላ የማማክረው ሰው ወይም ጓደኛ ስለሌለኝ ቴሌግራም ላይ መዋሌ አያስደንቅም ቤተሰቦቼ ብዙ ጊዜ ጎደኛ እንድይዝ እና ውጪ ወጥቼ እንድዝናና ቢነግሩኝም ብዙም ግድ የሚሰጠኝ ነገር አይደለም...

ሰኞ ከት/ቤት መልስ ቡሀላ መድረሳ ብገባም ዛሬ ሀዩ አልመጣችም ዛሬ መቅረቷ ሀሳቤን ጭንቀቴ እና ፍርሀቴን ይበልጥ ጨምሮታል ነገ ባትመጣስ ስለዚህ ካልመጣች ደብዳቤ ልፅፍና ለኢክራም ልልክላት ወስኜ መፃፍ ጀመርኩ ከብዙ መቸክቸክ እና ወረቀት መቅደድ ቡሀላ ይህን ፃፍኩ ።

ይድረስ ለምወድሽ የልቤ ውስጥ ሸራ ደጋግሞ ለሳለሽ:
ፍቅርሽ በልቤ ላይ የበላይ ላረገሽ:
የሀሳብ ጥምጣም ክር ጎንጉኖ ላበጀሽ:
ውብ እኔነቴ ከውበት ምድጃ ስር ከስሎ ማንነቴ:
አድርጎ ሾሞሻል ንግስቴ የኔነቴ:
ሆኖብኝ ከልቤ ባንዳ አጋፋሪ:
እኔነቴ ከስሟል ጀግናው ፊትአውራሪ:

መውደዴን ልነግርሽ በልቤ አስብና:
አላምነውም ልቤን ያንቺ ሆኖልና
ዳግም በሌላ ቀን ወዳንቺ ሳማትር:
ሂድ ንገር ይለኛል ሆላ ሊያስወረውር የፍቅርሽን በትር:
አመኔታ አጥቼ እኔው ከራሴጋ ልቅረፅሽ ልሳልሽ ቀኔ እስከሚነጋ።

በዚህ ደብዳቤ ላይ ልነግርሽ ያሰብኩት
አስቤ የፃፍኩት ፅፌ የሰረዝኩት:
ሰርዤ የላኩት ስርዝ ድልዝ ሆኖ አልነበብ ካለሽ ሳልሰርዘው በፊት:
ሀሳቡ መልዕክቱ - ምን ይላል መሰለሽ?

መግቢያው መደምደሚያው ሀተታው በሙላ:
ሌላ አይናገርም ከናፈቅሽኝ እና ካፈቀርኩሽ ሌላ።

ከአንቺው አፍቃሪ ሰሚር

ዛሬም ኢክራም ብቻዋን ነበር ከመድረሳ የወጣችው ደብዳቤውን ለኢክራም ከመስጠት ሌላ አማራጭ ስለሌለኝ ኢክራም ብዬ ጠራሆት አልፋኝ ልትሄድ ስትል "አቤት" አለች ፈገግ ብላ ነጭ የሆኑት ጥርሶቾ ልብን የይዛሉ ሀያትን ፈልጌ ነበር በሰላም ነው እንዴ ጠፋች? አልኳት አንገቴን አቀርቅሬ "እ ሀያትን ፈልገህ ነው እንዴ እነሱ እኳ አዲስ ቤት ሰርተው ቤት ለቀዋል ስለዚህ እዚህ መድረሳ አትመጣም" አለችኝ በድንጋጤ ከቅፅበት ፊት በላብ ተጠመቀ የት ነው የሄደችው አልኩ ካቀረቀርኩበት ቀና ብዬ "ደብረዘይት ነው የሄደችው " ደብረዘይት ለማንኛውም ይሄን ደብዳቤ ካገኘሻት ስጪልኝ ብዬ ሰጥቼት ሄድኩ የሚሰማኝን ስሜት አላውቅም እንባዬ ዱብ ዱብ እያለ ነው...

ልነግርሽ ያልኩለት አላየሽም እንጂ ብታይው ደስ ባለኝ:
ልነግርሽ ያልኩለት እንዴት እንደሆንኩኝ:
እንቅልፍ አልተኛሁኝ:
አንዳች አልቀመስኩኝ:
ስላንቺ ነው እንጂ ሌላም አላሰብኩኝ:
ለሊቱ ረዝሞብኝ:
ንጋት እርቆብኝ:
እንዲያ ስገላበጥ ቅብዝብዝ ሲያረገኝ:
አላየሽም እንጂ ብታይ ደስ ባለኝ።

ይቀጥላል...

@YEFKIR_LEZA
@YEFKIR_LEZA
685 viewsAbdu Emre, edited  18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:04:30 ለፈገግታ ከነስሩዲን ዐለም

ድሮ ድሮ ሁጃ ነስሩዲን ከቱርክ ወደ ግሪክ በአህያቸው ተጭነው ይመላለሱ ነበር

ታድያ ድንበር ጠባቂዎች ባገኟቸው ቁጥር የኮንትሮባንድ ፍተሻ ቢያደርጉባቸውም ምንም ሊያገኙ አልቻሉም

አመታት አለፉ እና ነስሩዲንም አሉ የተባሉ ባለሀብት ሆኑ በአጋጣሚ ድንበር ላይ ይፈትሻቸው የነበረው ጠባቂ በዚህ ድሎቱ ያገኛቸውና እንዴት ሀብት እንዳካበቱ ይጠይቃቸዋል

ነስሩዲንም መለሱለት "" ወዳጄ የአህያ ኮንትሮባንድ እጅጉን ያዋጣል ....።
አህያዎችን ነበር የሚቸበችቡት

@YEFKIR_LEZA
@YEFKIR_LEZA
294 viewsAbdu Emre, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 22:43:17 ለፈገግታ
                  
          በዐረቡ ምድር  ውስጥ የኖረ  ወንዳ ገረድ  የውበት ደላላ ነው። ከተለያዩ መንደሮች  ወደርሱ የሚጎርፉ ትዳር ፈላጊዎች ••እባክህን ቆንጂቷን ልጃገረድ ጠቁመን ••እያሉ ይዋደቁለታል።
   በአንድ ወቅት በዚያው አካባቢ የሚኖር መንደርተኛ   መልኳ እማይከፋ  ጸባየ ሠናይ ሴት እንዲጠቁመው ይጠይቀውና  ሳያገኝለት ይቀራል።
           በሌላ ቀን ተመልሶ የመጣውን ይህንኑ ሠውዬ   በጥቂት ቀናት  ሸጋ እንስት እንደሚድረው ቃል ገብቶለት ተለያዪ።•• በዚህኛው ዙር ምን የመሰለች ኮረዳ ካልዳርኩልህ   ይሄን ዠርጋጋ ፂሜን በራስህ እጅ ትላጨዋለህ••    ብሎት ነበር የሸኘው እርግጠኛ እንዲሆንለት።
        ቃል እንደገባው ከአንዲት የዐረብ ሸጊት አገናኝቶት ትዳሩን አሰመረለት።ሴቲቷ አበልሁር ካጋነነላት በላይ  መልከኛ እና ጸባይተኛ ነበረች።
        ነገር ወዲህ ነው....  በጫጉላ ሽርሽራቸው ሠሞን በአንደኛው የሙሽሮቹ  ሌሊት ላይ  የአዲሱ ጎጆ በር ተንኳኳ። ከጣፈጠ ወግ ያደፋረሳቸውን የበር ጩኸት የሰሙት ሙሽሮች ቆጣ ባለ  ድምጽ ••ማነው ደሞ በዚ ሌሊት ሚያንኳኳ ያ አሏህ?...እህ ማነው•• ብለው ካሉበት ሳይነሱ ምላሽ ጠበቁ።
        ከበሩ ኋላ ያለ አንድ ድምጽ  ••እእ ይቅርታ ሰይዲ እኔ  አበል ሁር   ነኝ  የሙሽሪት ደላላ...ይኸው እርስዎም እንዳይቸገሩ  ጺም የሚላጨውን ኻዲም እና ምላጬን ይዤ መጥቻለሁ•• ሲላቸው።
             ሙሽሮቹ  እይታቸውን ተለዋውጠው ሳቃቸውን እየለቀቁት  በባልየው ምላሽ  አበል ሁርን አሰናበቱት።
      يا أبا الحر  وفر الله لحيتك   ،ارجع إلى منزلتك بسلام
ውይ አበል ሁር አንተ ነህ እንዴ!  በል እንግዲህ አሏህ ፂምህን ያብዛልህ፡ያፋፋልህ። ወደ ቤትህ ተመለስ አሏህ በሰላም ይመልስህ።
       ሚስት በተራዋ... ••ውዴ ግን እንደኪራይ ቤት በደላላ ነው እንዴ ያገኘከኝ??••....የሙሽሪት የጥያቄ ናዳዎች ከነኩርፊያ ለምቦጮቻቸው ይቀጥላሉ.......

@YEFKIR_LEZA
@YEFKIR_LEZA
316 viewsAbdu Emre, 19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 22:01:26 #ሀያትና_የአይን_ፍቅር
#ክፍል_ስምንት

አብዱ ኤምሬ


"በእርግጥ ሙሀመድን ስወልድ የመጀመሪየሰ ልጄ ስለሆነ ብዙ ፈተና አሳልፌለሁ ቀጥሎ ቡሀላ ነቢል ኑራ አህመድ ሰሚርን ወለድኩኝ ሰብሪና ከተለወደች ቡሀላ በአባታችሁ እና በእኔ ለአራት አመት መሀል ግጭት ተፈጥሮ ነበር ግን ለአላህ ምስጋና ይገባውና አሁን ተፈቷል። እናንተን የመሰለ ልጆችን አፍርተናል አሁን ደግሞ ይህው እኔም ወግ ደርሶኝ ልጄን በወግ ማዕረግ ልድር ነው። በቃ ሂዱ ተኙ ደህና እደሩ" ብላ ንግግሮን አቋመች ከሰብሪና ውጪ ሁላችንም ተመስጠን እየሰማን ነበር ሰብሪና በተቀመጠችበት እንቅልፍ ወስዷታል ሰአቱን ሳየው በጣም ሄዷል 5:27 ይላል ሁላችንም ተነስተን በደስታ መንፈስ ወደ መኝታችን ሄደን ተኛን...

ጠዋት ስነሳ በጣም ረፍዷ ነበርና ወደ ት/ቤት አልሄድኩም በእርግጥ አውቄ ነበር የተኛሁ መስዬ ያረፈድኩት ቀኑ ሙሉ የመድረሳ ሰአት እስኪደርስ እና ለሀዩ የልቤን እስክናገር ቸኩያለሁ የማይደርስ የለምና የመድረሳ ሰአት ሲደርስ ሄድኩ የመውጫ ሰአቱ አልደርስ ብሎኛል ምን አለፋችሁ የቀን ያህል ነው የረዘመብኝ ምንም ትምህርቱን መከታታል አልቻልኩም ነበር... ከመድረሳ ቀደም ብዬ ወጥቼ ሀያትን መጠበቅ ጀመርኩ ግን እስካሁን አልወጣችም በመጨረሻ ኢክራም ስትወጣ አየሆት ኢክራምና ሀዩ አብረው ስለሚወጡ በጣም ደስ አለኝ ግን ሀዩ አብራት አልነበረችም ኢክራምም እንደሌላ ጊዜ ሀዩን ቆማ አልጠበቀችም ምን አልባት ትቆይ ይሆናል ብዬ ብጠብቃትም አልወጣችም ምክንያቱም ሀያት አልመጣችም ነበር። ሁሌ ለመናገር ስወስን እንደዚያ አይነት ነገር የሚያጋጥመኝ ለምን ይሆን ልቤ በጣም ተሰብሮል ነገም ልነግራት አልችልም ምክንያቱም ነገ አርብ ስለሆነ መድረሳ የለም መድረሳ ያለው ቅዳሜ ነው ምንም ቢሆን የመናገር ድፍረቱ አሁንም አለኝ ነገር ግን ባትመጣስ አሁንም ሰኞ ድረስ ልጠብቅ ነው...

አርብም ትምህርት መግባት ስለደበረኝ አልገባሁም ለጁመኣ ስግደት በጠዋት ገላዬን ታጥቤ የሰላት ሰአት ሲደርስ ወደ አንዋር መስጂድ ሄድኩ የዛሬው ኹጥባ (ስብከት) ስለ ረመዳን ፆም ነበር የረመዳን ወር የቀረው ወር ያህል ብቻ ነው ረመዳን ሁሉም ሙስሊሞች መምጣቱን የሚናፍቁት ወር ነው ከሰላት ቡሀላ ወደ ቤት ተመለስኩ.. ዛሬም ምሽቱ እማዬ እና አባዬ አድምቀውታል..

ዛሬ ቅዳሜ ነው ሰርጉ የቀረው አንድ ሳምንት ብቻ ነው ከማሜ ጋር ልብስ ለመግዛት ወደ ቦሌ አከባቢ ያሉ ልብስ ቤቶች ብንሄድም ዋጋቸው አይቀመስምና መርካቶ ሄደን ለማሜ አሪፍ ሱፍ አግኝተን ገዝተናል ለሚዜዎቹም የሚሆነውንም ተከራይተናል እኔ ሚዜ እንድሆን ቢጠይቀኝም ሰው በተሰበሰበበት ጎልቶ መታየት የማልወደው ነገር ነውና ድፍረቱም ስለሌለኝ ጥያቄውን አልተቀበልኩትም ከግማሽ ቀን መንከራተት ቡሀላ ወደ ቤት ተመለስን ...

እማ ዛሬ በጣም ደስተኛ ሆናለች "ምን ተገኝቷ ነው ይሄ ሁሉ ደስታ " አልኳት ፈገግ እያልኩ አጎቶችህ ሀሙስ ከገጠር እንመጣለን ብለውኛል ለዛ ነው የተደሰትኩት አለች በነገሩ ደስ ቢለኝም ከገጠር ድረስ ሰው ይጠራል ብዬ አላሰብኩም ነበር በዚህ አይነት ምንም ቢደገስ አይበቃም አልኩ በልቤ አሁንም ግን ሀሳቤ ሀዩ እና ሁዩ ጋር ነው በፍቅሮ መስከሬን እስክነግራት ቸኩያለሁ...

ልነግርሽ ያልኩ ለት መውደዴን አውጥቼ:
በሰው ተገፍቼ:
ብታይ ተርበትብቼ:
ድፍረቴን አጥቼ:
በቁም ሳለው ሞቼ:
ሳፈቅርሽ ፈርቼ:
ልቀርበሽ መጥቼ:
ሄዳለው ሸሽቼ:

ልነግርሽ ያልኩለት ፀሀይ ወጥታ ገባች:
ጎሁም ቀደደ ጨረቃም አለፈች:
በጋውም ነጎደ ለክረምት ለቆ:
ልነግርሽ ያልኩለት ድፍረት ከኔ ርቆ።

ይቀጥላል......

@YEFKIR_LEZA
@YEFKIR_LEZA
594 viewsAbdu Emre, edited  19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ