Get Mystery Box with random crypto!

. በቃ እወድሃለሁ ═════❁✿❁ ═════ ለምን አትበለኝ ምክንያት የለኝም | የፍቅር ወላፈን

. በቃ እወድሃለሁ
═════❁✿❁ ═════


ለምን አትበለኝ ምክንያት የለኝም
ፍቅር ስሜት እንጂ ሰበብ አይመስለኝም

ብቻ እወድሃለሁ መውደዴ ጥልቅ ነው
ፍቅርህ ለኔነቴ የልቤ ዙፋን ነው
ህያው የምሆነው አንተን በማፍቀር ነው
ሀቁ ቃል ይኔ ነው እድሜ ልክ የማምነው

ቂልነት አይደለም ሁሌ አንተ ማለቴ
ሞኝነት አይደለም ለፍቅርህ መክሳቴ
ጅልነት አይደለም እራሴን መጉዳቴ
በቃ አንተን መዉደዴ ነው በደስታ
መደሰቴ

ውለታ ፈልጌ ውደደኝ አላልኩም
ፍቅር ስጠው እንጂ ምላሽ አልፈለኩም
እንዴት ለምን ካልከኝ እኔም አላወኩም
በቃ እወሃለሁ ማለቴን አልተውኩም

አዎ እወድሃለሁ
አዎ አፈቅርሀለሁ
በፍቅርህ ውቅያኖስ እኖራለሁ
አንተ ካለህልኝ ደስተኛ እሆኖለሁ
ፍቅር ስሜት መሆኑን አቀለሁ
አዎ እልሀለሁ ማለት አይሰለቸኝ
ደግሜ ደጋግሜ ፍቅርህ ያዛለው
ልቤን ታቅፌ አሁንም አይሰለቸኝ
እኔ አንተን እወድሃለሁ ማለቴ

#ፅኑ_ቃል


,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

@yefikrwelafen
@yefikrwelafen
@yefikrwelafen