Get Mystery Box with random crypto!

ስብራት ክፍል አስራ ሁለት እኔ መርከብ ነኝ፡፡ የሆነች ትንሽ ስንጥቅ ተፈጥሮባት በስንጥቁ በ | ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

ስብራት

ክፍል አስራ ሁለት

እኔ መርከብ ነኝ፡፡ የሆነች ትንሽ ስንጥቅ ተፈጥሮባት በስንጥቁ በኩል በገባ ውሃ የተነሳ መስጠም የጀመረች መርከብ!

ንፅፅር ሚባል መዶሻ ባሳረፈብኝ ዱላ የተነሳ በተፈጠረብኝ ስንጥቅ ቅናት ሚባል ውሃ ገብቶብኝ ገብቶብኝ መስጠም የጀመርኩ መርከብ!

ቤተዘመዶቼ ከአክስቴ ልጅ ጋር አነፃፀሩኝና ከርሷ አንፃር የማልወደድ እንደሆንኩ በድርጊታቸው ነገሩኝ፡፡ ያኔ የአክስቴን ልጅ ጠላዋት፡፡

መሸማቀቅ የወለደ ዝምታዬን የተመለከቱ ተግባቢ ካሏቸው ጋር ሲያነፃፅሩኝ ሳይ ማህበራዊ ህይወት አስጠላኝ፡፡

የሃይማኖት ሰባኪዎች በዘወርዋራ ፃድቃን ካሏቸው ጋ ሲያነፃፅሩኝ ሃጥያተኝነቴ ጎላብኝና የሃይማኖት ተቋማትን ደጅ ላለመርገጥ ማልኩ፡፡
አያቴ ዘመኔን ከዘመኑ ጋ ሲያነፃፅር ስመለከት የቀደመውን ዘመን ጠላው፡፡

ተውኝ አታነፃፅሩኝ እኔ እራሴን ብቻ ነኝ ማለት ብፈልግም ዙርያዬን ማነፃፀር በሚወዱ ብሽቆች ተከብቤያለው፡፡ የወይንን ግንድ ከቡና ግንድ የበቆሎን ፍሬ ጤፍ ፍሬ ሚያነፃፅሩ ብሽቆች!

ንፅፅር ሰባሪ እንደሆነ ማይገነዘቡ ደደቦች ያስጠሉኛል፡፡

ዩኒቨርስቲ ደጅን የረገጥኩ ሰሞን ስለሴቶች ግድ ይሰጠናል ያሉ ሴትነትን ከወንድነት አንፃር ተመልክተው ሴትነትን ሲያከስሙት አይቻለው፡፡ ለሴቶች ተቆረቆር በሚሉ ሴቶች የተነሳ ሴትነት ስከስም ተመልክቻለሁ!
በዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ ወቅት ሴቶችን ብቁ ሴት ከማድረግ ይልቅ ወደ ወንድነት በማሸጋገር እኩልነትን ለማስፈን የሚጥሩ ድኩማንን ተመልክቻለሁ፡፡
እንዴት የወይን ፍሬ የቡናን ፍሬ ሁን ይባላል? ከብርቱካን ዛፍ ላይ የማንጎን ፍሬ መጠበቅ በምን ሚዛን እኩልነት ሆነ? የጨረቃን ሚና በፀሐይ ሚና ለመለወጥ መጣር መዘመን ወይስ ማበድ? ብሽቅ ስሌት!

አባትና እናቴን አሰብኳቸው፡፡ አባቴ ድምፁ ሻካራ ቢሆንም እወድለታለው፡፡ ልክ እንደድምፁ ተፈጥሮዎም ጠንካራ ነው፡፡ በጥንካሬውና በልቡ ባለው ጦረኛ ባህሪ የተነሳ ከለላ ሊሆነኝ ጥሯል፡፡
ባይሰምርለትም እንደ ሞረድ ሻከሮ ሊሞርደኝ ጥሯል፡፡

እናቴ ለስላሳ ድምፅ አላትና ድምጿን እወድላታለው፡፡ እንደድምጿ ሁሉ መለሳለስ ባህሪዋ ነው፡፡ ከልስላሴዋ ሚቀዳ ፍቅርና ርህራሄን ልታካፍለኝ ሞክራ ነበር፡፡ አልሰመረላትም እንጂ በለስላሳ ማንነቷ ላይ ልታንተራሰኝ ጥራ ነበር!

አሁን ላይ ሳስበው በዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ እናትና አባቴን ቦታ ላቀያይራቸው የሞከርኩ ይመስለኛል፡፡

ሴት ልጅ ቦክሰኛ እንድትሆን ጡቷ እንደማይፈቅድ እያወኩ ሴቶች ከወንድ እኩል ናቸውና ቦክሰኛ ይሁኑ አልኩ፡፡ ከወንድ ጭቆና ነፃ ለመውጣት ወንድነትን ማዳበር ጤነኛ መንገድ ነው ማለት ሲቃጣኝ ሴትነትን የማክሰም ወንጀል እየፈጸምኩ እንደሆነ አልተገለጠልኝምና በልጅነት ዘመኔ እናቴ የደረባት መከራ በህይወቴ እንዳይደገም በመፍራት አባቴን ለመሆን መጣር ጀመርኩ! ራስን ለመበደል የተወሰነ ብሽቅ ውሳኔ!

ሲዳራ ጠማኝ፡፡አጣው፡፡ ሲጃራ ሳጣ ከዘጋሁት ቤቴ ወደውጭ መውጣት አሰኘኝ፡፡

ይቀጥላል

@Yefikrclinic

@Yefikrclinic
@Yefikrclinic