Get Mystery Box with random crypto!

የፍቅር አለም

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefiker_alem — የፍቅር አለም
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefiker_alem — የፍቅር አለም
የሰርጥ አድራሻ: @yefiker_alem
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.56K
የሰርጥ መግለጫ

❤ፍቅር_አለም❤
የፍቅር አለም መሬት አደለችም
የፍቅር አለም በፍቅር ውስጥ
የምትፈጠር ሌላ አለም ነች
ኑ በጋራ የፍቅር አለም እንገንባ

#ጾታ_አይመርጥም
👉cross ፈላጊዎች አናግሩኝ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@tru_fact22
@abrolovem
@yefiker_alem

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-25 11:49:41 ወንዶች እየመሩ ነው
36 viewsRoyal M, 08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 11:43:22 የፍቅር አለም pinned «በቻናላችን የትኛው ብዛት አለው??»
08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 11:41:34
በቻናላችን የትኛው ብዛት አለው??
Anonymous Poll
47%
ሴት
53%
ወንድ
30 voters52 viewsRoyal M, 08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 11:25:52 አዲስ የፍቅር ሙዚቃ

ከንቅልፊ ቀስቅሰህ በፍቅር ያነቃሀኝ
እንኳን ላኬፍልህ ለኔም አልበቃሀኝ

#share @yefiker_alem
64 viewsDay dremer, 08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 10:07:54 ሴት ልጅ መቼ መሰለህ
አንተን ከልቧ ምታወጣህ
በአንተ ምክንያት የፈሰሰው
እንባዋን የሚያብስላት
ወንድ ሲመጣ ነው         
ስለዚህ መቼም ቢሆን

እንባዋ ምክንያት አትሁን

#share @yefiker_alem
158 viewsRoyal M, 07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 09:55:52
ሴት ልጅ አንተን እንዳፈቀረችክ የምታቅበት  10 ምልክቶች እና ህዝቤ ሆይ ምን ትተብቂያለሽ ገብተሽ ተመልከቻ
87 viewsRoyal M, 06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 06:37:15 ታውቂያለሽ የኔ ፍቅር እኔ ፍቅር ይይዘኛል ብዬ አልሜም አስቤም አላውቅም ነበር
ግን ፍቅር ሰውን አይመርጥምና አፈቀርኩ አይገርምም ለዚያውም አንቺን የመሰለ ለፍቅር መሠረት ከሆነ ሰው ፍቅር ያዘኝ።

ለካ ፍቅር ይሄ ነው በድንገት ሳይታሰብበት የሚከሰት ውስጣዊ ስሜት ነው ይሄን ያወኩት አንቺን ካፈቀርኩሽ ቡሃላ ነው። የኔ ፍቅር አፈቅርሻለው


➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢

#share @yefiker_alem
                     
ከወደዱት  ለሚወዱት ሰው ሼር ማድረግዎን አይርሱ
173 viewsDay dremer, 03:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 05:51:55 የፍቅር አለም pinned «ነሳሁ። የአልጋዉ ጫፍ ላይ ወረቀት ተቀምጧል። አንስቼ አነበብኩት። የሚኪ ፅሁፍ ነዉ። "ሀቢቤ አረፍ ብለህ ና እኔናሀጂ እዛዉ ስለሄድን አትጨነቅ።" ይላል። ወዲያዉ ተነስቼ ተጣጠብኩና ወደ ሆስፒታሉ ለመሄድ ከቤት ወጣሁ። ወዲያዉ ፌቨን ደወለችልኝ። አነሳሁትና "ወዬ ፌቪ" አልኳት። ፌቪ እያለቀሰች "ሀቢቤ በጌታ የት ሆስፒታል ነዉ ያላችሁት ጓደኛህ አልነግርም አለኝ። ፕሊስ መረጋጋት አልቻልኩም ልምጣና ልያቸዉ።"…»
02:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 05:51:49 ነሳሁ።
የአልጋዉ ጫፍ ላይ ወረቀት ተቀምጧል። አንስቼ አነበብኩት።
የሚኪ ፅሁፍ ነዉ። "ሀቢቤ አረፍ ብለህ ና እኔናሀጂ እዛዉ
ስለሄድን አትጨነቅ።" ይላል። ወዲያዉ ተነስቼ ተጣጠብኩና
ወደ ሆስፒታሉ ለመሄድ ከቤት ወጣሁ። ወዲያዉ ፌቨን
ደወለችልኝ።
አነሳሁትና "ወዬ ፌቪ" አልኳት።
ፌቪ እያለቀሰች "ሀቢቤ በጌታ የት ሆስፒታል ነዉ ያላችሁት
ጓደኛህ አልነግርም አለኝ። ፕሊስ መረጋጋት አልቻልኩም
ልምጣና ልያቸዉ።" አለችኝ። ለቅሶዋ ልብ ይነካል። ልነግራት
አሰብኩና ሀጂ ራህመቶ መኖራቸዉን ሳስብ መምጣቷ አግባብ
እንዳልሆነ ተሰማኝ።
"ፌቪ አንቺ መምጣትሽ ለኔ ጥሩ አይደለም። ባይሆን ሰዓት
ካገኘዉ እኔ ወጥቼ አገኝሻለሁ።" አልኳት። ምንም መምጣት
ብትፈልግም ለኔ ጥሩ አይደለም ስላልኳት ተስማማች።
"ግን ሀቢቤ ስደዉል ስልክ አንሳልኝ እሺ!" አለችኝ።
እሺ ብያት ተሰነባበትን።
.
ሆስፒታል ስደርስ ሀጂ እና ሚኪ እማዬ የተኛችበት ክፍል
ዉስጥ ተቀምጠዋል። እማዬ ነቅታለች። የሆነ የሆነ ነገር
ተሰካክቶላት ተጋድማለች። መናገር ምናምን ግን
አልጀመረችም። ሳያት የማላዉቀዉ ስሜት ዉርር አደረገኝ።
ወዲያዉ ግንባሯን ሳምኩና ከነሚኪ ጋር ተቀመጥኩ።
ወዲያዉ ሀጂ ፈገግ ብለዉ "ዶክተሯ ነገ ይወጣሉ ብላለች።"
አሉኝ። በጣም ደስ አለኝ። እማዬ እንደዚህ በአጭር ቀን
ከሆስፒታል ትወጣለች ብዬ አልገመትኩም ነበር።
"እና ዉጤቷን ነገሯችሁ?" አልኩ በጉጉት የሚሉትን
ለመስማት እየጠበቅኩ።
ሚኪ ወዲያዉ ፈጠን ብሎ "አዎ ነገሩን ደህና ናት ነገ በጣም
ከበዛ ከነገ ወዲያ ወደ ቤት እንወስዳቸዋለን።" አለኝ። ሚኪ
ደግሞ ሌላ አንድ ቀን ልትቆይ እንደምትችል አረዳኝ። ቢሆንም
ጠብቄዉ ከነበረዉ የተሻለ ነገር ነበር።
.
ከከሰዓቱን አብነት እና ከሪም ወደ ሆስፒታል መጡ። ስገምት
ሚኪ ነግሯቸዉ መሆን አለበት። አብነት እያቀፈኝ "አብሽር
ሀቢባችን ይሻላቸዋል እሺ!" አለኝ። ከሪሜ አይኔን ማየት
እየከበደዉ ሰላም አለኝ። እናቴን አይተዋት ካለችበት ክፍ


እየወጣን አብነት "ሀቢቤ መላ ከየት አግኝተህ ነዉ እዚህ
ያስተኛሀቸዉ?" አለኝ።
ሚኪ ፀጉሩን እየጠቀለለ "ባክህ አንድ መልዓክ የሆኑ ሰዉዬ
ናቸዉ የተሯሯጡለት አሁን ስራ ቦታቸዉ ላይ አንድ አንድ
ነገሮችን ለማስተካከል ሄደዉ ነዉ።" አለ።
አይን አይኔን እያየ "እግዚአብሔር ይጠብቃቸዉ። የእዉነት
በጣም ጥሩ ሰዉ ናቸዉ። ግን ማናቸዉ?" አለኝ።
ከሪሜ ዝም ማለቱ ገርሞኝ እያየሁት "የአምሪያ ፋዘር ናቸዉ።
ያቺ ጎረቤታችን" አልኩ።
ሚኪ ከሪምን እያየዉ "አንተ ደሞ ምናባህ ነዉ
የምትቆዝመዉ?" አለዉ።
ከሪሜ ፈገግ ለማለት እየሞከረ "ኧረ አልቆዘምኩም!" አለ።
የሆነ ጭንቀታም ነገር ነዉ። በኔ ቦታ ቢሆን ምን ሊሆን
እንደሚችል አስቤ ገረመኝ።
ወዲያዉ አብነት ከኪሱ ዉስጥ መቶ መቶ ብሮችን አዉጥቶ
እየሰጠኝ "ይኸዉ ሀቢቤ ሰዉየዉን ብዙ ብር
ከምናስወጣቸዉ ቢያንስ ልጅቷ የላከችልኝን ስምንት ሺህ ብር
እናግዛቸዉ።" አለኝ።
ወዲያዉ ምን ብሎ ልጅቷን ብር እንዳስላካት ትዝ ብሎኝ
እየበሸቅኩ "ስማ አንተ ጀዝባ ያንተ ሟርት ነዉ ይኸዉ እናቴን
ቀዶ ጥገና ላሰራበት ብለህ ብር አስልከህ እናቴን ቀዶ ጥገና
አስገባሀት። ወደዛ ዉሰድልኝ አልፈልገዉም!" አልኩት።
አብነት እንደመለማመጥ እያደረገዉ "ሀቢቤ ታዉቃለህ እኔ
ጋር ከሆነ ለረባ ነገር አንጠቀምበትም ስለዚህ ልጅቷም
ትፅደቅበት ደሞ ጓደኝነታችን ለመቼ ነዉ?" አለ።
ሚኪ ብሩን እየተቀበለዉ "ዝም በለዉ ባክህ!" አለና ወደኔ
እየዞረ "ሰዉየዉ አባትህ መሰለህ እንዴ? ቢያንስ ይህቺን ብር
ሰጥተን ልናግዛቸዉ ይገባል።" አለ። በርግጥ ሚኪ ልክ ነዉ።
ሀጂ ብዙ ብር ነበር ያወጡት።
ወዲያዉ ከሪሜ "በነገራችን ላይ ፋይናል እሮብ ይጀመራል።
ማስታወቂያ ተለጥፏል።" አለን።
"ዛሬ ቀኑ ምንድነዉ?" አልኩ ወደ ከሪሜ እየዞርኩ።
ከሪሜ "ዛሬ ሰኞ ነዉ ፈተናዉ ከነገ ወዲያ ነዉ።" አለ።
ሚኪ "ባክህ አሽቅ የለዉም እኛ እንደሆነ አናጠናም ያዉ
ከሪሜ ቸክይና ከቀለሞቹ ጋር እያዋዛን እንሰራዋለን።" አለ።
.
ትንሽ እንደቆየን አምሪያ እና ወ/ሮ ለይላ መጡ። አምሪያ
በእጇ ዘንቢል ይዛለች። አጠገባችን ሲደርሱ ወ/ሮ ለይላ
ፈገግ ብለዉ "ሀቢቤ ሽኩሪያዬ የት ናት?" አሉኝ። ፈገግ ብዬ
ወደ ዉስጥ ይዣቸዉ ገባሁ። አምሪያ ዘንቢሉን ለሚኪ
ሰጠችዉ። ወ/ሮ ለይላ ቁጭ ብለዉ ትንሽ ካወሩን በኋላ
ከመቀመጫቸዉ እየተነሱ "ምሳችሁን አምጥቼላችኋለሁ።
አደራ በደንብ ብሉ። ወደ ማታ ብቅ እላለሁ።" አሉን።
ወዲያዉ አምሪያን እያየሁ "አምሪ ግን ወደ ማታ መምጣት
ትችይ ነበር ትምህርት ለምን ቀረሽ?" አልኳት።
አምሪ ሳቀችና በከንፈሯ ጥርሷን ያጠረዉን ሽቦ ለመከለል
እየሞከረች "ሀቢቤ ባለፈዉ አርብ እኮ ኢንትራንስ ወሰድን
ረሳኸዉ እንዴ አስራሁለት ነኝ እኮ ጨርሰናል።" አለችኝ። ዉይ
ሶደሬ ፈተና ጨርሳ ዘና ልትል እንደተገናኘን ትዝ አለኝና "እንዴ
ለካ ..." ብዬ ልቀጥል ስል አምሪያ አቋርጣኝ "ለካ
አስራሁለተኛ ክፍል ነኝ።" አለች። እኔ ሶደሬ ተገናኝተን ነበር
ልል ነበር። እንዴት እንዳወቀች እኔንጃ! ደሞ ለማንም
እንዳልናገር አስጠንቅቃኝ ነበር። ወዲያዉ አምሪ እና ወ/ሮ
ለይላ ተነስተዉ ወጡ። እነሱ እንደሄዱ ሚኪ ምግቡን
አዘገጃጀና ለአራት አጣደፍነዉ።
.
ወደ አመሻሹ አስራ አንድ ሰዓት ሲሆን ፌቪ ደወለችልኝ።
ስልኩን አንስቼ ሆስፒታሉ የት እንደሆነ ነገርኳት። ስትደርስ
ምልክት አደረገችልኝና ወጥቼ አገኘኋት። ከትምህርት ቤት
በቀጥታ ነበር የመጣችዉ ዩኒፎርሟን እንደለበሰች ናት።
ገና አጠገቧ ስደርስ "የኔ ጌታ!" ብላ ተጠመጠመችብኝ።
የሸሚዜን ኮሌታ ይዛ "ሀቢቤ አሁን ማማ እንዴት ናቸዉ?"
አለችኝ።
"ደህና ናት ማታ ኦፕራሲዮን ተደርጋ ነበር። አሁን እንደ መንቃት
ብላለች።" አልኳት።
ፈገግ ለማለት ሞከረችና ከቦርሳዋ ዉስጥ አንድ እሽግ ብር
እያወጣች "ይኸዉ ሀቢቤ ለአንዳንድ ነገር ይሆናቸዋል።
ብራዘር ለአንዳንድ ነገር የላከልኝ ነዉ እትጨነቅ።" አለችኝ።
ፈገግ ብዬ ስለ ሀጂ ራህመቶ ተረኩላት። ገንዘቡ ለጊዜዉ
ስለማያስፈልገኝ እንደማልቀበላት ነገርኳት። ሲያስፈልገኝ
ልቀበላት ቃል አስገብታኝ ተለያየን። ሌላ ጊዜ ቢሆን እንዴት
ሰፍ ብዬ ብሩን እንደምቀበላት አስቤ ገረመኝ። ሀዘን ትንሽ
ስርዓት ያስይዛል።
.
ማታዉን ሀጂ ራህመቶ መጡ። ትናንት ማታ ስላልተኙ ዛሬ
ቤት ሄደዉ እንዲተኙ አስገደድናቸዉ። አብነት እና እኔ አደርን።
ሚኪ እና ከሪሜ ወደ ቤት ሄዱ። ትናንት ያሻትን በማድረግ
ስትደሰት የነበረችዉ ነብሳችን በሀዘን ተሸምቅቃ አደብ
ገዝታለች።
.
ይቀጥላል...
እንደተለመደዉ ይችን እየነካችሁ & #share
152 viewsDay dremer, 02:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ