Get Mystery Box with random crypto!

​​​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗ .' ከራስ ሽሽት '. . | የካምፓስ ህይወት_MAHIR

​​​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
." ከራስ ሽሽት ".
. ሶፊያ አህመድ

╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝

. በ @tibebislam_nw የቀረበ
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ
.━─━────༺༻────━─━


#ክፍል_ሰባት...⓻

ሉቅማን ዙሁር ሰላት ሊደርስ አከባቢ ስራ አለኝ ብሎ ሲወጣ አቶ ጀማልም ሊሸኙት አብረውት ወጡ። እነሱ ከሄዱ በኋላ ሀዩ ምንም እንዳልሰማች መስላ ከነፈቲ ጋር መጫወት ጀመረች። ውስጧ እያረረ ጥርሷ ግን ይስቃል። የውስጣችንን ሀዘን ጥርሳችን ባይሸፍነው ምን ይውጠን ነበር?


ሀሰን ከጠዋት ጀምሮ ሶፋ ላይ እንደተጋደመ ነው። ምንም እንኳን የራስ ምታት መድሀኒት ቢወስድም ሊሻለው አልቻለም። ቤተሰቦቹ እንዳይጨነቁ ከላይ ከላይ እንዳላመመው ለማስመሰል ቢሞክርም አልቻለም። ራሱ እንደእሳት ይለበልባል ፣ መተንፈስ እንከሚከብደው ድረስ ልቡ በሀይል ትመታለች ፣ ላብ ሰውነቱን አጥምቆታል...
በመጨረሻም እንደምንም ጨቅጭቀው ሆስፒታል እየወሰዱት ሳለ መንገድ ላይ እራሱን ስቶ ድንገተኛ ክፍል አስገቡት።

ቤተሰቦቹ በሀሰን ነገር እጅግ ተረብሸዋል። አባቱ አንድ አግዳሚ ወንበር ላይ ጭንቅላታን ይዘው ቁጭ ብለዋል። እናቱ እያለቀሱ ወደዚ ወደዛ ይንጎራደዳሉ።

ከሀሰን ጋር አብሮ ከመብላት ፣ አብሮ ከመጠጣት ፣ አብሮ ከመኖር ውጪ ስለሱ ህይወት ምንም ነገር አያውቁም። ምን እንደሚያስደስተው ፣ ምን እንደሚያስከፋው ፣ ጓደኞቹ እነማን እንደሆኑ...ምንም በቃ ምንም!

የሀሰን ከልክ በላይ ጭምት መሆን ትክክለኛ የቤተሰብ ህይወትን እንዳያሳልፉ አደረጋቸው። ዝምተኛነቱን በመቆጣት ሊያስተውት ቢሞክሩም ጭራሽ ሌላ ጭንቀት ውስጥ ስለሚገባባቸው ትተውታል። አንድም ቀን ግን ስለሱ ሳይጨነቁ ፣ ለባህሪው መፍትሄ ሳያፈላልጉ ውለውም አድረውም አያውቁም።


ሀዩ የመጣባትን የህይወት ፈተና ለመጋፈጥ ወስናለች። ቀኑን ሙሉ መፍትሄ ስትፈልግ ቆይታ በመጨረሻም ሁለት የአማራጭ ሀሳቦች ላይ ደርሳለች። የመጀመሪያው ሉቅማንን አግብቶ መኖር ነው። ግን በዚ ህይወት ውስጥ ሀዩ ራሷን ታጣለች። 2 አመት ከራሷ ቀንሳ ዋጋ የከፈለችላቸውን ሁሉ ገደል ታስገባዋለች። ከወንድምና ከእህቶቿ ተነጥላ ለማታውቀውና ለማትወደው ሰው ሚስት ሆና ትኖራለች።

ሁለተኛው አማራጭ ደሞ ወንድምና እህቶቿን ይዛ ከቤት መጥፋት ነው። በዚ ሀሳቧ ላይ ግን ብዙ ጥያቄዎች አሉ። ሀዩ ምንም ዘመድ የላትም። ገንዘብም እንደዛው። ይዛቸው የት ትሄዳለች? ምን ታበላቸዋለች? የት ታኖራቸዋለች? በምን ታስተምራቸዋለች? ይሄ ለሷም ጥያቄ ነው

አባቷ እንዳይድራት ብትጠይቀው ራሷን ከማስቆጣት ውጪ ምንም ምላሽ እንደማታገኝበት ታውቃለች። አባቷ አንዴ ስለወሰኑት ነገር ምንም ቢመጣ ሀሳባቸውን አይቀይሩም። አሁን ደሞ ገንዘብ በደንብ የሚያስፈልጋቸው ጊዜ ነው። ለዛ እሷን ከመዳር ወደኋላ አይሉም። እናም ሁዩም ይሄንን ሀሳቧን አስወጥታ በሁለቱ ሀሳቦች ላይ ለረጅም ሰአት መሟገት ጀመረች። አንድ መወሰን ግድ ነው። ሁለት ወዶ አይሆንም!


አንድ ጠቆር ያለ ዶክተር እጁ ላይ አድርጎት የነበረውን የእጅ ጓንት እያወለቀ ከሁለት ነርሶች ጋር ሀሰን ከሚታከምበት ክፍል ወጣ። እናትና አባቱም እየሮጡ በመሄድ ስለሀሰን ሁኔታ ጠየቁት።

እናት ፡ ዶክተር ሀሰኔ እንዴት ነው በአላህ እንባ አንቋቸው የሚሉትም በደንብ አይሰማም

ዶክተር፡ ይቅርታ እናንተ ለሀሰን ምኑ ናቹ? በግርምት እያየ ጠየቃቸው።

አባት፡ ወላጆቹ ነን ምንድን ነው ዶክተር በአላህ አታስጨንቀን ልጃችን ምን ሆኖ ነው?

ዶክተር፡ ታድያ እንዴት እዚ እድሜ ድረስ ለማንኛውም ውስጥ ገብተን እንነጋገራለን በማለት ወደሱ ቢሮ እንዲሄዱ ጋበዛቸው።

#ክፍል_ስምንት...⓼...ይቀጥላል