Get Mystery Box with random crypto!

ስብራት የመጨረሻ ክፍል ደከመኝ፡፡ ትላንትን ማሰብ ደከመኝ፡፡ ያልሻሩ ቁስሎቼን ማሰብ ደከመኝ | ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

ስብራት

የመጨረሻ ክፍል

ደከመኝ፡፡ ትላንትን ማሰብ ደከመኝ፡፡ ያልሻሩ ቁስሎቼን ማሰብ ደከመኝ፡፡ ሰዎች እንዲያቆላምጡኝ ተመኝቼ በሙሉ ስሜ እንኳን አለመገራቴን ማሰቡ ደከመኝ፡፡ ካወጡኝ ወንዶች መካከል ስምሽን ረስቼዋለው ያሉኝ እንዳሉ ማሰቡ ደከመኝ፡፡ የህይወቴ ደራሲ የሆነው ጭምር ስሜን አያውቀውም ብሎ ማሰቡ ደከመኝ፡፡

ሩብ ክፍለ ዘመን በዚህች ምድር ላይ የኖርኩ ቢሆንም አመታቱ የባከኑ ነበሩ፡፡ እኔ ሴት ነኝና እድሜ ያሳስበኛል፡፡ የውበት ጉዳይ ያስጨንቀኛል፡፡
ሴቶች ከጊዜ ጋር ተሳስረን ተፈጥረናል፡፡ የወር አበባችን ጊዜን ይነግረናል፡፡ የፅንሰት ዘመናችን ስለ እድሜ ዋጋ እንድንሰጥ ያስገድደናል፡፡ የምንወልድበት ጊዜም በገደብ የተፈጠረ ነው፡፡ በዚህ ሁለ ምክንያት እድሜ ለኛ ዋጋ አለው፡፡ ወንድ ልጅ የኛን ሩብ ያህል ስለዘመን እንደማይጨነቅ እወራረዳለሁ፡፡ ለኛ ለሴቶች እድሜ ሁሉንም ነገር ይወስነዋል፡፡ መፈቀር መውለድ የወር አበባ ማየት.... ሁሉም ከእድሜ ጋር ይተሳሰረብናል፡፡

የአበባነት ዘመናችን አጭር ነው፡፡ የሆነ ዘመን ላይ እንደምቅና ድምቀታችንን አጣጥመን ሳንጨርስ መክሰም እንጀምራለን፡፡ ተወልደን ሳንጨርስ እናረጃለን፡፡ እድሜ ብሽቅ ነው! ብሽቅ

ጠለቴ መውረድ የጀመረ ይመስለኛል፡፡ ቂጤ እንደቀድሞ እንዳልሆነ ይታወቀኛል፡፡ ጉንጮቼ ማድያት ማውጣት ጀምረዋል፡፡ ከንፈሬን ስጃራ አጥቀሮታል፡፡ እያረጀው ይሁን?
ገና የባሰ ቀን ይመጣል፡፡ በተፈጥሮዬ ውብ የነበርኩት በሜካፕ ጉልበት እንኳን ማማር ማልችልበት ብሽቅ ቀን ይመጣል፡፡ ማርጀት ያስፈራኛል፡፡

መክሰም አልፈልግም፡፡ ተወልጄ ሳልጨርስ ማርጀትን አልሻም፡፡ መኖር ሳልጀምር መሞት አልፈልግም፡፡ ዛሬን ሳላጣጥም ከትላንትናዬ ሳልወጣ መሞት አልፈልግም፡፡

በህይወቴ ዛሬ ሚባል ቀን ኖሮኝ አያውቅም፡፡ የሆነ ወቅት ላይ ስለነገዎቼ ሳስብ ዛሬዎቼ አመለጡኝ፡፡ ያለልክ በተስፋና ህልም ውስጥ ገብቼ ነበርና የአሁን ሃያልነት ተረሳኝ፡፡ ነገ ያልኩት ቀን ሲደርስ ደግሞ ተስፋ ካደርግናቸው ህልሞቻችን መካከል ብዙዎቹ እንደ ጉም ማይጨበጡ እንደሚሆኑ ገባኝ፡፡
ለጋ እያለው ግን ሁሉም ህልም ሚሰምር ይመስለኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ከንቱ ምኞት እንነበረ አየው፡፡

ብዙ ተስፋዎቼ ታላላቅ ህልሞቼ መክሰም ሲጀምሩ በድንጋጤ ወደ ትላንት ፈረጠጥኩ፡፡ ዛሬዬን በትላንት ውስጥ ሸሸግኩት፡፡ ትላንት ውስጥ ስደበቅ ዛሬዬ መትነን ጀመረ...
መኖር ሳልጀምር መሞት የጀመርኩ በአግባቡ ሳልደምቅ መክሰም የጀመርኩ አበባ ነኝ፡፡

እኩለ ቀን አልፏል፡፡ አሁንም ግን የተዘጋ ቤት ውስጥ ነኝ፡፡ ማለዳዬንና ረፋዱን በዘጋሁት ቤቴ ውስጥ ሆኜ በሃዘንና ተስፋ ማጣት ስሜት ተውጬ አሳልፌያለሁ፡፡ አሁን ግን መውጠት ፈለግኩ፡፡

እንደምንም እየታገልኩ ወደደጅ ስወጣ ፀሃዩ ይከብዳልና አይኔ ተጭበረበረ፡፡ ጋግርታሙ ደመና ሰማዩን ለቆት ሄዶ ፀሃይ ተተክታለች፡፡

ፀሃይ እናቴን ትመስላለች፡፡ በማለዳዋ ዘመን ምትፈቀር ቀትር ሲሆን ሚያማርሯት አመሻሽ ላይ ደግሞ ለተረኞች ስፍራዋን አስረክባ ምትሸሽ....

ሰማዩ እኔን ይመስላል፡፡ ሁለም ሚፈራረቅባት፡፡

መምሸቱ አይቀርም፡፡ ሲመሽ ደግሞ ከዋክብትና ጨረቃ በጨለማው ሰማይ ላይ ይደምቃሉ፡፡ ይህን ሳስብ ሰማዩ አሳዘነኝ፡፡ ከዋክብት ለመድመቅ ሰማዩ ላይ የተፈጠረውን ጨለማ የተጠቀሙበት መሰለኝና ሰማዩ አሳዘነኝ፡፡
ጨለማዬን ለድምቀታቸው የተጠቀሙበት ስንት ናቸው?

አመሻሽ ላይ በስተምእራብ በኩል ሰማዩ በእሳት የተቀቀለ ብረት ሲመስል ማየት ያጓጓል፡፡ እኔን በወከለው ሰማይ ምትወጣን ወርቃማ ጀምበር ማየት አጓበኝ፡፡ ፍም እቶን የሚመስለውን የሰማይ ክፍል በፍቅር እየተመለከትኩ ሃሴት ማድረጉ አጓጓኝ፡፡

የማለዳው ተወዳጅ ሰማይ አምልጦኛል፡፡ ቀጥሎ የወጣው ጋግርታም ደመና ተገፎ ለፀሃይ ተራውን አስረክቧል፡፡ ይህም ፀሐይ ያልፋል፡፡ ንዳዱ ይበርድና ውቧን ጀምበር በሰማይ ምንጣፍ ላይ አያታለው፡፡

የዛሬን ፕሮግራሜን ካስተካከልኩ ጀምበሯን አያታለው፡፡ የመዋሰብ ቀጠሮ አለብኝ፡፡ ቀጠሮዬን ከሰረዝኩ ጀምበሬን አያታለው፡፡ ደግሞም በጋግርታም ስሜት ተሞልቼ በሬን ዘግቼ የመምከንከን ባህል አለብኝ፡፡ በኋላ ግን መውጣት ይኖርብኛል፡፡

ሰማዩ እኔን ይመስላል፡፡ በሰማዩ ምንጣፍ ፀሃይና ደመና ብቻ ሳይሆን ውብ ጀምበርም ይወጣል፡፡

! ጀምበሯን አያታለው፡፡ በልቤ ተስፋ እየተወለደ ነው፡፡ ሃሌሉያ!

ተፈፀመ
@Yefikrclinic
@Yefikrclinic
@Yefikrclinic