Get Mystery Box with random crypto!

ታሪካዊት ኢትዮጵያ [ Historical Ethiopia ]

የቴሌግራም ቻናል አርማ historical_ethiopia — ታሪካዊት ኢትዮጵያ [ Historical Ethiopia ]
የቴሌግራም ቻናል አርማ historical_ethiopia — ታሪካዊት ኢትዮጵያ [ Historical Ethiopia ]
የሰርጥ አድራሻ: @historical_ethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.25K
የሰርጥ መግለጫ

ስለ ሀገር ብቻ ስለ ኢትዮጵያ
በዚች ድንቅ ሀገር እጅግ ብዙ ታሪክ ባላት
በተለይም በቀደምት ኢትዮጵያን የተፃፉ
የተለያዩ ታሪኮችን ለማግኘት
YOUTUBE : https://youtube.com/@Historical_Ethiopia
✅ጥያቄ ካለዎት❓ 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion
✅ለቻናሉ መስራች አስተያየትዎን ለመስጠት @Abel_balehager_bot

Ratings & Reviews

1.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

3


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-20 19:41:42
"…የመቻቻል ሰባኪው፣ ቅን፣ ትሁት፣ ደርባባ፣ ኢትዮጵያዊ የአዛውንት፣ የሽማግሌነት ማሳያ የተከበሩ ዶ/ር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር ኢድሪስ እንኳን አደረስዎት…!!

"…አክባሪ ልጅዎ ኩሩ ኢትዮጵያዊው #አቤል_ባለሀገር ነኝ። ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ተመኘሁ።

"•…ዒድ ሙባረክ…!!

ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ !!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

YOUTUBE : https://youtube.com/@Historical_Ethiopia
ጥያቄ ካለዎት @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia
352 viewsየቃየል ታናሽ ወንድም, 16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:33:13
ለዘመናት ከፍተኛ የንግድ ማዕከል ሆና ስትኖር ከመሃል አገር፣ ከአፍሪካ ቀንድ እና ከአረብ አገራት ጋር በንግድ መንገዶች ስትገናኝ ከቀሪው አለም ጋር ደግሞ በቀይ ባህር ወደቦች አማካኝነት ትገናኝ ነበር። የሐረር ጀጎል ግንብ ከ1998 ጀምሮ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ይገኛል። በእስልምና ሃይማኖት "4ኛዋ የተቀደሰች ቦታ" ተብላም ስትታወቅ 82 መስጊዶች፤ አንዳንዶቹ ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ…
302 viewsየቃየል ታናሽ ወንድም, 16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:31:52 ለዘመናት ከፍተኛ የንግድ ማዕከል ሆና ስትኖር ከመሃል
አገር፣ ከአፍሪካ ቀንድ እና ከአረብ አገራት ጋር በንግድ
መንገዶች ስትገናኝ ከቀሪው አለም ጋር ደግሞ በቀይ ባህር
ወደቦች አማካኝነት ትገናኝ ነበር።
የሐረር ጀጎል ግንብ ከ1998 ጀምሮ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ
ዝርዝር ውስጥ ይገኛል። በእስልምና ሃይማኖት "4ኛዋ
የተቀደሰች ቦታ" ተብላም ስትታወቅ 82 መስጊዶች፤ አንዳንዶቹ
ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበሩ፤ እንዲሁም 102 የቀብር
ቦታዎች አሉዋት።
ሐረር በ1877
አርተር ራምቦ
. ዋግነር፣ ዘ ዲክሽነሪ ኦፍ ኢትዮጵያን ባዮግራፊ፣ ገጽ 1፣
ቮልዩም 1፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ጥናት
ኢንስቲትዩት፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ።27 መድሃኒያለምና
ሙስሊሟ ሀረር እኛ እርስበእርስ ስንናከስ ወይናደጋማዋ ሐረር
እርስ በእርሱ ከሚበላላው ጅብ ጋር ሳይቀር ተግባብቶ
የሚኖርባት ከተማ ናት፡፡
ሐረር ከአዲስ አበባ ደቡብ ምስራቅ በአምስት መቶ ኪሎሜትር
ርቀት ላይ የምትገኝ የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተማ ናት። በዘመኑ
የአስተዳደር መዋቅር የሃረሪ ክልል ዋና ከተማ ናት። በ1,885
ሜትር ከፍታ ላይ፣ የወይና ደጋ የአይር ጠባይ በተላበሰ ቦታ ላይ
አርፋለች።  በ1987 ዓመተ ምህረቱ የህዝብ ቆጠራ መሰረት
ሐረር 76,378 ሕዝብ ይኖርባታል።
ሐረር ለዘመናት ከፍተኛ የንግድ ማዕከል ሆና ስትኖር ከመሃል
አገር፣ ከአፍሪካ ቀንድ እና ከአረብ አገራት ጋር በንግድ
መንገዶች ስትገናኝ ከቀሪው አለም ጋር ደግሞ በቀይ ባህር
ወደቦች አማካኝነት ትገናኝ ነበር። የሐረር ጀጎል ግንብ ከ1998
ጀምሮ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ይገኛል።
በእስልምና ሃይማኖት "4ኛዋ የተቀደሰች ቦታ" ተብላም
ስትታወቅ 82 መስጊዶች፤ አንዳንዶቹ ከ10ኛው ክፍለ ዘመን
ጀምሮ የነበሩ፤ እንዲሁም 102 የቀብር ቦታዎች አሉዋት
ኣው-ባዲር፣ አው-ባድር፣ አባዲር፦ (ዑመር አርሪዳ) (በግምት
ወደ ፲፫ ኛው ክ/ዘ)፦ በ ፲፫ ኛው ክ/ዘመን ውስጥ የተፃፈውና
ስለ ሐረር ጥንታዊ አፈታሪካዊ ታሪክ የሚዘክረው 'ፋዝ መዲናት
ሐረር' የተባለው ያልታተመ መጽሐፍ እንደሚገልጸው አባድር
(ዑመር አርሪዳ) እጅግ ከተከበሩት የሐረር ሼኽዎች ውስጥ
አንዱና ዋንኛው ናቸው። በዚሁ መጽሓፍ አገላለጽ መሠረት፡
አባድር ከሌሎች በርካታ ሼኾች ጋር በመሆን ከሂጃዝ በ፮፻፩፪
ሂጅሪያ (1216 እ.ኤ.አ) ተነስተው ሐረር ከገቡ በኋላ
በአካባቢው የጎሣ እና ኃይማኖት መሪዎች ተመርጠው ዒማም
ሆኑ።
የሀረር ህዝብ ታሪክ ፣ ባህል እና ማንነት ከሀረር ከተማ ጋር
በእጅጉ የተቆራኘ ነው፡፡ ሀረሪዎች በረዥም ዘመን የስልጣኔ
ታሪካቸው ያፈሯቸው ተንቀሳቃሽ እና የማይንቀሳቀሱ እንዲሁም
የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ በርካታ ቁሳዊ እና መንፈሳዊ ቅርሶች
ባለቤት ናቸው፡፡ ከእነዚህ ቅርሶች መካከልም የከተማዋ ልዩ
መለያ ምልክት ከመሆንም አልፎ እ.ኤ.አ በ2006 በአለም
ቅርስነት የተመዘገበው የጀጎል ግንብ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡
በግንቡ ውስጥም ከ82 በላይ መስኪዶች እና በርከት ያሉ የሀረሪ
ባህላዊ ቤቶች ይገኛሉ፡፡
ሀረር ከፍተኛ የስልጣኔ እድገት ደረጃ ላይ በደረሰችበት
በ16ኛው ክፍለ ዘመንም በምስራቅ አፍሪካ የእስልምና
ሀይማኖት ትምህርት እና የንግድ ማዕከል ሆናም አገልግላለች፡፡
ይህም የበርካታ ታሪካዊ እና ባህላዊ ቅርሶች ባለቤት እንድትሆን
አድርጓታል፡፡ የጀጎል ግንብ የሀረሪ ህዝብ የኪነ ህንፃ ችሎታውን
የሚያስመሰክር የታሪክ እና የጥበብ መዘክር ነው፡፡ ይህ ግንብ
በ16ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ በአሚር ኑርአማካኝነት
እንደተገነባም ይነገራል፡፡ሐረር እንኳን ዛሬ ቀን ዘምኖ ትናንትናም
ቢሆን ስንቱ ባህር አቋርጦ የከተመባት፤ ስንቱ ቅጥሯ ገብቶ
ለትውልድ የተረፈ ትዝታ ያስቀመጠባት የውበትና የጥበብ
መዲና ናት፡፡ የኢትዮጵያ ኢስላማዊ ኪነ ህንጻና ባህል ማንምም
ሳይመስል፤ ሃይማኖታዊ መሰረቱን ሳይጥል የነገሰባት መዲና፤
ያው ጀጉልን መዞር ነው፡፡ በየቦታው መቆም፡፡ በየቦታው
ማየት….በየቦታው መደምም…ጀጉልን ገብተው ይኖሯታል እንጂ
አይጽፏትም፡፡
ጀጉልን ውስጥ ለውስጥ ከጀመርናት መቆሚያ የለውምና ከጊዜ
እየተሻማን በበራፍ በበራፍ እንለፍ
ሀረር ከቅርስነት ባሻገር እ.ኤ.አ በ2003/4 በሰላም ፣ በመቻቻል
፣ በመፈቃቀር እና በልማት ከተማነት አለም አቀፍ ሽልማት እና
እውቅናን አግኝታለች፡፡ ይህም የተለያየ እምነት ፣ ባህል እና
ቋንቋ ያላቸው ህዝቦች ለዘመናት በሰላም እና በፍቅር የኖሩባት
እና ዛሬም የሚኖሩባት ከተማ በመሆኗ የተቀዳጀችው ክብር እና
እውቅና ነው፡፡ ሀረር ዩኔስኮ ዕውቅናን የቸራት በዓለም ቅርስ ብቻ
አይደለም፡፡ ከኪነ ህንጻዎቿ ልቀት ባለፈ ህያው ሆኖ ዛሬም
እየኖረ ባለው ሰዋዊ እሴት ምርጥ ነሽ ብሏታል፡፡ ፈረስ መጋላ
ይሉታል ሀረሮች ከፊት ለፊቱ የአሚር አብዱላሂ አደራሽ አለ፡፡
ሀረር መድኃኒዓለም በር ላይ፡፡ ጀጉል በሀገራችን በርካታ
መስጂዶች የሚገኙባት ከተማ ናት፡፡ በግንብ የተከበበው ቅጥሯ
ውስጥ የሚገኘው የመድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ከተማዋ
ዩኔስኮ የተባለውን ዓለም አቀፋዊ ትኩረት ስባ የመቻቻልና
የሰላም ተምሳሌት የተባለ እውቅና እንድትቀበል አድርጓታል፡፡
በረዣዥም የመስጂድ ሚናራዎች የታጀበው የሀረር
መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን በ27 በድምቀት ይነግሳል፡፡
የጀጉል መንገዶች ከጁምአ ዕለት ድምቀት በተጨማሪ በተለየ
27 ነጠላ ለባሾች ከየአሉበት ወደ ቅጥሯ የሚገቡበት ሌላ
ትዕይንት ያስተናግዳሉ፡፡ ምዕተ ዓመት የተሻገረው ይህ ቤተ
ክርስቲያን ንጉሰ ነገስቱ አጼ ምኒሊክ ኢትዮጵያን በሚመሩበት
ራስ መኮንን የሀረርጌ ገዢ በነበሩበት ዘመን የታነጸ ነው፡፡ ያሰሩት
ራስ መኮንን ናቸው፡፡ ክቧ ቤተክርስቲያን ውብ ናት፡፡ ዛፎቿ ጥቂት
ናቸው ነገር ግን ከግቢዋ ስፋት አኳያ ጥሩ አድርገው
አጅበዋታል፡፡ ዛሬ ከሁሉም አቅጣጫ ሰው ወደ ጀጉል እያመራ
ነው፡፡ ሐረር ወይም ዱክ በር ከሚባለው በሗላ በተሽከርካሪ
ማለፍ አይቻልም፡፡ ይሄ አጋጣሚ ሌላ ትዕይንት ፈጥሯል፡፡ ነጠላ
ያጣፉ ጧፍ የያዙናና ሂጃብ የለበሱ መንገደኞች በጋራ እየተሳሳቁ
መንገዱን ሞልተውታል፡፡ እጣንና ጧፍ የዘረጉ ነዋየ ቅድሳት
የሚሸጡ መንገዱን ዳርና ዳር ይዘውታል፡፡ የኔ ቢጤዎች ስለ
መድሐኒያለም እያሉ ይለምናሉ፡፡ መላው የሐረር ህዝብ አቦ
እንወድሃለን! ሀገርን ለማጥፋት ለመበታተን ቀን ከሌት የሚተጋ
መንግስት መሳይ ጊዜ አንግሶት እየገዛን ቢሆንም አንተም
እንደኛው በቁምም በስጋም እየሞትክ ቢሆንም አብሽሩ እኛ
አንድ ሆነን ሽ የሆንን ኢትዮጵያውያንነን! የመጣብንን ሰይጣናዊ
የጥፋት ውሃ ከአምላክ ጋር አንድ ከሆን እናከሽፈዋለን!!!
"ኢትዮጵያ" ማለት መንፈስ ነው፣ እሱም "አንድነት" ማለት ነው፡፡
ኢትዮጵያ የፍቅር ሀገር የመቻቻል ምድር ለዘላለም ትንሩልን!!!!

#አቤል_ባለሀገር ነበርኩ ዒድ ሙባረክ

ምንጭ ፦የኢትዮጵያ ቅርሶች

ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ !!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

YOUTUBE : https://youtube.com/@Historical_Ethiopia
ጥያቄ ካለዎት @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia
255 viewsየቃየል ታናሽ ወንድም, 16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:08:19
“ፍቼ” በሲዳማ ባህል ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የቆየ የዘመን መለወጫ በአል ነው፡፡ በአሉ ከሁለት ሳምንት ላላነሰ ጊዜ በድምቀት የሚከበር ሲሆን አከባበሩም ቅደም ተከተላዊ ሂደትና በደረጃ እየሰፋ የሚሄድ የጋራ የአከባበር አድምታ ያለው ነው፡፡ ስለሆነም ፍቼ በቤተሰብ ወይም በጎረቤት ደረጃ ተሰባስቦ በማክበር የሚያበቃ ሳይሆን ከዚህም በሰፋ መልኩ በባህላዊ አደባባይ /ጉዱማሌ/ በጋራ በድምቀት የማክበር ሂደትን…
216 viewsየቃየል ታናሽ ወንድም, 16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:05:51 “ፍቼ” በሲዳማ ባህል ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የቆየ የዘመን
መለወጫ በአል ነው፡፡ በአሉ ከሁለት ሳምንት ላላነሰ ጊዜ በድምቀት
የሚከበር ሲሆን አከባበሩም ቅደም ተከተላዊ ሂደትና በደረጃ እየሰፋ
የሚሄድ የጋራ የአከባበር አድምታ ያለው ነው፡፡ ስለሆነም ፍቼ በቤተሰብ
ወይም በጎረቤት ደረጃ ተሰባስቦ በማክበር የሚያበቃ ሳይሆን ከዚህም
በሰፋ መልኩ በባህላዊ አደባባይ /ጉዱማሌ/ በጋራ በድምቀት የማክበር
ሂደትን ያካትታል፡፡ ለአከባበሩ እያንዳንዱ ቤተሰብ በቅድሚያ እንደ አቅሙ
ቅድመ ዝግጅት ያደርጋል፡፡ ከዚሁ አንጻር የቤቱ እመቤት ለበአሉ ቅቤ
ታጠራቅማለች ወተት በታጠነ ማለፊያ “ቁሹና” /የወተት እቃ/
ታከማቻለች የእንሰት ውጤት የሆነውን ቆጮ ለበአሉ በሚሆን መጠንና
ጥራት ከወዲሁ ታሰናዳለች፡፡
አባወራው በፍቼ ማግስት /በጫምበላላ/ እለት ለከብቱ የሚያበላውን
ቦሌ ያዘጋጃል፡፡ ልጃገረዶች ለበአሉ መዋቢያ ለእግሮቻቸውና ለእጆቻቸው
ጣቶች ቀለበት፣ ለፀጉራቸው መስሪያ “ሄቆ” /የተለያዩ ቀለማት ያሉት
የቱባ ክር/፣ ጨሌ፣ ለአንገታቸው ቡሪቻና ዶቃ የጌጥ አይነት ለጸጉራቸው
ማሸሚያ ግንባራቸው ላይ የሚያስሩትን በእራፊ ጨርቅ ላይ ደርድረው
የሚሰፉትን ኢልካ /አዝራር/ ወዘተ የመሳሰለውን ያስገዛሉ እግራቸውና
እጃቸው ላይ የሚቀቡትን እንሶስላ ያዘጋጃሉ፡፡
ፍቼ/ Fichchaa/
የፍቼ ዕለተ በዕለተ ቃዋዶ በአሉ መከበር የሚጀምረው ከአመሻሽ ጀምሮ
ነው፡፡ ለዚህም በቅቤ የራሰ “ቡሪሳሜ” ከቆጮ የተሰራ ባህላዊ ምግብ
“በሻፌታ” /ከሸክላ በተሰራ ባህላዊ ገበታ/ ቀርቦ በወተት በጋራ
የመመገብ ሥርዓት የሚካዳሄድ ሲሆን አመጋገቡ የሚጀምረው በአካባቢ
ከሚገኝ አንጋፋ ወይም ጪሜሳ /ብቁ አረጋዊ ቤት/ በመገኘት ገበታው
ከቀረበ በኋላ ለቡራኬው ሁሉም እጁን በገበታው ትይዩ በመዘርጋት “ፍቼ
ከዘመን ዘመን አድርሽን” በማለት አንጋፋው የሚሰነዝረውን ቡራኬ ቃል
በጋራ በማስተጋባት አመጋገቡ ይጀምራል፡፡ ለመመገቢያ በቅድሚያ
ለሁሉም በእሳት ሙቀት ተለብልቦ የለሰለሰ ኮባ ስለሚታደል አንጋፋው
በኮባው ከገበታው በመጨበጥ ከጀመረ በኋላ በጋራ የመመገቡ ሂደት
ይጀምራል፡፡ በፍቼ እለት በየቤቱ የሚቀርበው ገበታ ውስጥ ሥጋ
አይካተትም፡፡ የዚህ አይነተኛው ምክንያት ከብቱም በሰላም ከዘመን ዘመን
መሸጋገር ስላለበትና ሲዳማ ለከብት ከፍተኛ ግምት ያለው በመሆኑ ነው፡፡
ቀደም ሲል ታርዶ ሲበላ የተረፈ ሥጋ እቤት ውስጥ ካለ በእለቱ ሥጋው
ከቤት ውጪ እንያዲያድር ይደረጋል፡፡ አባወራ /የቤቱ ባለቤት /በፍቼ
እለት ከቤቱና ከቤተሰቡ ተለይቶ ሌላጋ አያድርም፡፡ በዚህ እለት በየደጁ
ከእርጥብ እንጨት “ሁሉቃ” የተሰኘ መሹለኪያ ተዘጋጅቶ አስቀድሞ
አባወራው በሁሉቃው ውስጥ ከሾለከ በኋላ ቤተሰቡንና ከብቱን ያሾልካል
ይህም በሰላም ከዘመን ዘመን የመሸጋገር ተምሳሌት ነው፡፡
የጨንበላላ /የፍቼ ማግስት/ አከባበር
“ጫንበላላ” በፍቼ ማግስት በእለተ ቃዋለንካ  የሚከበር ሲሆን የፍቼ
እለት በጋራ በተበላበት “ሻፌታ” /ባህላዊ ገበታ/ ውሃ ተሞልቶ ጠዋት
ላይ አባወራውና ቤተሰቡ በውሃው ፊታቸውን በማስነካት እና ከዚሁ ጋር
የቀረበውን ቅቤ አባወራው እየቆነጠረ የራሱን እና የቤተሰቡን አናት
በማስነካት ወደ አዲሱ ዘመን የመሸጋገር ተምሳሌት ይከናወናል፡፡
የ“ጨንበላላ” እለት መሬት የማረስ እንጨት የመስበር የመሳሰለውን
ተግባር ስለማይከናወን ለማገዶም ቢሆን አስፈላጊው እንጨት አስቀድሞ
ይዘጋጃል፡፡ በዕለቱ አባወራው ከብቶቹን ማለፊያ “ካሎ” /የግጦሽ
ሳር/ ውስጥ አሰማርቶ ለከብቱ ቦሌ ነስንሶ እያበላ ከብቱን አጥግቦ
ያውላል፡፡ በዚህ ዕለት ልጆች ተሰባስበው በየቤቱ በመሄድ “አይዴ
ጨምባላላ” እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ የቤቱ ባለቤቶች ምላሹን “ኢሌ
ኢሌ” ከዘመን ዘመን ያድርሳችሁ በማለት ልጆቹን አጥግበው
ያበሏቸዋል፡፡ አናታቸውን ቅቤ ይቀቧቸዋል፡፡ በዚህ ዕለት ልጆችንም ሆነ
ከብትን በአርጩሜ መምታት ነውርና አይደረጌ ነው፡፡
ፍቼ ፋሎ
“ፍቼ ፋሎ” የፍቼን በዓል በጋራ በባህላዊ አደባባይ በድምቀት የማክበር
ሥነ-ሥርዓት ነው፡፡ ስለሆነም በአመዛኙ የፍቼ ዕለተ ቀን በተከበረ
በሶስተኛው ቀን አሊያም አንደአካባቢው በተመረጡ ቀጣይ ቀናት “ፈቺ
ፋሎ” ወይም /ሻሻጋ/ በባህላዊ አደባባይ በጋራ ይከበራል፡፡አደባባዩ
“ጉዱማሌ” ይባላል፡፡ “ጉዱማሌ” የፍቼ በአል በጋራ የሚከበርበትና
እንዲሁም በሌላ ጊዜ የጎሳ መሪዎችና “ጭሜሳዎች” /ብቁ አረጋውያን/
ልዩ ልዩ ባህላዊ ስርዓት የሚያከናውኑበት የተከበረ ባህላዊ ስፍራ ነው፡፡
ህብረተሰብ በአሉን ለማክበር በጎሳ በጎሳ በመሆን በተለያየ ባህላዊ
ጭፈራና ባህላዊ አልባሳት አጊጠው ወደ “ጉዱማሌ” ይጓዛሉ፡፡ ሁሉም
በጋራ በየጎሳው ወደ “ጉዱማሌ” ከገቡ በኋላ የባህላዊው ሃይማኖት
አባቶችና የጎሳ መሪዎች እንደ ማህበራዊ ደረጃቸው በየተራ ንግግር
ያደርጋሉ፣ ይመርቃሉ፣ ባሮጌው ዘመንና በአዲሱ ዘመን ላይ ያተኮሩ
መልእክቶች ያስተላልፋሉ፡፡ በጎው እንዲጎለብት አስከፊው እንዳይደገም
ምክር አዘል መልዕክት ያስተላልፋሉ፤ ዘመኑ የሰላም፣ የብልጽግና የልማት
ይሆን ዘንድ ቃል ቡራኬ ያደርሳሉ፡፡
(የሲዳማ ዞን ማስታወቂያና ባህል መምሪያ በ2001 ዓ.ም
ካሳተመው ፍቼ መጽሄት የተወሰደ፡፡)
ምንጭ፦ http://tubamegazine.blogspot.com/2012/08/
fichchaa-2001.html

ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ !!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

YOUTUBE : https://youtube.com/@Historical_Ethiopia
ጥያቄ ካለዎት @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia
269 viewsየቃየል ታናሽ ወንድም, 16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 14:15:54
መጋቢት ፲፫ ፩፰፻፺፰ ዓ.ም ልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል ያረፉት ቀን ነበር። የገናናው የሸዋ ንጉሥ የንጉሥ ሳህለሥላሴ የልጅ ልጅ፣ የታላቁ ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክ የአክስት ልጅ እንዲሁም የግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ አባት የሆኑት ልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል ያረፉት መጋቢት ፲፫ ቀን ፩፰፻፺፰ ዓ.ም ነበር። ስመ ጥሩ የሸዋ ንጉሥ ሳህለሥላሴ ወሰንሰገድ ልዕልት ተናኘወርቅን ወለዱ፤ ልዕልት…
396 viewsየቃየል ታናሽ ወንድም, 11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 14:14:56 መጋቢት ፲፫ ፩፰፻፺፰ ዓ.ም ልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል ያረፉት ቀን ነበር።

የገናናው የሸዋ ንጉሥ የንጉሥ ሳህለሥላሴ የልጅ ልጅ፣ የታላቁ ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክ የአክስት ልጅ እንዲሁም የግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ አባት የሆኑት ልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል ያረፉት መጋቢት ፲፫ ቀን ፩፰፻፺፰ ዓ.ም ነበር።

ስመ ጥሩ የሸዋ ንጉሥ ሳህለሥላሴ ወሰንሰገድ ልዕልት ተናኘወርቅን ወለዱ፤ ልዕልት ተናኘወርቅ ደግሞ ወልደሚካኤል ወልደመለኮት አግብተው ልዑል ራስ መኮንንን ወለዱ፡፡ልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል የተወለዱት ግንቦት ፩ ቀን ፩፰፶፬ ዓ.ም ጎላ ወረዳ ደረፎ ማርያም በሚባል ሥፍራ ነው፡፡ ገና በወጣትነታቸው ወደ ምኒልክ ቤተ-መንግሥት ሄደው ከአጎታቸው ልጅ ከንጉሥ ምኒልክ (በኋላ ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ) ጋር ተዋውቀው ቤተሰባዊና ዝምድናቸውን አጸኑ፡፡

በፀባያቸውም ታገሽና አስተዋይ ስለነበሩ ከንጉሥ ምኒልክ ጋር ጠንካራ ወዳጆች በመሆን እንደ አባትና ልጅ ይተያዩ ጀመር፡፡ የሐረርጌን ግዛት በሚገባ በማስተዳደር ለንጉሥ ምኒልክ ሀገር የማቅናት ተግባር ብርቱ አጋዥ ሆኑ፡፡ ከቤተ መንግሥት ባለሟልነት ተነስተው በዘመኑ ከንጉሥ በመቀጠል ከፍተኛ ለሆነው የ‹‹ራስ›› ማዕረግም በቁ፡፡ልዑል ራስ መኮንን የአጼ ምኒልክ ተወካይ በመሆን ሁለት ጊዜ ወደ አውሮፓ ሀገራት ተጉዘዋል። ወደ ኢጣሊያ በሄዱ ጊዜም የኢጣሊያ ጋዜጦች የውጫሌ ውልን ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያ በኢጣሊያ መንግሥት ጥገኝነት ስር እንዳለች አድርገው የሚጽፉትን ጽሑፍ በመመልከታቸው ራስ መኮንን ተቃውሟቸውን ለኢጣሊያ መንግሥት ከነገሩ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው የውሉን መበላሸት ለአጼ ምኒልክም አሳውቀዋል።

የውጫሌ ውል ያስከተለው የትርጉም ለውጥ መፍትሄው ጦርነት ሲሆንም ልዑል ራስ መኮንን ሰራዊታቸውን ይዘው ከአምባላጌ እስከ እስከ አድዋ በተደረጉት ውጊያዎች ላይ በመሳተፍ ጀግንነታቸውን አስመስክረዋል፡፡ ልዑል ራስ መኮንን ከቤተ መንግሥት ባለሟልነት ጀምረው በወታደርነት፣ በጦር መሪነት፣ በግዛት አስተዳዳሪነትና በዲፕሎማትነት በፈጸሟቸው አኩሪ ተግባራት ምክንያት ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የዙፋናቸው ወራሽ ሊያደርጓቸው ያስቡ ነበር፡፡
ነገር ግን እምዬ ያሰቡት ሳይሆን ቀረና ልዑል ራስ መኮንን መጋቢት ፲፫ ቀን ፩፰፻፺፰ ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ ሞታቸው በንጉሰ ነገሥቱ ቤተ መንግሥት (አዲስ አበባ) በተሰማ ጊዜም ከፍተኛ ሀዘን ሆነ፡፡ ታላቁ ንጉሥ ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክም አምርረው አለቀሱ፡፡ በወቅቱም ይህንን የተመለከቱ ሰዎች እንዲህ ብለው ገጠሙ …

‹‹ዋ አጤ ምኒልክ እግዚአብሔር ያጥናዎ፣
በየበሩ ቋሚ ከላካይ ሞተብዎ፡፡
ሲታሰር አየነው ብረቱ ሲመታ፣
ምን ዋስ አገኘና ሐረርጌ ተፈታ፡፡
ጃንሆይ ምኒልክ ጠጉራቸው ሳሳና በራ ገለጣቸው፣
እንግዲህ ንጉሡ ምን ራስ አላቸው፡፡››
ከአልቃሾቹ መካከል አንደኛው ደግሞ የልዑል ራስ መኮንንን ደግነት ለማስታወስ እንዲህ ብሎ ሙሾ አወረደ …
«ስልከኛው ሲያረዳ ነገር ተሳሳተው፣
መኮንን አይደለም ድሀ ነው የሞተው፡፡»




ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ !!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

YOUTUBE : https://youtube.com/@Historical_Ethiopia
ጥያቄ ካለዎት @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia
340 viewsየቃየል ታናሽ ወንድም, 11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 21:23:24

441 viewsየቃየል ታናሽ ወንድም, 18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 21:22:30
'' ኢትዮጵያን ያላንተ አሰብኳት ፤ ማሰብም ከበደኝ።''

ሚኒሊክ ዛሬም ንጉሥ ነው !!




#አቤል_ባለሀገር


ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ !!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

YOUTUBE : https://youtube.com/@Historical_Ethiopia
ጥያቄ ካለዎት @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia
381 viewsየቃየል ታናሽ ወንድም, 18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 17:14:47
የምስራቁ የጦር ጀነራል ፍታውራሪ ያዮ ሀመዱ. ፍታዉራሪ የዮ ሀመዱ አብዛኛውን ጊዜ የሚታወቁት ፍታውራሪ በሚለው ስማቸው ነው፡፡ የተወለዱት በአፋር ኤሊዳኣር ወረዳ ኢሚኖ ቀበሌ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ። ፍታዉራሪ የዮ በአፄ ሀይለስላሴ ዘመነ-መንግስት የታወቁ የጦር መሪና አገረ-ገዢም ነበሩ፡፡ በአፄ ሀይለስላሴ ዘመን ከሱልጣን አሊሚራህ ጋር አዉሳንና አካባቢውን ለረጅም አመታት አስተዳድረዋል፡፡…
353 viewsሞዐ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ አቤል ባላገር ዘሀገረ ኢትዮጵያ, 14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ