Get Mystery Box with random crypto!

የፒያሳዋ ወፍ #ክፍል አንድ እነሆ ተጀመረ ደራሲ ፦ ዘሪሁን ገመቹ ዋቅቶላ እባላለው፡፡ከክልል | የፍቅር ጎጆ

የፒያሳዋ ወፍ
#ክፍል አንድ እነሆ ተጀመረ

ደራሲ ፦ ዘሪሁን ገመቹ


ዋቅቶላ እባላለው፡፡ከክልል ለስራ ነው የመጣውት ፡፡እርግጥ አዲስ አበባ ስመጣ
የመጀመሪያ ቀኔ አይደለም፡፡በተለያ አጋጣሚዎች በአመት አንዴም ሁለቴም ለቀናቶች ቆይታ
እመጣለው፡፡አዲስ አበባ ለስራ ስመጣ ደስተኛ ሆኜ አይደለም የምመጣው፡፡አብዛኞቹ
ነገሮቾ አይመቹኝም፡፡ልክ ከሆነ ሰርጐ ገብ ጠላት ጋር ለመፋለም ወደ በረሀ የተላኩ አይነት
ስሜት ነው የሚሰማኝ፡፡ወደ ጦርነት እንደምሄድ አይነት፡፡
ሁለ ነገሯ የተጨናነቀ ነው፡፡ወከባ እና ኳኳታ የሚመረትባት የትርምስ ፋብሪካ
ትመስለኛለች፡፡የሰው ልጅ ከሰባአዊነት ዝቅ ብሎ በየጥጋ ጥጉ የተወሻሸቀባት ..እናት
ልጆቾን ለመለመኛነት የምትገለገልበት….ጎልማሳው ለማኝ የሰውን ልብ ለማራራት ሰውነቱን
የሚያቆሳስልባትና የሚቆራርጥባት መኖር የየእለት ፈተና የሆነባት….ሰው ለሆዱ ብቻ
ሲባትት የሚውልባት …ለአብዛኛው የወር የቤት ኪራዩን ከወር ደሞዙ እኩል የሆነባት….
የብዙ ምንድባኖች ማጠራቀሚያ መጋዘን ትመስለኛለች፡፡
ይሄን ስል በተቃራኒው በድሎት የሚቃትቱ ቱጃሮችን በውስጧ ሳላይ ቀርቼ አይደለም፡፡
በከተማዋ ዳርቻዎች እየታነፁት ህንፃዎች ከተማዋን የሲወዘርላድን ከተማ ነች እንዴ …?
ብለን እንድንገረም የሚያደርጉትን አፍን የሚያሲዙ ድንቅ መንደሮችም ታዝቤያለው.. ግን
ፖሊስ ስለሆንኩ መሰለኝ ዓይኖቼ ወደ ተገፉት ያደላሉ…ትኩረቴ ጓስቆሎች መንደር መክርም
ይወዳል፡፡
ላዳር የመረጥኩት ፒያሳን ነው፡፡ለምን ብትሉኝ ምክንያጽ የለኝም፡፡ግን አላውቅም
ጨለምለም ሲል እግሬ ወደእዛ መራኝ ፡፡የለበስኩት የሲብል ልብስ ነው፡፡በእጄም ምንም
አይነት ሻንጣ ወይም ሌላ ዕቃ አልያዝኩም፡፡ምክንያቱም ዕቃዎቼ ጠቅላላ ይዘናት የመጣነው
መኪና ውስጥ ነው ያስቀመጥኩት፡፡
ትንሽ ዞር ዞር ካልኩ ቡኃላ ከጣይቱ ሆቴል ቀጥለው ካሉ ሆቴሎች መካከል ወደ አንድ ጐራ
ብዬ ማደሪያዬን 150 ብር ተከራየው፡፡ቤርጐዋ መፈናፈኛ የሌላት በጣም ጠባብ ብትሆንም
ብዙም ግድ አልሰጠኝም፡፡‹‹ደግሞ ለአንድ ቀን…›› አዳር ብዬ እራሴን አጽናንቼዋለው፡፡
ቤርጐ ከያዝኩበት ክፍል ወጣውና በእግሮቼ መንቀሳቀስ ቀጠልኩ፡፡እራቴን እንዳልበላው
ያወቅኩት በመንገዴ ላይ የይሆሚያ ክትፎ ቤትን ሳይ ነው፡፡አንጀቴ በምግብ አምሮት
ግልብጥብጥ ስላለብኝ አላወላወልም ገባው፡፡
በጥንድም በብድንም የሆኑ ተመጋቢዎች በብዛት ይታያሉ …እኔም እጄን ታጥቤ መቀመጫ
ያዝኩ፡፡የቤቱ አብዛኛውን ነገሮች ባህላዊ እንዲመስሉ ለማድረግ ተሞክሮል …ያዘዝኩትም
ክትፎ ሲቀርብልኝ የበላውት በጣም ጣፍጦኝ ነው፡፡ቢሉ እጄ ላይ ሲደርስ ግን በተቃራኒው
እንዴት እንደጐመዘዘኝ አትጠይቁኝ፡፡አይ አዲስ አበባ …አንድም ለዚህ ነው የምታስጠለኝ..፡፡
እንድከፍል የተጠየኩት ብር እኮ በሀገሬ አንድ ደህና ጠቦት ይገዛል፡፡
ለማንኛውም ከፈልኩና ስወጣ ሰዓቱም ገፋ ብሎ ነበር ፡፡ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ›…በዚህ
ሳዓት ወደ መኝታዬ መመለስ አልፈለግም..በዚህ ሰዓት ገብቼ ልተኛም ብል እንቅልፍ እሺ
አይለኝም.. ..የአስፓልቱን ጥግ ይዤ በቀጥታ መንገዴን ቀጠልኩ…ግራና ቀኝ ያሉ አጥሮች
ሁሉ በቆነጃጅት ተሞልተዋል….በ14 ዓመት እና በ40 ዓመት መካከል ያሉ ሴቶች
እራሳቸውን ለገበያ አቅርበዋል፡፡ብቲክስ ውስጥ ለሽያጭ እንደተሰቀሉ የልብስ ሞዴሎች
ይመስላሉ ፡፡ልክ ሸማቹ መጥቶ በዓይኖቹ መርምሮ በእጆቹ ደባብሶ ይሆነኛል አይሆነኝም
ብሎ አመዛዝኖ ሂሳብ ተደራድሮ ቀንሱ አልቀንስም ተባብሎ ቀልቡ ከወደደለት ከፍሎ
አስጠቅልሎ ይዞቸው እንደሚሄድ ከልሆነው ደግሞ እዛው እነበሩበት ማንጠልጠያ ላይ
ሰትሮቸው ጉዞውን እንደሚቀጥል አይነት ነው፡፡
እኔም ልክ እንደሸማች እያንዳንዷን በአይኔ እየመረመርኩ፤ እየተደነቅኩ እና እየተገረምኩ
ጉዞዬን ቀጠልኩ …ያ ብቻ አይደልም የሚያስደንቀው እነዛው ቆነጃጅት የቆሙበት አጥር
ወይንም ግንብ ወይንም ቤት ግድግዳ ስር ማዳበሪያ ውስጥ ገብተው የተኙ፡በላስቲክ
ተጠቅልለው የተጋደሙ ፤በለበሱት ልብስ ተኮራምተው በተቀመጡበት ድፍት ያሉ የጓዳና
ልጆች ይታያሉ…የሚበላ ዕንቁላል ቅቅል የሚያዞሩ ጨቅላ ወጣቶች..ጥግ ይዘው ሲጋራና
መስቲካ የሚቸረችሩ..ኮንደምና ብሱክት በካርቶን ዳርድረው ሚሸጡ… ብዙ ብዙ ትዕይንት
ይታያል፡፡ነፍሱ አንድ ብር ስጠኝ…ቆንጆ አትለፈኝ…..ልጅ አዝለው በስራቸው ወደላይ እና
ወደታች ሚመላለሰውን ሰው የሚማፀኑ…….
ወታደሮችም መሳሪያቸውን ደቅነው በቡድን አምስትና ስድስት በመሆን በየሁለት መቶ ሜትር
ርቀት ልዩነት ይንጎራደዳሉ…አንዳንዴም መንገዱ ላይ የተኮለኮሉትን የምሽት ንግስቶችን
ከአንዱ የመንገዱ ጠርዝ ወደ ሌላው ያባርራሉ….ይመቶቸዋል መሰለኝ ሲመጡባቸው ግር
ብለው ይሸሾቸዋል፡፡
ብቻ ለእኔ ለገጠሬው ከማሰብ አቅሜ በላይ የሆኑ ብዙ የሚገርሙና ናላ የሚያዞሩ
ትዕይንቶችን ፒያሳን በመሽለኩለክ ስታዘብ ከቆየው ቡኃላ ደከመኝና ወደ አንዱ ሆቴል ጎራ
ብዬ ..አንድ ሁለት ማለት ጀመርኩ…ሆቴል ውስጥም ከጠጪዎች ቁጥር በላይ ቁጥር
ያላቸው ሴቶች ይርመሰመሳሉ‹‹አሁን እኚ ሁሉ እናትና አባት አላቸው አይደል…?እሺ እናት
አባት አይኑራቸው ወንድም እና እህት ያጣሉ..?እሺ እሱስ ይቅር አጎትና አክስት…?እኔ እንጃ
እኔ የገባኝ ብዙ ቤተሰቦች እዚህም እዛም እየፈረሱ እንደሆነ ነው…ምክንቱም እነዚህ ከፈረሰ
ቤተሰብ …ባይፈርስ እንኳን ተሸንቁሮ ማፍሰስ ከጀመረ ቤተሰብ ሾልከውና ተመዘው የመጡ
ብኩኖች ናቸው…ብዙ ቤተሰብ እዚህም እዛም መፍረስ ሲጀምር ደግሞ አገርም እየተናደች
መሆኑ ማሳያ ነው…እንደዛ ነው የተሰማኝ..፡፡ይንን እያሰላሰልኩ መጠጤን ከቢራ ወደ አልኮል
አዘዋውሬ ስጋት ..እናም ደግሞ በተከፈተው ሙዚቃ ስደንስ ..ከማላቃቸው መስል ጠቺዎች
እየተጋፋውን እየተሻሸው ሀገርኛውንም ፈረንጅኛውንም ሳስነካው ቆየውና ሺደክመኝና
ሽከሬም ጠንከር እያለ ሲመጣ …ምነካህ ዋቅቶላ ?አዲስ አበባ እኮ ነው ያለሀው
ይበቃሀል››አልኩና እራሴን በመምከር ስድስት ሰዓት ተኩል አካባቢ ሂሳቤን ከፍዬ እራሴን
ላለመንገዳገድ እየጠራኩ የነበርኩበትን ሆቴል ለቅቄ ልወጣ ስል አብሬያቸው ስደንስ
ከቆየዋቸው የስካር ጎደኛቼ አንድ ጎትቶ ወደ ኃላ መለሰኝና አንድ ሙሉ ቢራ በእጄ
እያስጨበጠኝ ‹‹ነፍሱ በጣም ተመችታሀኛል..በዚህች መዚቃ የመጨረሻ ፈታ እንበል እና
ትሄጃለሽ›› አለኝ
ተወዳጅ መሆንን የሚጠላ የለምና ተወዳጅና ተመራጭ በመሆኔ ኩራት በውስጤ እየተሰማኝ
የተጋበዝኩትን ቢራ እየተጎነጨው በተከፈተው ሙዙቃ እስኪያልበኝ መወራጨት ጀመርኩ
አራት ሆነን ሆቴሉን መሀከል ክብ ሰርተን ቀወጥነው..ሙዚቃው እንዳለቀ አመስግኜቸው
ሹልክ ብዬ .ወደ ቤርጎዬ መንገድ ጀመርኩ…. እንሰደተቃረብኩ አንደ ልጅ እግር በብዥታ
ውስጥ ቢሆንም ደማቅ ቀይ መሆኖ የሚያስታውቅ እንስት ሳለስበው እየተጋላመጥኩ
ሳስተውላት ‹‹ሀይ ቆንጆ›› አለችኝ…ውስጤ ያለው የሴት ፍቅር ይሁን የጠጣውት መጠጥ
ፊቴን አዞርኩና ወደእሷ ቀረብኩ ተጠጋዋት..ጮርቃ ወጣት ብትሆንም ታምራለች…ግን
ሁለመናዋ የተንቀዠቀዠ ነው..አይኖቾ ራሳቸው ከወዲህ ወዲያ ይሽከረከራሉ..እጆቾም ከቀኝ
ወደ ግራ ይወናጨፋሉ..ምርቅን ቅን ብላለች መሰልኝ ከንፈሯንም እያኘከች ነው
‹‹እሺ ሰላም ነሽ?››ብዬ እጄን ዘረጋውላት..እንደመጨበጥ በመዳፎ ነካ አድርጋ መልሳ
ግንባሯን በማቀርቀር ፀጉሯን መጠቅለል ጀመረች‹‹..ቆንጆ ነሽ››አልኳት ሌላ ምላት ጠፍቶኝ
‹‹ሾርት ነው አዳር››አለችኝ እኔ ያልኳትን እንዳልሰማ ሆና
የምለው ግራ ገባኝ…የመዳራት ዕቅድ ፈፅሞ