Get Mystery Box with random crypto!

.... አንድ ወጣት አንዲት ቆንጆ ልጅ ይወድና ፍቅሩን ለመግለፅ በጣም ይፈራል። ጓደኞ | ❤ የፍቅር ነገር ❤

....


አንድ ወጣት አንዲት ቆንጆ ልጅ ይወድና ፍቅሩን ለመግለፅ በጣም ይፈራል። ጓደኞቹ እንዲነግራት ቢያበረታቱትም ደፍሮ መናገር አልቻለም።
#በቃ_እሷዋን_እያሰበ በትምህርቱ እየደከመ ሳቅ ጨዋታ እያስጠላው ሰውነቱ እየቀነሰ ጭንቀታም መሆኑ እጅግ ያሳስባቸው ጓደኞቹ በስንት መከራ አግባብተው እንዲነግራት ያደርጉታል።
#እናም ሲፈራ ሲቸገር በጣም እንደሚወዳት ይነግራታል እሷም #ቀብራራ ነገር ነበረችና እንዲህ አለችው "ውይ በጣም ይቅርታ እንኳዋን የፍቅር ጥያቄህን ልቀበልህ ይቅርና በአለም ላይ ማንን ትጠያለሽ ብባል አንተን ነው የምለው እና ይሄን ጥያቄ ደግመህ እንዳታነሳብኝ"
#ልጁም_ምንም_እንዳልተፈጠረ ተረጋግቶና ፈገግ ብሎ ወደ ጓደኞቹ ይመለሳል። ጓደኞቹም ፈገግታውን ሱያዩ ልጅቷ የፍቅር ጥያቄውን እንደተቀበለችው አምነው በደስታ ተቀበሉት።
#አንደኛው_ጓደኛው "እሽ አለችህ አይደል በጣም ደስ ይላል "ሲለው ወጣቱ ልጁ አረ በፍፁም እንዲውም በአለም ላይ እንደኔ የምትጠላው ሰው እንደሌለ ነው የነገረችኝ አላቸው።
#ጓደኞቹ ግራ ተጋብተው ታድያ እንዴት አላዘንክም ? እንዴት አልተከፋህም ? "አሉት እሱም ረጋ ብሎ እንዲህ ሲል መለሰላቸው።
#ለምን_እከፍለሁ_ለምንስ_አዝናለሁ?
#እኔ እኮ ያጣሁት በአለም ላይ ከምንም በላይ #የምትጠላኝን ልጅ ነው #እሷ ግን ያጣችው በአለም ላይ ከምንም በላይ #የሚወዳትን ሰው ነው። ስለዚህ እኔ ሳልሆን ማዘንም መክፋትም ያለባት እሷ ናት"አላቸው።
@Abdu_ke