Get Mystery Box with random crypto!

​​╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮ .' ከራስ ሽሽት '. | የካምፓስ ህይወት_MAHIR

​​╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ )
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯



. በ @tibebislam_nw የቀረበ
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ
.━─━────༺༻────━─━


#ክፍል_አስር....⓾
⊱◈◈◈⊰──────



ልጅቷ ይባስ ብላ ሄዳ አቅፋ ሰላም አለችው። ሀዩ በድንጋጤ ውስጥ ሆና እንደቆመች ነው።
ተዋወቂያት እህቴ ናት... ሁለቱንም እያየ እንዲተዋወቁ ጋበዛቸው።
አሰላም አለይኩም...ኢማን እባላለሁ..ለሰላምታ እጇን ዘረጋችላት።
ወአለይኩም አሰላም...ሀያት.. እጇን እየጨበጠች ፈገግ ብላ መለሰችላት።

ምኑንም ሳታጣራ ሉቅማንን የገመተችበትን እያሰበች እየሳቀች ከክፍሉ ወጣች።
የሄደችበት ጉዳይ አልተሳካም። ይልቁንም ሌላ ሀሳብ ነው የጨመረባት። ስለራስሽ ህይወት በደንብ አስቢበት ያላት ደጋግሞ አእምሮዋ ላይ እየተመላለሰ አስቸገራት። እውነቱ ያ እንደሆነ እኮ ታውቃለች ፤ ግን መቀበል አትፈልግም።



ሀሰን ዛሬ ከሆስፒታል የሚወጣበት ቀን ነው። ተሽሎት ሳይሆን ትንሽ መለስ ስላለለት ነው እንዲወጣ የተደረገው። ለህመሙ ማስታገሻ እንጂ መድሀኒት ሳይገኝለት!
ጭንቀቱን አውቀው ሊያስደስቱት ይቅርና ሀሰን ከልቡ ፈገግ ካለ እንኳን ቀናት ተቆጥረዋል።

ሀሰን አሁን ሁሉም ነገር አስጠልቶታል። ትምህርት ቤት አልሄድም እያለ ከቤተሰቦቹ ጋርም ይከራከራል። እሷ የሌለችበት ት/ቤት አልሄድም በሚል ደረቅ ብሂል ልቡን አደንድኖታል።

ህይወት ሁሌ እንዳሰብነው አትሄድም። እኛ እንደፈለግነው ሳይሆን አላህ ባዘዛት መንገድ ብቻ ነው የምትጓዘው። ታድያ አንዳንዴ እኛ የፈለግነውና አላህ የመረጠልን የመንገድ አቅጣጫ የተለያየ ሲሆን እናማርራለን። ነገሮችን የምንቀበልበት መንገድም ልክ እንደአቅጣጫው የተለያየ ነው። ታድያ ሀሰንም ለውጦችን ፣ አጋጣሚዎችን በፀጋ ተቀብሎ ከመጋፈጥ ይልቅ መሸሽን ይመርጣል። ምናልባትም ማፈግፈግ ጀርባን እንደሚያስመታ አላወቀም ይሆናል።

ከስንት ክርክርና ሙግት በኋላ ይሄን ሁለት ቀን አርፎ ከዛ በዋላ ትምህርቱን እንዲጀምር ተስማሙ።



አቶ ጀማል ዛሬ ሳያመሹ በጊዜ ነበር ወደቤት የመጡት። ፊታቸው ላይ የድካም፣ ተስፋ የመቁረጥ ፣ የሀዘን ስሜት ይነበባል። ከዚ በፊት እንደዚ ሲሆን አይተውት አያውቁም። ዛሬ እንደከፋው ያስታውቃል። ሀዩ ወንድምና እህቶቿ እንዳይጨነቁ ብላ እነሱ ፊት ምንም አላለችውም። ከተኙ በኋላ ግን ምን እንደሆነ ቀርባ አዋራችው። እሱም ባንክ ያለው ገንዘብ እያለቀ እንደሆነና ለልጆቹ ት/ቤት የሚከፍለውን ገንዘብ እንዳጣ በሀዘን ተውጦ ነገራት።

የአባቷን ሀዘን ስታይ ሀዩም በጣም ከፋት። አቅፋው
አብሽር አላህ ያውቃል እያለች አፅናናችው። አሁን የመጣላትን ባል ለማግባት ፍቃደኛ ከሆነች የአባቷን እንባ ማበስ እንዲሁም ለወንድምና እህቶቿ የነገ ህይወት ዛሬ አሻራ መጣል ትችላለች።

ዛሬ ያየችው የሉቅማን መልካም ስብዕና እንዲሁም የአባቷ ሀዘን ሉቅማንን እንድታገባው የገፋፋት ይመስላል። ዛሬም ስለዚሁ ጉዳይ እያሰበች እስከመጨረሻው የማትወላውልበትን ውሳኔ ለመወሰን ቆርጣ ከራሷ ጋር ግብ ግብ ይዛለች። ግብ ግቡ ግን እንዲው በከንቱ አልቀረም። ውሳኔ እንድትወስን አድርጓታል።

ጠዋት ላይ ልጆቹ ትምህርት ቤት ከሄዱ በኋላ አባቷ ጋር ሄዳ ስለውሳኔዋ ነገረችው።

#ክፍል_አስራአንድ....⓫...ይቀጥላል
──────⊱◈◈◈⊰──────