Get Mystery Box with random crypto!

ልጩህበት! የመጨረሻው ክፍል ክፍል 24 አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ . . . ሌላ ስሜት | ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

ልጩህበት!

የመጨረሻው ክፍል

ክፍል 24

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.
ሌላ ስሜት ውስጥ እንድትገቢ ስላልፈለኩ ነው ይህን ደብዳቤ በእጅሽ ሳልሰጥሽ ከምርቃቷ ቡሀላ ወደ አዲስ አባባ ስሸኛት ሳታየኝ የልብስ ሻንጣዋ ውስጥ አስቀምጥላታለሁ ባየችው ግዜ ትየው ብዬ የወሰንኩት።
በነበረን ስሜት ወንድምሽ ሆኜ ልሸኝሽ ቀናቶች ቀርተዋል ለዛም ተዘጋጅቻለሁ ።
የኔ ኤደን ዛሬም ቢሆን ስላወኩሽ ደስተኛ ነኝ።
የማንም ሁኚ እኔ ግን አፈቅርሻለሁ። መቼም ቢሆን አረሳሽም። ዝምምምም ብዬ ሳፈቅርሽ እኖራለሁ።
ሰላም ሁኚ!
__ ዳኒ ነኝ።
ደብዳቤውን ፅፌ እንደጨረስኩ ለመውረድ ተጨማሪ ሀይል እየጠበቀ ያቀረረውን እንባዬን ከአይኖቼ ላይ ጠራረኩና ተጠቅልዬ ተኛሁ።
የውስጤን በትንሹም ቢሆን አውጥቼ ስልፃፍኩት ነው መሰለኝ ቅልል ያለኝ መስሎ ተሰማኝ ። እንቃፍ ይዞኝ ከመሄዱ በፊት ፈጣሪዬ አንተ ያልከው ብቻ ይሁን! አልኩ ። እንቅልፍ ወሰደኝ።
ጥዋት ከንቅልፌ ስነቃ ጆሲ እክፍላችን ውስጥ መሀል ግድግዳ ላይ በሰቀላት ክብ መስታወት እየተመለከተ እርጥብ ፀጉሩን ያደራርቃል ።
በኔ ተናዶ ስለምንም ጉዳይ ከኔ ጋር ማውራት ካቆመ ቢቆይም ላወራው ፈለኩ•••
ጆሲ ለኤደን እኮ ደብዳቤ ፃፍኩላት !
"ተው ባክህ! ምነው ቁልቁል?"
ምንድነው ቁልቁል?
"በቴክኖሎጂ ተሽቀንጥሮ የተጣለውን የፍቅር ደብዳቤ መፃፃፍ ኬት ፈልገህ አገኘከው ብዬ ነዋ!"
የመረጥኩት መንገድ እሱን ስለሆነ ከወደቀበት አነዳሁት!
"ምርጫህ ከሆነ ይሁን ግን ምነው ፈጠንክ ገና ከመተዋወቃችሁ!"
እያላገጥክ ነው ጂሲ?
"እያላገጥክ ያለኸው እማ አንተ ነህ ዳንዬ እሄን ሁሉ ግዜ በፍቅራ ፍዳህን ስታይ ቆይተህ
አንተስ ወደህ ነው ባንተ እንደዛ መሆን እኔንም ቤተሰቦችህንም በጭንቀት ስትንጠን ከርመክ አሁን ልጅቷ ትምህርቷን ጨርሳ አንተንም ሀገሩንም ጥላ ልትሄድ ቀናቶች ሲቀሯት ምን ብለህ ልትፅፍላት ነው ?
እባክሽ ጥለሽኝ አትሂጂ ወይ ተያይዘን እንሂድ ልትላት ነው?
ቆይ በዚህ ሰአት ምን ልትላት ነው!?
አፈቅርሻለሁ ነው አፈቅርሽ ነበር ?"
ጆሲ በቃህ እንግዲህ አታናደኝ !
ከተረዳኸኝ እኔ ለሷ ያለኝ ፍቅር እሷን በማግኘትና በማጣት የሚወሰን አይደለም !
የትም ትሁን የማንም ትሁን አፈቅራታለሁ!
ደሞም ደብዳቤውን የፃፍኩት አሁን ልሰጣት አይደለም!
"ምን ማለት ነው ? ከሄደች ቡሀላ በፖስታ ቤት ልትልክላት ባልሆነ!"
ለምን አይሆንም ?ቢሆንስ?
" እንዴ ታድያ ለምን መፃፉ አስፈለገህ ዝም ብልህ እንዲሁ ፍቅር ዲዳ ያረገህ ይመስል ትንፍሽ ሳትል እንደተለጎምክ ለምን አትሸኛትም?
አዋ እንደተለጎምኩ እሸኛታለሁ ከልጁ ጋር ፍቅር እንደጀመሩ እርግጠኛ ነኝ የኔ ላትሆን ላስጨንቃት አልፈልግም !
"ታድያ እንደዛ ካሰብክ ተዋታ ! እርሳታ በቃ ደብዳቤውን እዛ ደርሳስ ቢሆን ስትልክላት ማንበባቧ ይቀራል እንዴ ያኔስ አትጨነቅም ነው የድሬዳዋ እና ያዲስ አበባ ጭንቀት ይለያያል!"
ጭንቀቱ ላይለያይ ይችላል ያንን የማደርገው በሁለት ምክንያት ነው
አንድ አሁን በመመረቋ የተሰማትን ደስታ ላለመረበሽ
ሁለተኛው እና ዋናው ምክንያቴ ደግሞ ተመርቃ ከሄደች ከኔ ምንም ነገር በማትፈልግበት ሁኔታ ውስጥ ስትሆን ለመወሰን ነፃ ትሆናለች
"አየህ አሁንም ዙረህ ዙረህ ቋጠሮው ጋር ሄድክ ዳንዬ እሄን ቋጠሮ መፍታት ወይ መተው ካልቻልክ በሷ ጉዳይ ከኔ ጋር መቼም አንግባባም "
ብሎኝ ጥሎኝ ወጣ። እሱ ባይሰማኝም
እንኳን ካንተ ጋር ከራሴም መግባባት አልቻልኩም ጓደኛዬ ይቅርታ ስላስጨነኩህ አልኩ ለራሴ።
የኤዱ ቤተሰቦች ድሬ ዳዋ ከመድረሳቸው ከሰአታት በፊት ያ ከመደብደብ ያተረፈኝ ጥበቃ ወደ ሚሰራበት ሆቴል ሄድኩና አልጋ ያዝኩላቸው ስገባ አለነበረም ስወጣ ገና ከሩቅ ሲያየኝ መሳቅ ጀመረ አጠገቡ ስደርስም•••
" ካካካካ ስማ እኔ እኮ እነዛን ልጆች አውቃቸዋለሁ ያን ቀን የባጥ የቋጡን ቀባጥሬ ባላስመልጥህ ለቀብር እሚሆንም እንኳን አያስቀሩልህም ነበር
የት እንደማውቃቸው ታውቃለህ•••"
ብሎ ሊቀጥል ሲል እኔም ፈገግ እያልኩ አቦ ሌላ ግዜ በሰፊው እናወራለን እሺ ከአዲስ አበባ የሚመጣ እንግዳ ልቀበል ነው ደርሰዋል ብየው የሻሂ ሰጠሁትና ሄድኩ።
ከኤዱ ጋር ሆነን ቤተሰቦቿን እየጠበቅን ያ ልጅ በየደቂቃው ይደውል ነበር ስታናግረውም ከኔ ፈንጠር እያለች ነበር ቤተሰቦቿ ደርሰው በኔው ባጃጅ ወደ ያዝኩላቸው ማረፊያ ሄድን ።
እንደደረስን •••
"እማ ዳኒ ማለት እኮ እሱ ነው " አለች እናትና አባቷን በየተራ ልብ በሚሰውረው ፈገግታዋ እያቻቸው።
አቤት ምርቃት እናትና አቧቷ እየተቀባበሉ የመረቁኝ ምርቃት ሰምቸው ሁላ አላውቅም ካሁን ቡሀላ በሂወት ዘመኔ ማንም እኔ ነኝ ያለ ተራጋሚ የፈለገውን አይነት እርግማን ቢረግመኝ እራሱ እሄን ምርቃት አሸንፎት እንደማይደርስብኝ እርግጠኛ ነኝ።
ኤዱ በተመረቀችበት እለት መሄዷን እያሰብኩ ውስጤ ሀዘን ቢሰማውም መመረቋ በሷና በቤተሰቦቿ ፊት ላይ የማየው የደስታ ጥግ ግን ሀዘኔን ለግዜውም ቢሆን አክሽፎት ደስታቸውን ለመጋራት ተገደድኩ።
እንዳትደርስ የፈራኋት የመጨረሻዋ ሰአት ደረሰች።
እኔና ኤዱ በኔ ባጃጅ ወደ ግቢ ሄድንና ከግቢ ያመጣቻቸውን ሻንጣዋን ጨምሮ ሌሎች የግል እቃዎቿን ባጃጇ ውስጥ አስገብታ•••
"ዳኒዬ መጣሁ እሺ ጓደኛቼን ልሰናበታቸው" ብላኝ ሄደች።
ደብዳቤውን ከውሃላ ኪሴ አወጣሁና የልብስ ሻንጣዋን ከፍቼ ልብሶቿ መሀል አርቄ ቀበርኩት።
ሀሙስ ከለሊቱ 10:30 ድሬ ዳዋ የድሮ ባቡር ጣብያ ፊት ለፊት ባጃጄን ተደግፌ ቆሚያለሁ
ከኔ ፊት ለፊት እነ ኤዱን ይዞ ወደ አዲስ አበቧ የሚነጉደው ዘመናዊ አውቶብስ የተሳፋሪዎቹን እቃ ከታች ሆዱ ውስጥ ተሳፋሪዎቹን ደግሞ ከላይ ጭኖ ለመምዘግዘግ መዘጋጀቱን በሚያጓራው ድምፁ ያውጃል።
ኤዱ አንዴ ከኛ ራቅ ብለው የያዙትን እቃ ወደሚያስመዝኑት ቤተሰቦቿ አንዴ ውስጤ ትርምስምስ እንዳለ ባጃጄን ተደግፌ ወደ ቆምኩት ወደኔ ሄድ መለስ ትላለች ።
ግራ ግብት! ጭንቅ !እንዳላት ታስታውቃለች ።
የን ስሜት የፈጠረባት የኔ ሁኔታ ሳይሆን አይቀርም ።
ምንም ማውራት ሳንችል በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ካቅማችን በላይ ሆነና መላቀስ ጀመርን በቃ ተላቀስን እሷን እያባበልኩ እኔ አለቀስኩ።
እኔን እያባብለች እሷም አለቀሰች ።
ተለያየን ሄዱ ።
በሄደች በአራተኛው ቀን ስልኬ ላይ በማላውቀው ቁጥር ተደወለ አነሳሁት ••• ኤዱ ነች•••
"ዳንዬ ቆይ ለምን ለምን ለምን " ብቻ ብላ ማልቀስ ጀመረች ደብዳቤውን አግኝታ አንብባው እንደሆነ ገባኝ ።
በስልክም ከመላቀስ ውጩ ብዙ ማውራት አልቻልንም ነገር ግን በሷ ምክንያት በመጎዳቴ እጅግ ማዘኗንና ከልጅ ጋር በፍቅር አብራ መሆኗን ነገረችኝ ለኔ አዲስ አልነበረም በነበርኩበት ከባድ የድብርት ሂወት ቀጠልኩ።
ይህ ከሆነ አንድ አመት ከሁለት ወር እንደሆነው
እንደሁልግዜው ማታ በስካር ጥንብዝ ብዬ ገብቼ ተኝቻለሁ እዛው እንደተኛሁ ከቀኑ አምስት ሰአት አከባቢ ከተኛሁበት በሀይል ተቀሰቀስኩ ብንን ስል ጆሲ ጋደኛዬ እና የኔዋ ኤደን አጠገብ ላጠገብ ቆመዋል።
ወይ መቃዥት አልኩና አይኔን እየጠራረኩ ከተኛሁበት ብድግ ብዬ ቆምኩ አሁንም ፊት ለፊቴ ጎን ለጎን ቆመዋል።ግን ዝም ብለው ያዩኛል እንጂ ትንፍሽ አይሉም።