Get Mystery Box with random crypto!

​​╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮ .' ከራስ ሽሽት '. | የካምፓስ ህይወት_MAHIR

​​╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ )
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯


. በ @tibebislam_nw የቀረበ
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ
.━─━────༺༻────━─

#ክፍል_ዘጠኝ....⓽
⊱◈◈◈⊰──────


ሀዩ የቢሮውን በር ከፍታ ወደውስጥ ገባች። ሉቅማን አንድ ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ፊቱን ወደውጪ አዙሮ ቁጭ ብሏል። ፊቱን ወደበሩ አዙሮ ሀዩ መሆኗን ሲያይ በጣም ደነገጠ! ሀዩ ሰላምታ ከሰጠችው በኋላ የእንግዳ መቀበያ ወንበር ላይ ሄዳ ተቀመጠች። ከዛም ስለሁሉም ነገር ነግራው ማግባት እንደማትፈልግና ሌላ ሴት እንዲያገባ ጠየቀችው። ሉቅማን የሰጣት መልስ ግን ጭራሽ ያልጠበቀችው ነበር።


ሀሰኔ በመታከሚያ ክፍሉ ኩርምት ብሎ ተኝቷል። እጁ ላይ ግልኮስ ተደርጎለታል። ምግብ የሚባል ነገር ከቀመሰ ሁለት ቀን ሞላው። ምንም ቢሉት ፣ የምግብና የመጠጥ መዓት ቢደረድሩለትም እሺ ብሎ ሊበላ አልቻለም።

እናትና አባቱም ስለሚያስጨንቀው ነገር ለማወቅ ቀርበው ቢያናግሩትም እሱ ግን አንድም ቃል ሊተነፍስ ፍቃደኛ አልሆነም። በቃ ማልቀስ ፣ ዝምታን መርጧል። የሱ ህመም ፍቅር እንደሆነ ማን በተረዳለት። አዎ እሱ ሀዩን አጥቶ መኖር አይችልም። የመጀመሪያው እንደሆነች ሁላ የመጨረሻውም እንደሆነች ነው የሚያስበው። ልቡን ብቻ ሳይሆን እሱነቱንም በሀዩ ፍቅር ዘግቶታል።

ፍቅር ከሁለቱም ወገን ሆኖ ፣ በሀላል መንገድ ሳይመሰረት ቀርቶ ፣ ከአንዱ ወገን ብቻ ሲመጣ ስቃዩ ብዙ ነው። ለመቀበል መስጠት ግድ ነው። ታድያ ምንም ሳይቀበሉ ሁሌ መስጠት ብቻ ልብን ሊያደማ ይችላል። የሷ ናፍቆት ሁሉ ነገሩን ተቆጣጥሮታል። እሱ ያለሷ ባዶ ነው! ምን ያደርጋል እሷ ግን ይሄን አታውቅም! በሷ ምክንያት እንደታመመ አታውቅም! በሷ ፍቅር እንደሚሰቃይም አታውቅም!


ሉቅማን ሀዩ የምታወራውን ምንም ሳያቋርጣት በጥሞና ካዳመጣት በኋላ እንዲ አላት...
ይሀውልሽ ሀያት እኔ አንቺ እንዳሰብሽው ገንዘብ ወይም ሀብት አለኝ ብዬ አይደለም አንቺን ማግባት የፈለኩት። የእውነት ስለምታስፈልጊኝ ፣ ስለምወድሽ እንጂ.
አንድ ሰው ሽማግሌ ልኮ ላግባ ሲል በገንዘቡ ብቻ እሷን መግዛት እንደሚፈልግ ነው ብዙ ሰው የሚያስበው። እኔን ግን በፍፁም እንደዛ እንዳታስቢኝ። አንቺን በፊትም አውቅሽ ነበር...ሱቅ ስትመጪ ምናምን አይሽ ነበር...ልቤ ከከጀለሽ ቆይቷል፤ ነገር ግን አጋጣሚውን አግኝቼ ልነግርሽ አልቻልኩም። ለዛ ነው አባትሽን አንቺን እንዲድሩልኝ የጠየኳቸው። በእርግጥ መጀመሪያ አንቺን አናግሬ ፍላጎትሽን ልጠይቅሽ ይገባ ነበር። ለዚ ደሞ አውፍ በዩኝ!

ሀያት ላንቺ ያለኝን ፍቅር ለማሳየት የግድ የኔ ሁኚ ብዬ አልጫንሽም። ግን ካገባችኝ እንደዚ አደርግላታለው ያልኩትን ነገር ባታገቢኝም አደርግልሻለው። ለትምህርትሽ ያለሽን ቦታና ወደፊት ትልቅ ደረጃ መድረስ ትፈልጊ እንደነበር አባትሽ ነግረውኛል ፤ ስለዚ ትምህርትሽን እንድትቀጥዪ እፈልጋለው።

እድሜሽን ሙሉ ለውንድምና እህቶችሽ ብለሽ የራስሽን ህይወት እንድታጪም አልፈልግም። እነሱም እኮ ነገ የራሳቸው ሰው ሲመጣ አግብተው አንቺን ጥለውሽ መሄዳቸው አይቀርም ፤ እና ስለራስሽ ህይወት በደንብ አስቢበት!

ስለትዳሩ ደሞ በጣም እንድትጨነቂበት አልፈልግም። የአሁኑን አመት ትምህርትሽን በስርዓቱ ተማሪ። አላህ ብሎ መቀራረባችን ለኔ ስሜት እንዲኖርሽ ካደረገሽ ታገቢኛለሽ። ካልሆነም ግን አልሆነም ነው። እኔ የምፈልገው አካልሽን ሳይሆን ልብሽን ነው!

ሀዩ በመለሰላት መልስ በጣም ደነገጠች። ልክ እሱ እንዳላት ገንዘብ ስላለው ብቻ ሊገዛት የመጣ አድርጋ ነበር ያሰበችው። ግን በተቃራኒው ሆኖ ጠበቃት። ምን እንደምትለው ግራ ገብቷት አንገቷን ደፍታ ቁጭ አለች። ሁለቱም ጋር ለደቂቃዎች ዝምታ ነገሰ።

ሀዩ ምንም መልስ ሳትሰጠው ለመሄድ አስባ ከተቀመጠችበት ስትነሳ አንዲት ሴት የቢሮውን በር ከፍታ ገባች።
ሀቢቤ ምንሆነህ ነው ቅድም ስደውልልህ ስልክ አታነሳም አለች ወደሉቅማን እየተጠጋች። ሁዩ የልጅቷ ማንነት ግራ አጋብቷት ባለችበት ቆመች። ምናልባትም ሉቅማን መጀመሪያ እንዳሰበችው አይነት ወንድ የሆነ መሰላት።

#ክፍል_አስር....⓾...ይቀጥላል
──────⊱◈◈◈⊰──────