Get Mystery Box with random crypto!

. . .  #ውሸቴን_ነው_ለካ . . . አቅሙ እንዳለው ሰው በመርሳት ልረካ እረሳሁህ ያልኩት ው | የፍቅር ጥቅሶች❤️


. . .  #ውሸቴን_ነው_ለካ . . .

አቅሙ እንዳለው ሰው በመርሳት ልረካ
እረሳሁህ ያልኩት ውሸቴን ነው ለካ!

ብዙ’ኮ አፍቃሪ አለ . . .
እውነቱን በልቡ ባፉ ውሸት ይዞ
እረስቼዋለው እያለ ሚያወራ በሽንፈት ተክዞ

ምስልህን ልቤ ላይ አትሜው ካይኖቼ
ፎቶህን ብቀደው ካለበት አውጥቼ

እረሳውህ ብዬ ላስታውስህ ነገር
ከዚህ የበለጠስ ምን ሽንፈት ሊፈጠር

ስልክህ ከስልኬ ላይ እንዳይቀር ማጥፋቴ
ለካስ ውሸት ነበር አወይ ጅሉ እምነቴ

በቃሌ ሸምድጄው ልረሳህ ብለፋ
ትርጉም ይሰጣል ወይ? ቁጥርህን ባጠፋ

እናማ ሲገባኝ . . .
ለካስ ውሸቱን ነው መሸነፉን አምኖ ላለመባል ፈሪ
እረሳሁ እያለ የሚዘላብደው አብዛኛው አፈቃሪ ፡፡
─━━━━ ⊱✿⊰ ━━━━━─

@yefikir_tiksoch 
@yefikir_tiksoch 

ሼር