ያበድኩ የለየልኝ መሰለኝ።ወደ ጆሲ ተጠጋሁና ነካ አደረኩት ።ያኔ ባሰብኝ።ለራሴ አዘንኩ እንባዬ በሁለቱም አይኖቼ ግጥም አለ። የጆሲንም እንባ ያየሁት መሰለኝ። ጆስዬ በናትህ ተንፍስ!? ጆሲ እባክህ እውነት ነው እየቃዥህ አይደለም በለኝ ። ህልም ነው እንዳትለኝ እሺ ጆሲ? አጠገቤ የቆመችው የንተዎ ኤደን ነች በለኝ ተወርውራ አንገቴ ላይ ተጠመጠመች !። "አዎ ዳንዬ ያንተዋ ኤደን ነኝ ሁሉንም ነገር ትቼ ወዳንተው መጥቻለሁ ። እጠብቅሻለሁ ብለከኝ የለ ዳንዬ አረሳከኝም አደል? ዛሬም ታፈቅረኛለህ አይደል ዳንዬ?" አፏን አፍኜ አቋረጥኳትና እንባዋን እየጠራረኩ ወደ ጆሮዋ በመጠጋት አንድ ጥያቄ ብቻ ልጠይቅሽ ኤዱዬ አልኳት። እሺ አለችኝ አፋን ስላፈንኳት ጭንቅላቷን እያወዛወዘች ። አንዴ ልጩህ በናትሽ????? ---------ተፈፀመ------ @yefikrclinic @yefikrclinic የፍቅር ክሊኒክ የቴሌግራም ቻናል 1.2K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 19:00