Get Mystery Box with random crypto!

የተውጋ ልብ ሀዊ #ክፍል 4 አስተማሪ .....ሰራተኛ ሁሉንም እጠይቃለሁ። ብቻ | 👑የፍቅር_ደብዳቤዎች 💏

የተውጋ ልብ

ሀዊ

#ክፍል 4


አስተማሪ .....ሰራተኛ ሁሉንም እጠይቃለሁ። ብቻ አሁንም ተስፋ ያልቆረጠው ልቤ አራት ኪሎ አለሁ። ጊቢው አያቀኝም እንጂ .......በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ..የአራት ኪሎ የተፈጥሮ ሳይንስ ግቢ አካባቢ ምንም ግሬድ የለንም እንጂ የሁለተኛ አመት ተማሪ ሆኛለሁ።..

"ያቺ ምታተኛ ቀን እኔ ና ክብሮሜን ጓደኛ አድርጋናለች። ሹራብን አመስግኜ ልመልስለት ስል ነው በጣም እረጅም ሰዓታት አብረን አሳለፍን ተግባባን ከመግባባትም በላይ አብረን መዝናናት ምግብ መብላት የሚኖረው ከናቲ ጋር ነው። አልተሳሳምን እንጂ ልክ ፍቅረኞች እንደሚሆኑት እንሆናለን።

እቤቱ ቁጭ እኔ በሀሳብ ባህር እዋኛለው
ሂዊ ......እንዴ.....ውደ እኔ እየተጠጋ ድንገት ሳላስበው ከአይኞቼ የእንባ ዘለላ ድብ እያለ ይወርዳል። የውረደው እንባዬ ከናፍሮቼ ጋር ደርሰው ከንፈሬን እንደመንከስ ስል ጨው ጨው የሚል ነገር .......ክብሮሜ በደንብ ተጠግቶኝ ምን ሆሽብኝ አንዴ ያቅፈኛ አንዴ በእጁ ቀና እያደረገ ይመለከተኛል እኔ ....። ባሰብኝ ተነፋረኩ የኔ እንደዛ መሆን ግራ አጋብቶታል ......ሂዊ አታስጨንቂኝ ንገሪኝ ........

ሁለት አመት ሙሉ የያዝኩትን ዛሬ ላይ አልቅሼ ልውጣልኝ አልቻለም። በዛ አንደበቴ ስለሁሉም ነገር ነገርኩት።

"በድንጋጤ ግን ለምን ደበቅሽኝ እኔ ምንም እንደማልደብቅሽ እያወቅሽ እእእእ ሂዊ........በቃ አታልቅሺ እኔ አገኛዋለው እንደምንም ብዬ ......
"ባያገኛው እንኳን ውስጤ እንደዛ ስላለ ደስ ብሎታል ጉንጩን ስሜ እንባዬን እየጠራረኩ ....።።.....
"አረ ሰዓቱ ...... በቃ ልሂድ
" ክብሮሜ በቃ እስከሳምንት አንገናኝም ማለት ነው ትናፍቀኛለክ እኮ ታውቃለክ እስከዛሬ ማንም እንዳንተ የቀረብኩት ሰው የለም። ....
" ሂዊዬ አውቃለው እኔም ካንቺ በላይ ነው የምናፍቅሽ ግድ ስለሆነ ነው የምሄደው እንጂ ፍላጎት ኖሮኝ አይደለም።..........

ሰፈር አካባቢ ደርሰን ትንሽ ጨለም ስላለ ጋሽ አንዳርጌ የሉም ደስ አለኝ።....ቢኖሩ እንደሚያስገብት 100%እርግጠኛ ነኝ

የቆምንበት ጋር ቦይ ነበር ሳላስበው ውስጡ ገባው እኔን ለማውጣት እጂን ዘረጋልኝ እኔም በፀፋው ውደ እሱ ሳብ ሲያረገኝ ደረቱ ላይ የያዘውን እጄን ውደልብ አስጠግቴ አይን ለአይን መተያየት ...... እኔ እጄን ወደ አንገቱ የማላውቀው ስሜት ከላይ እስከታች ነዘረኝ እሱ ቁና ቁና መተንፈስ ጀመረ ምንም ቃል አልተነፈስኩም አይኖቼን ጨፍኜ ስጠጋው.......

ይቀጥላል .....