Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያዊነት ወይ ሞት

የቴሌግራም ቻናል አርማ yeethelmdr — ኢትዮጵያዊነት ወይ ሞት
የቴሌግራም ቻናል አርማ yeethelmdr — ኢትዮጵያዊነት ወይ ሞት
የሰርጥ አድራሻ: @yeethelmdr
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.46K
የሰርጥ መግለጫ

√ ይህ የደብረ ይድራስ ሽማጎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካውንት ነው። 1000057909769 ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ እያላችሁ የቻላችሁትን አበርክቱ።
https://www.youtube.com/@Arkeledis_21
https://www.facebook.com/profile.php?id=100084055399303
✍🏾 ለአስተያየት @AmdE_MeleK_13

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-20 06:41:33 ውድ ኦርቶዶክሳውያን ቤተሰቦቼ ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን እንዴት ናችሁ? እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ። እንግዲህ ዛሬም በድጋሚ ተገናኝተናል። ዛሬም እንደተለመደው በቡሬ ወረዳ ስለሚገኘው የደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጉዳይ እናወራለን። ለዚህ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ልሣን መሆናችንን እንቀጥላለን። እርዳታው ተጀምሯል። ወገን እየተረባረበ ነው። እኛም ያለን በገንዘብ የሌለን በጸሎት እንረባረብ። ለዘለዓለማዊው ቤታችን ስንቅ እንያዝ። እውነት እላችኋለሁ መልዕክቱን Share ስታደርጉት ብዙ ቅን ልብ ያላቸው ክርስቲያኖች አይጠፉም። ለእናንተም በረከት ነው፤ ለእነርሱም ድኅነት ነው። እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ያስተምራል። ሰው ግን አያስተውልም።
•••
ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬም ለራሱ ራሱ ሰው አዘጋጅቷል። እያዘጋጀም ነው። ያዘጋጅማል። እኛ እቃ ነን። እቃ ሆነን እናገልግል። በቀና ትብብር መልዕክቱን ለብዙኃኑ እንዲደርስ የበኩላችሁን አድርጉ። እንዲያው በሕያው እግዚአብሔር ስም ይህንን መልዕክት ቢያንስ ለ 10 ሰው አስተላልፉት። እግዚአብሔር ይመስገን ዛሬም የምሥራች አለ። ግብዳ የምሥራች አለ። በኋላ ላይ በዩቲዩብ ብቅ እላለሁ። የምሥራቹን ዝርግፍ አደርገዋለሁ። እናንተም ደስ ይላችኋል። ጥያቄያችሁ ተመልሷል። ከዚህ በኋላ ከእኔ ጋር ሳይሆን ከ........... ነው ነገሩ። እኔም እንደ እናንተ ይህ መልዕክት የሚደርሰኝ ሰው ነኝ። መልዕክቱ የእኔ አይደለም። የራሱ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ነው። ሰፋ ባለ ቪዲዮ እንገናኛለን።
•••
~ ቸር እንቆይ ~
121 viewsዐምደ ብርሃን, 03:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 09:31:52
123 viewsዐምደ ብርሃን, 06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 09:25:52
ምነው ወደ ሸዋ ፈጣሪ ማድላቱ ፣
ምነው አንጎለላን ለይቶ ማየቱ ፣
ሲሰደድም ሸዋ እመ እጓል መግባቱ ፣
ደሙን ከጽዋው ጋር ዑራኤል ማምጣቱ ፣
ከተክልዬ ገዳም ሸዋ ላይ መዝመቱ ፣
ሸዋ ምን ታይቶ ነው ምን ይሆን ምክንያቱ ?

ደሞ'ስ ደብረ ታቦር ብርሃን መለኮቱ ፣
ክብሩን ለሐዋርያት ገልጦ ማሳየቱ ፣
ሙሴን ከኤልያስ ባሉበት መጥራቱ ፣
ለምን ደብረ ታቦር ምን ይሆን ምክንያቱ ?

~ ብዬ ሳስብ ሳስብ ~
አንድ መልዓክ ቢጤ በጆሮዬ መጥቶ ፣
ምሥጢሩን ነገረኝ ሁሉንም አብራርቶ ።
ስማኝ ዓምደ ብርሃን ጎልማሳው ወጣቱ ፣
ሸዋን የመምረጡ ለይቶ ማድላቱ ፣
በደብረ ታቦር'ም ክብሩን ማሳየቱ ፣
"ሸዋ በምኒልክ ታቦር በጣይቱ" ፣
ሚባል ትንቢት ነበር ከአበው ሐዋርያቱ ፣
አስምሕሮ ነበር ከአበው ሊቃውንቱ ፣
ትንቢትን መፈጸም ወንጌል ከኦሪቱ ፣
ባሕርይው ነው የአምላክ ጌትነቱ ፣
ትንቢት ሊፈጽም ነው ወደዚህ መምጣቱ ፣
ለዚህ ማድላቱ ይኼ ነው ምክንያቱ ።

||

ምኒልክን ሸዋ ጣይቱን ከታቦር ፣
አነግሣለሁ የሚል ቀደም ትንቢት ነበር ።
~ ይኼው ተፈጸመ ~

መልካም ልደት
111 viewsዐምደ ብርሃን, 06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 09:25:51
ልደት ዘንጉሥ ወንግሥት ||

•••
ትንሣኤሽ ቅርብ ነው አይርቅም ሃገሬ ፣
ዘውድሽ ተዘጋጅቷል የለም ጥርጣሬ ፣
አሰብኩት የዛሬን ወደ ኋላ ዞሬ ፣
ንግሥት እና ንጉሥ ፈልቀው ከመንደሬ ፣
ፀሐይ እና መልዓክ ተፈጥረው ከአድባሬ ፣
ተፈርቼ ቆየሁ ይኸው እስከዛሬ ፣
ምን ይልሃል ሸዋ የነጻነት ክብሬ ።

||

ምኒልክ እያሉ ፈጣሪን በጸሎት ፣
ምንትልክ እያሉ አምላክን በስግደት ፣
ሣህለ ሥላሴን ሁሌ ቢለምኑት ፣
ይኸው ንጉሥ ላከ ሸዋን ግዛ ሚሉት ።

እንደ ጠዋት ጀንበር እንደ ፀሐይቱ ፣
እንደ አደይ አበባ እንደ ለምለሚቱ ፣
ልክ እንደ ጨረቃ እንደ ከዋክብቱ ፣
በጠዋት ፈክታለች ብርሃን ጣይቱ ።

||

ምናለ የዛሬው ቀኑ ቢደጋገም ፣
ምናለ ሌሊቱ ባይነጋ ቢጨልም ፣
ምናለ ዶሮውም ባይጮህ ቢያጉረመርም ፣
ምናለ ከዋክብት ጨረቃ ባትገባም ፣
ንጉሥ እና ንግሥት ቢወለዱ ዳግም ።

ሃገሬ ኢትዮጵያ ማሕጸነ ውብ ነሽ ፣
የከዋክብት እናት ፀሐይቱን የወለድሽ ፣
የጨረቃን ድምቀት ብርሃኗን የሰጠሽ ።

||
64 viewsዐምደ ብርሃን, 06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 08:45:18
ምነው ወደ ሸዋ ፈጣሪ ማድላቱ ፣
ምነው አንጎለላን ለይቶ ማየቱ ፣
ሲሰደድም ሸዋ እመ እጓል መግባቱ ፣
ደሙን ከጽዋው ጋር ዑራኤል ማምጣቱ ፣
ከተክልዬ ገዳም ሸዋ ላይ መዝመቱ ፣
ሸዋ ምን ታይቶ ነው ምን ይሆን ምክንያቱ ?

ደሞ'ስ ደብረ ታቦር ብርሃን መለኮቱ ፣
ክብሩን ለሐዋርያት ገልጦ ማሳየቱ ፣
ሙሴን ከኤልያስ ባሉበት መጥራቱ ፣
ለምን ደብረ ታቦር ምን ይሆን ምክንያቱ ?

~ ብዬ ሳስብ ሳስብ ~
አንድ መልዓክ ቢጤ በጆሮዬ መጥቶ ፣
ምሥጢሩን ነገረኝ ሁሉንም አብራርቶ ።
ስማኝ ዓምደ ብርሃን ጎልማሳው ወጣቱ ፣
ሸዋን የመምረጡ ለይቶ ማድላቱ ፣
በደብረ ታቦር'ም ክብሩን ማሳየቱ ፣
"ሸዋ በምኒልክ ታቦር በጣይቱ" ፣
ሚባል ትንቢት ነበር ከአበው ሐዋርያቱ ፣
አስምሕሮ ነበር ከአበው ሊቃውንቱ ፣
ትንቢትን መፈጸም ወንጌል ከኦሪቱ ፣
ባሕርይው ነው የአምላክ ጌትነቱ ፣
ትንቢት ሊፈጽም ነው ወደዚህ መምጣቱ ፣
ለዚህ ማድላቱ ይኼ ነው ምክንያቱ ።

||

ምኒልክን ሸዋ ጣይቱን ከታቦር ፣
አነግሣለሁ የሚል ቀደም ትንቢት ነበር ።
~ ይኼው ተፈጸመ ~

መልካም ልደት
40 viewsዐምደ ብርሃን, 05:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ