Get Mystery Box with random crypto!

Abune Gorgorios

የቴሌግራም ቻናል አርማ abugs — Abune Gorgorios A
የቴሌግራም ቻናል አርማ abugs — Abune Gorgorios
የሰርጥ አድራሻ: @abugs
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.93K

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-10-30 21:28:46 Watch "7 ገዳይ የሆኑ የግቢ ውስጥ ትክሎች" on YouTube


1.3K viewsYonas, 18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 14:11:54 15/01/2015 ዓ.ም
ለወላጆች በሙሉ በቅድሚያ እንኳን ለብረሃነ መስቀሉ በሠላም አደረሳችሁ እያልን ነገ ማለትም  በ16/01/2015 ዓ.ም ከደመራ በዓል ጋር በተያያዘ ብዙዎች መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ  ስለሚሆኑ ት/ቤት በወጥነት ሰለሚዘጋ ትምህርት የማይኖር መሆኑን እያሳወቅን መደበኛ ትምህርት ረቡዕ በ18/01/2015 ዓ.ም የሚቀጥል መሆኑን እንገልጻለን።
      ። ።።።። መልካም በዓል ።።።።።።።። ።
።። ። ።።።።።።።።።።።። ት/ቤቱ  ።።።።።።።።
1.7K viewsEsdros ICT, 11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 21:43:12
አለን ለማለት ያህል…

"…በዘመን ውስጥ የምንለወጥ እንጂ ዘመን የሚለወጥብን አይሁን።" እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም በጤና አሸጋገረን አሸጋገራችሁ።"

"…ተወዳጆች ሆይ ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።" መክ 3፥1 እናም አምላካችን ሆይ፣ ስለ እናትህ ብለህ፣ ስለ ቅዱሳን መላእክቱ፣ ስለ ቅዱሳን ነቢያት፣ ስለ ቅዱሳን ሐዋርያት፣ ስለ ቅዱሳን ሰማእታቱ ብለህ …"መከራ ባሳየኸን ዘመን ፈንታ፥ ክፉም ባየንባቸው ዘመኖች ፋንታ ደስ ይበለን።" መዝ 90:15።

"…እንደተነገረንም እንደተስፋው ቃል 2015 ዓም የኢትዮጵያ ትንሣኤዋን ብሥራት የምንሰማበት ዘመን አድርግልን። መከራ ባሳየኸን ዘመን ፈንታ፥ ክፉም ባየንባቸው ዘመኖች ፋንታ ደስ ይበለን።" መዝ 90:15። አሜን…!!

•… ታዲያ ነገ እናንነቱ ስትበሉ፣ ስትጠጡ፣ ከበር ከደጃፋችሁ ላይ የቆመ እንዳለ እና እንደሌለ አስተውሉ። መልካም ዓውደ ዓመት። ምሕረት ለኢትዮጵያ…!!

መልካም አዲስ ዓመት!!!
4.1K viewsYonas, 18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 08:35:51 የ2015 ዓ.ም ባሕረ ሐሳብ የአጽዋማትና የበዓላት ማውጫ ስሌት
ክፍል ፩ ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
ዓመተ ዓለም = ዓመተ ምሕረት + ዓመተ ኩነኔ (ፍዳ) = 2015 + 5500 =7515
ወንጌላዊ ፦ በዓመቱ የሚሾም ወንጌላዊ ማለት ነው፡፡
ዓመተ ዓለም፥4
7515 ÷ 4 = 1878
1878 ፦ መጠነ ራብዒት ይባላል፡፡
1878×4=7512
7515-7512=1341 ደርሶ ቀሪ 3
ቀሪው ' 1 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ
ቀሪው ' 2 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ
ቀሪው ' 3 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ
ቀሪው ' 0 ' ከሆነ (ያለ ቀሪ ከተካፈለ)ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ይሆናል።
ስለዚህ ቀሪው '3' ስለሆነ የዘንድሮው ወንጌላዊ ሉቃስ ሲሆን ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ ይባላል።
•••
 ዕለተ ቀመር፦ መስከረም አንድ የሚውልበት ቀን ነው፡፡
ዕለተ ቀመር= ዓመተ ዓለም + መጠነ ራብዒት÷7
= 7515 + 1878 =9393
= 9393 ÷ 7 = 1341 ደርሶ ቀሪ 6 ይሆናል
ቀሪው '0 'ከሆነ ሰኞ
ቀሪው '1' ከሆነ ማክሰኞ
ቀሪው '2 'ከሆነ ረቡዕ
ቀሪው '3 'ከሆነ ሐሙስ
ቀሪው '4 'ከሆነ ዓርብ
ቀሪው '5 'ከሆነ ቅዳሜ
ቀሪው '6 'ከሆነ እሁድ መባቻ ይሆናል። በመሆኑም ዘንድሮ ቀሪው '6' ስለሆነ ዕለተ ቀመር እሑድ ይሆናል።
•••
መደብ = ዓመተ ዓለምን በዐቢይ ቀመር(532) በማዕከላዊ ቀመር(76) እና በንዑስ ቀመር(19) በማካፈል ማግኘት እንችላለን
1.7515፥532=14 ደርሶ ቀሪ 67
2.67 ለ ማዕከላዊ ቀመር ወይም ለ 76 መካፈል ስለማይችል ቀጥታ ለንዑስ ቀመር (19) ይካፈላል።
67 ፥19=3 ደርሶ 10 ይቀራል።
ስለዚህ መደብ 10 ይሆናል፡፡
•••
ወንበር =መደብ ሲቀነስ አንድ ነው(አሐደ አእትት ለዘመን የሚል አዋጅ አለና ላለፈው መሸኛ ለሚመጣው መቀበያ)
መደብ - 1=ወንበር (10 - 1= 9) ይሆናል።
በዚህም መሠረት ወንበር 9 ነው እንላለን
አበቅቴ ፦ጥንተ አበቅቴን በዘመኑ ወንበር አባዝተን ከ 30 በላይ ከሆነ በ30 ገድፈን ቀሪውን ከ30 በታች ከሆነ ደግሞ የመጣውን ቁጥር በመጠቀም እናገኛለን።
አበቅቴ =11×9=99
99፥30= 3 ደርሶ ቀሪው 9 ይሆናል ስለዚህ የዘንድሮው አበቅቴ 9 ነው እንላለን።
አበቅቴን ለማግኘት ሌላው አማራጭ ያለፈው ዘመን አበቅቴ ላይ ጥንተ አበቅቴን (11) በመጨመር የሚገኘው ቁጥር ከ30 በላይ ከሆነ ለ 30 በማካፈል ቀሪውን ከ30 በታች ከሆነ ደግሞ የመጣውን ቁጥር በመጠቀም ማግኘት እንችላለን ። ይህም ማለት
የ2014 ዓ.ም አበቅቴ 28 ነበር፤ ስለዚህ የ2015 ዓ.ም አበቅቴን ለማግኘት 28+11=39
ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 9 ስለሆነ አበቅቴ '9' ይሆናል ማለት ነው።
መጥቅዕ፦ ጥንተ መጥቅዕን በዘመኑ ወንበር አባዝተን በ 30 በመግደፍ(በማካፈል) እናገኛለን።
መጥቅዕ = 19×9 = 171
171 ÷ 30= 5 ደርሶ ቀሪው '21 'ስለሆነ መጥቅዕ ዘንድሮ '21 'ይሆናል።
መጥቅዕን ለማግኘት ሌላው አማራጭ ያለፈውን ዘመን መጥቅዕ ከጥንተ መጥቅዕ ላይ( 19 ) በመጨመር የሚገኘው ቁጥር ከ30 በታች ከሆነ ራሱ ከ30 በላይ ከሆነ ለ 30 ተካፍሎ ቀሪው የዘመኑ መጥቅዕ ይሆናል። ይህም ማለት የ2014 ዓ.ም መጥቅዕ 2 ነበር፤ ስለዚህ የ2015 ዓ.ም መጥቅዕን ለማግኘት
2+19=21 ስለዚህ የ2015 መጥቅዕ '21' ይሆናል ማለት ነው።
“አበቅቴ ወመጥቅዕ ክልዔሆሙ ኢይበዝኁ እም ሠላሳ ወኢይውኅዱ እም ሠላሳ ወትረ ይከዉኑ ሠላሳ ፤
አበቅቴ ቢበዛ መጥቅዕ ቢያንስ መጥቅዕ ቢበዛ አበቅቴ ቢያንስ ከሠላሳ አይበዙም ከሠላሳ አያንሱም”
ይህም ማለት በሌላ አገላለጽ መጥቅዕና አበቅቴ ተደምረዉ ውጤቱ ከሠላሳ መብለጥና ማነስ
የለበትም፤ ሁልጊዜ ሠላሳ ይሆናል፡፡ የዘንድሮዉ የ2015 ዓ.ም = 9+21= 30
መጥቅዕ ከ14 በላይ ከሆነ በመስከረም ይዉላል፤
መጥቅዕ ከ14 በታች ከሆነ በጥቅምት ይዉላል፤
መጥቅዕ በመስከረም ቢዉል ጾመ ነነዌ በጥር፣ መጥቅዕ በጥቅምት ቢዉል ጾመ ነነዌ
በየካቲት ይውላል።
ስለዚህ በዚህ ዓመት መጥቅዕ 21 ስለሆነ ከ14 ይበልጣል፤ ስለዚህም መጥቅዕ በመስከረም ይዉላል፤
•••
ስለዚህ የ2015 መጥቅዕ መስከረም 21 ሲሆን መጥቅዕ የሚወድቅበት ዕለት (ዕለተ መጥቅዕ) ቅዳሜ ይሆናል፡፡
•••
መባጃ ሐመር= የዘመኑ መጥቅዕ + መጥቅዕ የወደቀበት የዕለት ተውሳክ በመጠቀም የሚገኘው ቁጥር ከ 30 በላይ ከሆነ ለ 30 በማካፈል ቀሪውን መባጃ ሐመር እንላለን፡፡

ልብ ይበሉ የዕለታት ተውሳክ ከቅዳሜ ይጀምራል፡፡
የቅዳሜ---8
የእሑድ---7





ክፍል ፪ እና ፫
ስለ ግእዝ እንማርን ይቀላቀላሉ እና አንብበው ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ


https://t.me/Learning_Geez
https://t.me/Learning_Geez
https://t.me/Learning_Geez
https://t.me/Learning_Geez


መልካም
አዲስ
ዓመት

3.6K viewsYonas, 05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 08:34:55 https://t.me/Learning_Geez
2.5K viewsYonas, 05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 12:10:18
3.4K viewsYonas, 09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 08:42:27 1. ሰባቱ አባቶች

ሀ. ሰማያዊ አባት እግዚአብሔር
ለ. የነብስ አባት
ሐ. ወላጅ አባት
መ. የክርስትና አባት
ሠ. የጡት አባት
ረ. የቆብ አባት
ሰ. የቀለም አባት

2. ሰባቱ ዲያቆናት

ሀ. ቅዱስ እስጢፋኖስ
ለ. ቅዱስ ፊልጶስ
ሐ. ቅዱስ ጵሮክሮስ
መ. ቅዱስ ጢምና
ሠ. ቅዱስ ኒቃሮና
ረ. ቅዱስ ጳርሜና
ሰ. ቅዱስ ኒቆላዎስ

3. ሰባቱ የጌታ ቃላት(እኔ ነኝ)

ሀ. የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ
ለ. የአለም ብርሃን እኔ ነኝ
ሐ. እኔ የበጎች በር ነኝ
መ. መልካም እረኛ እኔ ነኝ
ሠ. ትንሳኤና ህይወት እኔ ነኝ
ረ. እኔ መንገድ እና ህይወት ነኝ
ሰ. እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ

4. ሰባቱ ሰማያት

ሀ. ጽርሐ አርያም
ለ. መንበረ መንግስት
ሐ. ሰማይ ውዱድ
መ. እየሩሳሌም ሰማያዊት
ሠ. ኢዮር
ረ. ራማ
ሰ. ኤረር

5.ሰባቱ ሊቃነ መላዕክት

ሀ. ቅዱስ ሚካኤል
ለ. ቅዱስ ገብርኤል
ሐ. ቅዱስ ሩፋኤል
መ. ቅዱስ ራጉኤል
ሠ. ቅዱስ ዑራኤል
ረ. ቅዱስ ፋኑኤል
ሰ. ቅዱስ ሰቂኤል

6. ሰባቱ አቢያተ ክርስቲያናት

ሀ. የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን
ለ. የሰርምኔስ ቤተ ክርስቲያን
ሐ. የጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን
መ. የትያጥሮስ ቤተ ክርስቲያን
ሠ. የሴርዴስ ቤተ ክርስቲያን
ረ. የፊልድ ልፍልያ ቤተ ክርስቲያን
ሰ. የሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን

7. ሰባቱ ተዓምራት
ጌታ እየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈፀሙ ተዓምራት

ሀ. ፀሐይ ጨልሟል
ለ. ጨረቃ ደም ሆነ
ሐ. ከዋክብት ረገፉ
መ. አለቶች ተሰነጣጠቁ
ሠ. መቃብራት ተከፈቱ
ረ. ሙታን ተነሱ
ሰ. የቤተ መቅደስ መጋረጃ

8. ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት

ሀ. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ
ለ. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው
ሐ. ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ
መ. እነሆ ልጅሽ እናትህ እነሆት
ሠ. ተጠማሁ
ረ. ተፈፀመ
ሰ. አባት ሆይ ነብሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ

9. ሰባቱ ሚስጥራተ ቤተ ክርስቲያን

ሀ. ሚስጥረ ጥምቀት
ለ. ሚስጥረ ቁርባን
ሐ. ሚስጥረ ክህነት
መ. ሚስጥረ ሜሮን
ሠ. ሚስጥረ ተክሊል
ረ. ሚስጥረ ንሰሃ
ሰ. ሚስጥረ ቀንዲል

10. ሰባቱ አፅዋማት

ሀ. አብይ ፆም
ለ. የሐዋርያት ፆም
ሐ. የፍልሰታ ፆም
መ. ፆመ ነቢያት
ሠ. ፆመ ገሀድ
ረ. ፆመ ነነዌ
ሰ. ፆመ ድህነት

11. ሰባቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠሉ ነገሮች

ሀ. ትዕቢተኛ አይን
ለ. ሐሰተኛ ምላስ
ሐ. ንፁህ ደምን የምታፈስ እጅ
መ. ክፉ ሐሳብ የምታፈልቅ ልብ
ሠ. ለክፋት የምትፈጥን እጅ
ረ. የሐሰት ምስክርነት
ሰ. በወንድማማቾች መካከል ፀብን የምታፈራ ምላስ

12.ሰባቱ ፀሎተ ጊዜያት

ሀ. ነግህ (የጠዋት ፀሎት)
ለ. ሰለስት (የ 3 ሰዓት ፀሎት)
ሐ. ቀትር (የ 6 ሰዓት ፀሎት)
መ. ተሰዓቱ (የ 9 ሰዓት ፀሎት)
ሠ. ስርክ (የ 11 ሰዓት ፀሎት)
ረ. ነዋም (የመኝታ ፀሎት)
ሰ. መንፈቀ ሌሊት (የሌሊት ፀሎት)

Join at
https://t.me/Learning_Geez
https://t.me/Learning_Geez
https://t.me/Learning_Geez
3.2K viewsYonas, 05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 15:24:49 2/13/2014
የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2015ዓ.ም የትምህርት አጀማመር በተመለከተ በባለሙያዎች የትምህርት ተቋማት ላይ ምልከታ እየተደረገ ነው::
በአንዳንድ ተቋማት ተዟዙረን እንደተመለከትነው ተቋማቱ ክፍሎችን ጥገና በማድረግ እና ቀለም በመቀባት ሲሰሩ ተመልክተናል::
በአቡነ ጎርጎርዩስ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ደረጀ በቀለ የትምህርት አጀማመር ዝግጅታቸውን አስመልክቶ እንደገለጹት የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማሳለጥ አዲሱን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሰረት በማድረግ ዕቅድ ማቀዳቸውን እንዲሁም አዲሱ የስርዓተ ትምህርት ሲተገበር የሚያስፈልጉ መምህራኖችን የማሞላት ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡በተጨማሪም ጥገና የሚያስፈልጋቸው ክፍሎች በመጠገን እና ግቢውን በማስዋብ ለመማር ማስተማሩ ዝግጁ ለማድረግ ጥረት እያደረጉ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡
በመንግስት በኩል በመፅሐፍ ሕትመት ጋር ያለው ሂደት ትኩረት ተሰጥቶበት ለግል የትምህርት ተቋማትም የሚዳረስበት ሁኔታ ቢፈጠር የሚለውን ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል፡፡
በአራዳና ቂርቆስ የትምህርት ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኤልያስ ኡንጋሞ የትምህርት አጀማመር ቅድመ ዝግጅት በትምህርት ተቋም ላይ በመሄድ ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማር ዝግጁ መሆናቸውን እና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ፖሊሲ ዝግጅታቸው በምን መልኩ እንደሆነ በሁሉም የትምህርት ተቋማት እየታዩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ተቋማት ከትምህርት ቤት አገልግሎት ክፍያ ውጪ በአይነት ይሁን በገንዘብ ከሕብረተሰቡ ተጨማሪ ገንዘብ ማሰባሰብ የሌለባቸው ሲሆን ይህን በተመለከተ ክትትል እና ቁጥጥር የሚደረግበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ተማሪዎች ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት የመማሪያ ክፍሎች እና የተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ክፍሎች በአግባቡ ምቹ ሆኖ አገልግሎት እንዲሰጥ መዘጋጀት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
#ኢትዮጵያን_በዘላቂነት_እናልማ_እንዘጋጅ!!
#የፈረሰውን_አብልጠን_እንገንባ!!
#ለማንኛውም_ፈተና_እንዘጋጅ!!
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
#ፌስቡክ; https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ ; educoc.gov.et
885 viewsYonas, 12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 15:24:48
885 viewsYonas, 12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 13:26:46 የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደቱን በይበልጥ ለማዘመን ከመደበኛ ትምህርት ጎንለጎን በኢ-ለርኒግ መተግበሪያ ሂደት ማስተማሩን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በዚህም ተማሪዎች ክረምትን በቤታቸው በሚያሳልፉበት ወቅት አጋዥ ይሆናቸው ዘንድ የፓይተን ፕሮግራሚንግ ቲቶሪያል፣ ውዳሴ ማርያም ከዘወትር ፀሎት እስከ መልከአ እየሱስ ከነምልክቱ በግዕዝ ንባብ በድምጽ እና በፒዲኤፍ፣ የተለያዩ የስነ-ህይወት ትምህርት መማሪያ ቪዲዮዎችን እና የእንግሊዘኛ ንግግር መማሪያ በቪዲዮ እና በፒዲኤፍ ብሎም የተማሩትን ትምህርት በምን ያህል መልኩ ተረድተዋል የሚለውን ለመፈተሽ የሙከራ ፈተናዎችን በኢ-ለርኒግ በኩል ማግኘት እንዲችሉ ተዘጋጅቷል፡፡ በተጨማሪም ለ2015ዓ.ም ቅድመ ዝግጅት በሁሉም የክፍል ደረጃ መጽሀፍቶች ይገኛሉ፡፡

ይህንን የቴሌግም ቦት ይክፈቱ @abg_lab_test_bot
በመቀጠልም /start ብለው ያስገቡ
1.5K viewsEsdros ICT, 10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ