Get Mystery Box with random crypto!

​​​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗ .' ከራስ ሽሽት '. | የካምፓስ ህይወት_MAHIR

​​​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ )

╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝

. በ @tibebislam_nw የቀረበ
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ
.━─━────༺༻────━─━



#ክፍል_ስምንት...⓼
∴━━━✿━━━∴


የሀሰን እናትና አባት የልጃቸውን የህክምና ውጤት ለመስማት ልባቸው ተንጠልጥሏል። ከምንም በላይ የዶክተሩ ፊት ላይ ጥሩ ነገር እያዩ ስላልሆነ በጣም አስፈርቷቸዋል። ዶክተሩ ሁለቱንም በትንሹ ካረጋጋ በኋላ ስለሀሰን የህክምና ውጤት መናገር ጀመረ።

ዶክተር፡ ቢስሚላሂ እንግዲ ስለልጃችሁ እናንተ በደንብ ታውቃላችሁ ብዬ አስባለው...እስኪ ንገሩኝ ልጃቹ የሚያስጨንቀው ነገር ምንድን ነው? መልስ ፍለጋ ሁለቱንም ተራ በተራ አያቸው።

አባት፡ ወይ ዶክተር! እሱን ብናውቅ ኖሮ ምናልባትም ዛሬ እዚ ባልተገኘን ነበር። እሱ ለኛም ጥያቄ ነው።
ሀሰኔ በጣም ዝምተኛ ልጅ ነው። ከኛ ጋር ኖረ እንጂ እኛ ስለሱ ምንም አናውቅም ማለት ይቻላል። ሁሉንም ነገር በሆዱ ነው የሚይዘው። ቢደሰትም ቢከፋም ለኛ አይነግረንም። ከሰዎች ጋር ብዙ አይግባባም። የትምህርት ቤት ጓደኞቹ እነማን እንደሆኑ እንኳን አናውቅም።
ይሄንን ጭምተኝነቱን እንዲተው ብዙ ነገር ሞክረን ነበር፤ ግን እያባሰበት ከመምጣቱ ውጪ ምንም መፍትሄ ማግኘት አልቻልንም።

ዶክተር፡ አዎ ሀቅ ነው...ይሄ በአንዳንድ ልጆች ላይ ይፈጠራል። የሀሰን ጭምት ወይም ዝምተኛ መሆን ተፈጥሮአዊ ባህሪው ነው። በግዳጅ ልናስለውጠው አንችልም። ምናልባት ግን በጣም የሚያስደስተውን ወይም በጣም ማግኘት የሚፈልገውን ነገር ካገኘ ቀስ በቀስ በራሱ ፍላጎት እየተወው ሊመጣ ይችላል። ከዚ ተፈጥራአዊ ባህሪው ሌላ በጣም የሚያስጨንቀው ነገር ግን አለ...

የምርመራ ውጤቱ እንደሚያሳየው ከሆነ ሀሰን የልብ ህመም heart case አለበት። ይሄ ደሞ የመጣው ከፍተኛ በሆነ stress ወይም ጭንቀት ምክንያት ነው። ለዛ ነው ቅድም ምንድን ነው የሚያስጨንቀው ብዬ የጠየኳችሁ። አሁን ያለበት የልብ ህመም ደረጃ ለክፋት ባይሰጠውም የሚያስጨንቀውን ነገር አውቀን ችግሩን ካልፈታንለት ግን ወደፊት ከፍተኛ ደረጃ በመድረስ ሊጎዳው ከዛም በላይ ለሞት ሊያደርሰው ይችላል።

ለ3 ቀን እዚው አልጋ ይዞ ህክምናውን መከታተል ይኖርበታል። አንዳንድ ማስተገሻዎችንም አዘንለታል። እናንተም የምትገዙለት መድሀኒት ይኖራል። ከሁሉም በላይ ግን ለሱ ትልቅ መድሀኒት ሊሆነው የሚችለው ደስታ ነው። ባገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ ደስታ ይፈጥርለታል ብላቹ ያሰባችሁትን ነገር አድርጉለት። እኛ የምንችለውን እናደርጋለን። ሁሉም የሚሆነው አላህ ያለው ስለሆነ እናንተም ጠንከር ብላቹ በዱዓ በርቱ። በተረፈ አብሽሪ

የሀሰን እናት መሬት ላይ ወድቀው ማልቀስ ጀመሩ። እሳቸውን እንደምንም ካረጋጉ በኋላ ሀሰንን የሚያስጨንቀውን ጉዳይ ለማጣራት የቤት ስራ ተቀብለው ወጡ።


ሀዩ በድቅድቅ ጨለማ ብቻዋን ቁጭ ብላለች። እንቅልፍ የሚባል በአይኗ ሳይዞር ለሊቱ ተጋመሰ። ስለቀኑ ጉዳይ እያሰበች ነበር በድንገት ግን አንድ ሀሳብ በሀዩ አዕምሮ ላይ ብልጭ አለ።

<አዎ! አዎ! እንዴት ይሄን አላሰብኩትም ነበር? በቃ ይሄ ነው ምርጥ ሀሳብ ሳታውቀው ጮክ ብላ ማውራት ጀመረች። የደስታ ስሜት ውስጧን ሲያሰክረው ተሰማት። ገና ውጤቱን ሳታውቀው እንዲ የሆነችበትን ምክንያት አላህ ነው የሚያውቀው።

አሁን የመጣላት ሀሳብ ሉቅማንን ራሱ ሄዶ አታግባኝ ማለት ነው። ስላለችበት ህይወት ነግራው፣ ማግባት እንደማትፈልግ ነግራው ለማሳመን። እሱ እሺ ካላት ሁሉም ቀላል ነው። ለአባቷ ሀሳቡን እንደቀየረ ይናገራል እሷም ሰላሟን አግኝታ ወደበፊት ህይወቷ ትመለሳለች። ጠዋት የሱ ህንፃ ነው የተባለበት ቦታ ሄዳ ልታገኘውና ልታዋራው እቅድ ይዛ ተኛች። የከዳት እንቅልፍም ምላሽ ያገኘ ይመስል ጋደም እንዳለች ቶሎ ይዟት ሄደ።

ጠዋት እንደልማዷ ስራዋን በጊዜ ከጨራረሰች በኋላ አባቷ ሲወጡ ጠብቃ ለነፈቲ እቃ ልትገዛ እንደሆነ ነግራቸው ሄደች። አባቷ የሉቅማን
ነው ያላት ህንፃ ጋር እንደደረሰች ጥበቃዎቹን የሉቅማንን ቢሮ ካወቁ በማለት ጠየቀቻቸው። ሙሉ ህንፃው የሱ ስለሆነ እዚ ማንም የማያውቀው ሰው የለም። ጥበቃዎቹ በነገሯት አድራሻ ወደሉቅማን ቢሮ አመራች። የሉቅማን ቢሮ ጋር እንደደረሰች በሩን በቀስታ አንኳኳች።
ይግቡ ... አለ ከውስጥ ያለ አንድ ሰው። እሷም ቀስ ብላ የቢሮውን በር ከፈተችው።

#ክፍል_ዘጠኝ...⓽...ይቀጥላል
◈ ━━━━━━━ ⸙ ━━━━━━━ ◈