Get Mystery Box with random crypto!

ሳብድ ግን ዝም በይኝ ብዬሽ ነበር የኔ አንቺ እየሳቅሽ እያለቀስኩ እኔ ሳብድ ዝም በይኝ በበርሽ | የፍቅር ወላፈን


ሳብድ ግን ዝም በይኝ

ብዬሽ ነበር የኔ
አንቺ እየሳቅሽ እያለቀስኩ እኔ
ሳብድ ዝም በይኝ
በበርሽ ስገባ በመስኮት ወተሻል
አንቺን ስጠብቅሽ አንቺ ግን ቀርተሻል

እኔማ

ፍቅር ሳይኖረኝ ስለ ፍቅር ዘፍኛለው
ተስፋ ሳይኖረኝ ስለ ተስፋ ገጥሜለው
ሳላገኝ ስለ ማግኘት ፃፌለው
አንቺ ሳታስቢኝ ስለ አንቺ አስቤለው

እናማ
ድንገት ካገኘሺኝ መንገድ ላይ አብጄ፡
ባላየ እለፊኝ ግድ የለም ወዳጄ፡
ምንም ቅር እንዳይልሽ በሰራሺው ስራ፡
ብቻ ዝም በይኝ ሳብድልሽ አደራ



,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

@yefikrwelafen ,,,,,, bina143u