Get Mystery Box with random crypto!

​​​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗ .' ከራስ ሽሽት '. | የካምፓስ ህይወት_MAHIR

​​​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ )

╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝

. በ @tibebislam_nw የቀረበ
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ
.━─━────༺༻────━─━


.ክፍልስድስት...⓺
「✿」────❮✿



አባታቸው አቶ ጀማል ወደውስጥ እንደገባ ከኋላው አንድ በወጣቶች የእድሜ ክልል ውስጥ ያለ ፣ የተስተካከለ ቁመትና ሰውነት ያለው ቀላ ያለ ልጅ ተከትሎት ገባ። አልይን አቅፎ ሰላም ካለው በኋላ መርየምን ፣ ፈቲንና ሀዩን በርቀት ሰላምታ ሰቷቸው ከአባትየው አጠገብ ሄዶ ቁጭ አለ።

ሉቅማን ይባላል...እዚ እኛው ሰፈር እኮ ነው ያለው...ወደአስፓልቱ መውጫ ጋር ያለው ትልቅ ህንፃ የሱ ነው...እንዴት ያለ መልካም ሰው መሰላቹ...በማለት አባትየው ስለወጣቱ በአጭሩ ገለፀላቸው።
ስለሉቅማን ሲያወራ በጣም ደስ እያለው ነው። ሉቅማንም ስለሱ ጥሩ ነገር ሲወራ እንደሚሽኮረመም ሰው አንገቱን ደፋ ያደርጋል።

ሀዩና ፈቲ ተነስተው ምግብ ማቀራረብ ጀመሩ። ሉቅማንና አቶ ጀማልም የቀለጠ ወሬ ይዘዋል። ስለንግድ ፣ ስለትዳር እያነሱ ተጫዋወቱ። ምግብ ቀርቦ አንድ ሁለት ከጎረሱ በኋላ ሉቅማን
በጣም ይጣፍጣል ቆንጆ ምግብ ነው...እያለ በቀስታ ወደሀዩ ተመለከተ።
ታድያስ እንዴ ልጄ እኮ ባለሙያ ነው... ሀዩ ናት የሰራችው...በምግብማ አትታማም! የሉቅማንን ትከሻ መታ መታ አደረጉት!

ምግብ በልተው ከጨረሱ በኋላ
በሉ ልጆች ወደጓዳ ገብታቹ ተጫወቱ በቃ ...እኔና ሉቅማን ትንሽ የምንጨዋወተው ነገር አለ... ብሎ ሁሉም እንዲገቡ ነገራቸው። ሀዩም ልጆቹን ይዛ ወደክፍላቸው ገባች።

*

ሀሰን እራሱን አሞት ሶፋ ላይ ተኝቷል። የሀዩን ስልክ በመጠበቅ እንቅልፍን ስለከዳ እየቀጣው ይመስላል።
ሀሰንዬ አሁንስ እንዴት ነህ ትንሽ አልተሻለህም? አለች የሀሰን እናት ልቧ እየተንሰፈሰፈ መጥታ አጠገቡ ቁጭ አለች።
ወይ ካልሆነ ሆስፒታል እንሂድ.. ሰውነቱን በእጇ ስትዳብሰው በጣም ያተኩሳል።
አይ ኡሚ እዚው ብሆን ይሻለኛል... አለመሄዱን ለማረጋገጥ አተኛኘቱን አመቻቸ።
ከትምህት ቤት ደውለው ነበር...አሞት ነው የቀረው ብያቸዋለው...
ሌላስ ምን አሉ?
ምንም...ሌላ ምን ይላሉ ልጄ?
አዲስ ተማሪ ገብቷል አላሉሽም? ሀሳቡ ሁሉ ሀዩ ጋር ስለሆነ እንጂ ከመች ጀምሮ ነው አዲስ ተማሪ ሲገባ ለወላጅ የሚነገረው። እናቱ በግርምት አፍጥጣ ስታየው ነው ምን እንዳላት ትዝ ያለው። ደነገጠ!
በቃ ኡሚ ልተኛ...ብተኛበት ይሻላል..አትጨነቂ አንቺ... ምንም እንዳትጠይቀው ፊቱን አዙሮ እንደሚተኛ ሰው አስመሰለ።

ሰው እንዴት አንድ ሰውን ለረጅም ጊዜ ከዛ ሰው ምንም አይነት የፍቅር ምላሽ ሳያገኝ ሊያፈቅር ይችላል? ያውም በዚ ጊዜ...ትናንት ተዋውቀው ዛሬ የሚጣሉ ሰዎች በበዙበት ዘመን.. ፍቅር ቃሉ ብቻ የቀረ በሚመስል ብዙዎቹ በፍቅር በሚቀልዱበት ዘመን...

ሀሰን እኮ የእውነት አፍቃሪ ነው። እሷን ያፈቀራት ገንዘብ አላት ብሎ ፣ ከሷ ጥቅምን ፈልጎ ወይም እሷ ትወደኛለች ብሎ አይደለም። በቃ ፍቅር የሚባለው ነገር በትክክል በልቡ ስለገባ ነው።
ሀሰን አሁንም ቢሆን ተስፋ አልቆረጠም። ስልኳ ካርድ ስለሌለው ይሆናል ወይም አልተመቻትም ይሆናል እያለ ዛሬም የሀዩን የስልክ ጥሪ እየጠበቀ ነው። ያልደወለችበትን መጥፎ ጎን ጭራሽ ማሰብ አልፈለገም።

*

ሀዩ አባታቸው ውስጥ ግቡ ብሏቸው ብትገባም ተረጋግታ ልትቀመጥ ግን አልቻለችም። ይሄን ያህል ስለምን ሊያወሩ ቢሆን ነው እንድንገባ ያደረጉን? በዛ ላይ ዛሬ ያለወትሮው የአባቷ ሙገሳ ፣ ፈገግታ ብቻ ብዙ ነገር ለየት ብሎባታል።
ልጆቹን ክፍል ካስገባች በኋላ ለሳሎኑ የምግብ መስሪያ ቤቱ ስለሚቀርብ እቃ እንደምታስቀምጥ መስላ ገብታ ጆሮዋን ወደሳሎኑ አስጠግታ ስለምን እንደሚያወሩ መስማት ጀመረች።

አባት፡ እቺት እንግዲ ...ቆንጆዋ የመጀመሪያ ልጄ ሀዩ ማለት እሷ ናት..

ሉቅማን፡ ማሻአላህ ቆንጅዬ ልጅ አለቾት...እና እሷስ ስለነገሩ ታውቃለች?

አባት፡ ኧረ አታውቅም... ዛሬ ጠዋት ነው እንደምትመጣ ብቻ የነገርኳቸው...ግን ልጄ አርቆ አሳቢ ናት...ቀድማ እንደምታስብ አልጠራጠርም...

አሁን ይባስ ለመስማማት ወደግድግዳው ተጠጋች። ስለምን እንደሚያወሩ ምንም ሊመጣላት አልቻለም።

ሉቅማን፡ ያው እንዳልኮት ነው...ካምፓስ እስከምትገባ ድረስ እዚው ሆና መማር ትችላለች...እኔ እሷን ጨምሮ ሁሉንም ልጆች አስተምራለሁ... ይሄ አመት አልቆ 12ተኛ ክፍልን ከጨረሰች በኋላ ግን ከእኔ ጋር እንድትኖር ነው የምፈልገው...

አባት፡ ኧረ ችግር የለውም...ሀያቴን እኔ አንድ ነገር ብያት እንቢ አትለኝም...በዛ ላይ የሚጠቅማትን በደንብ የምታውቅ ልጅ ናት...

አሁን ሁሉም ነገር ገባት። አባቷ ለሉቅማን ሊድራት እንደሆነ...በጣም ደነገጠች። ከወንድምና እህቶቿ ላለመነጠል ብላ ብዙ መስዋትነት ከፍላ ነበር እኮ። አሁንም ቢሆን እሷ ማግባት አትፈልግም።

ሉቅማን፡ እስከዛው ግን አደራዎትን እርሶ ሊጠብቋት ይገባል.. እስከነክብረንፅህናዋ ነው ላገባት የምፈልገው..

አባት፡ ኧረ ሀያቴ ወንድ ራሱ ጭራሽ አታውቅም እኮ...ለዚስ ጭራሽ አታስብ...

ሉቅማን፡ መርሀባ ያው ትምህርት ከተጀመረ ገና 1 ወር እንኳን ስላልሞላው ትምህርቷን አሁን መጀመር ትችላለች...

ሀዩ የምትገባበት ቀዳዳ ጠፋት። የምትይዝ የምትጨብጠውን አጣች። ለማታውቀና ለማትፈልገው ሰው ልትዳር ነው...መቀበል አትፈልግም።
በጭራሽ! በጭራሽ አላገባም! እልህ በተናነቀው የሲቃ ድምፅ ከሷ ውጪ ማንም በማይሰማ መልኩ ዝቅ አርጋ እየደጋገመች ተናገረች።
ያአላህ ስቃዬን አታብዛው...እኔ ደካማ ባርያህ ነኝ...ምንም ነገር ለመጋፈጥ አቅሙ የለኝም..ያ አላህ የልቤን አንተ ነህ የምታውቀው...በማልችለው ነገር አትፈትነኝ...እያለቀሰች እጇን ከፍ አርጋ ስሞታዋን ለአላህ አቀረበች።
ወይ ዱንያ ቀጣይስ ምን ይፈጠር ይሆን? አለች በልቧ ጭራሽ ያልጠበቀችው ነገር በመፈጠሩ ግራ እየተጋባች።

#ክፍል\ሰባት...⓻...ይቀጥላል
✿❯────「✿」─