Get Mystery Box with random crypto!

የአዶናይ ስቱዲዮ | YEADONAI STUDIO ™🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ yeadonai1st — የአዶናይ ስቱዲዮ | YEADONAI STUDIO ™🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ yeadonai1st — የአዶናይ ስቱዲዮ | YEADONAI STUDIO ™🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @yeadonai1st
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.43K
የሰርጥ መግለጫ

_ እ ን ኳ ን ደ ህ ና መ ጡ !
የቻናላችን ቤተሰብ ስ ለ ሆ ኑ እ ና መ ሰ ግ ና ለ ን 🙏
(ሐምሌ 30- 2011 ተጀመረ)
📧ሀሳብ አስተያየታችሁን
በ @Yeshewu ላይ ላኩልን👍
ይህንን አጋር የዩቲዩብ ቻናል subscribe ያድርጉ ይከታተሉ
https://www.youtube.com/@WISDOMTUBEETHIOPIA2

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 20:55:02
አንድ ነገር የእናንተ አለመሆኑን የምታውቁት ነገሩ ከእናንተ ጋር ባለው የጊዜ ቆይታ ነው።በዚህ አለም ሰዎች የእኔ ነው ብለው የሚመኩበት ነገር ሁሉ ለጊዜው ከእነርሱ ጋር ስላለ የእነርሱ ይመስላችዋል።ነገር ግን እውነት የእነርሱ እንዳልሆነ የሚታወቀው በስጋ ይሄንን አለም ሲሰናበቱ ነው።የእኔ ነው ብለው የሚመኩበት ነገር ሁሉ ሲሞቱ ይዘውት አይሄዱም።ገንዘቡ ይሁን፣ መኪናው፣ G+5 ቤቱ ይሁን፣ ዝና ይሁን ታዋቂነት እነዚህንና እነዚህን የመሰሳሰሉ ቁሶች ያለው ሰው ሲሞት እኛ እኮ የአንተ ነን ብለው እርሱ ወደሚሄድበት አይሄዱም።እንኳን እነዚህ ቁሳቁሶች ቀርቶ፥ አሁን ያላችሁ አካል(ስጋችሁ) እራሱ የእናንተ አይደለም።ስትሞቱ ጥላትታችሁት ትሄዳላችሁ።የእናንተ የሆነ ነገር ብትሞቱ እንኳን ከእናንተ ጋር ዘላለም የሚቆይ የሚኖር ነው።በዚህ አለም ሆነ በሚመጣው አለም የእናንተ የሚባለው ኢየሱስ ነው።መመካት ያለባችሁ በዚህ ነው።እርሱ የእናንተ፤ እናንተም የእርሱ ናችሁ።በዚህ ምድር የእኔ ከምትሉት ነገር ሞት ይለያያችዋል።ከኢየሱስ ጋር ግን ማን ይለያያችዋል? ሞት? ልክ ነው! ሞት ከአለም ጋር የተላመደው አካላችሁ ጋር ለዘላለም ይለያያችዋል።ምክንያቱ አሁን ያላችሁበት አካል የተበጀው ለወደቀው አዳም እንጂ በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት ለሆነው ማንነታችሁ አይደለም።ስለዚህ ይሄ አካል የእናንተ አይደለም።ልክ ነው! ሞት ከዚህ አለም ያስወጣችዋል።ምክንያቱም እናንተ ዳግመኛ የተወለዳችሁት በዚህ አለም ዘላለም እንድትኖሩ ሳይሆን በሚገለጠው አዲስ አለም ውስጥ ነው።በነገራችን ላይ ሞት አንድም የእናንተ ካልሆኑ ነገሮች ሁሉ ከስጋችሁ ጀምሮ ለዘላለም እንድትለያዩ በማድረግ፥ የዘላለም የእናንተ ወደ ሆነው ጌታ ደግሞ የሚያደርስ ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ነው።የእናንተ የሆነ ነገር ስትሞቱ እራሱ ታገኙታላችሁ።share it
64 viewsADONIJAH_(ABI), 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:53:53 በርቱ

በህይወት መንገድ ብዙ አድካሚ እንዲሁም ተደጋጋሚ ነገሮች አሉ እነዚህ ነገሮች ህይወትን አሰልቺ ሊያደርጉብን ይሞክራሉ እናም ይህንን ስሜት ተቀብለን የራሳችን ካደረግነው እግዚአብሔር ካየልን ነገር እንጎድላለን፤ አላማችንም ይቀልብናል። ስለዚህ ለተፈጠርንለት ነገረ ለመኖር እይታችንን ማስተካከልና የሀይላችንን ምንጭ መረዳት አለብን።

እይታችን በየዕለቱ + በየደቂቃው አዲስ የሆነው ኢየሱስ ላይ ከሆነ የነገሮች አድካሚነት ህይወታችንን አሰልቺ ሊያደርገው አይችልም(መክ 1:9)

በጌታ ሀይል (በመንፈሱ) የምንደገፍ ከሆነ እሱ ሁሉን ቻይ ስለሆነ ብርታትን ይሰጠናል ወዳሰበልንም ያደርሰናል(ፊሊ 4÷13፣ ኤፌ6÷10)

አይናችን ሌላው ላይ ከሆነ የተሻለ ነገር እንደሌለ በማሰብ እንቁአችንን እንጥላለን ግን አዲስ የሆነውን ጌታ ስናይ የተሻለ ነገር እንድናይ ያደርገናል።

ተባረኩ

በአቢጊያ

@yeadonai1st
@yeadonai1st
138 viewsADONIJAH_(ABI), edited  16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 10:18:49 ኢየሱስ የሚባለውን በአለም ሁሉ የሚወራለትን ታላቅ የሆነውን ከሁሉ በላይ የሆነውን ግን እናንተን የሚወዳችሁን ህይወታችሁን የሚያጣፍጠውን person ስለ እሱ መስማታችሁ እንድታውቁት አያደርጋችሁም ያላችሁ ሐይማኖት እንድታውቁት አያደርጋችሁም።

እሱን እንድታውቁት እና እንድታገኙት እና ህይወታችሁ እንዲቀየር የሚያደርገው እሱ እራሱ የፈቀደው እና ያዘጋጀው መንገድ በግላችሁ በእውነት እና በመንፈስ ሆናችሁ እሱን ለማወቅ በእርሱ ለመኖሮር ባለ ልብ እና ፍላጎት እሱን መፈለግ ነው።

እንዴት?

የሚል ጥያቄ ከተፈጠረባችሁ ከላይ ባልኳችሁ ልብ ሆናችሁ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ በዛ መሰረት መጸለይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያላቸውን ከዛ ጋር የተያያዙ ትምህርቶችን መስማት።

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ዝንብሎ ንባብ አይሆንባችሁም ከዛ የምታገኙት ነገር ህይወታችሁን ቅርጽ የሚያሲዘው ነው የሚሆነው መጸለይ ደግሞ በዛ መሰረት እየሱስን እንድታወሩት እና በህልውናው ውስጥ እንድትሆኑ ያደርጋችኋል ትምህርት መስማት ደግሞ ቃል የማንበብን እና የመጸለይን ፍላጎት ያጋግለዋል እኚህን ነገሮች ቀላል ናቸው ነገር ግን ለማድረግ እንቸገራለን በብዙ ምክንያት ግን እውነተኛ እሱን ማወቅ እና ማግኘት የሚፈልግ ልብ ካላችሁ ይቻላል

ቢያቅታችሁ እንኳን መሞከር በጣም አስፈላጊ ነው ምንም ከማያደርግ ሰው የሚሞክር ይበልጣል እና እኚህን ነገሮች ደጋግማችሁ ማድረግ ስትቀጥሉ በህይወታችሁ የሚገርም አዳዲስ ነገር ይሆናል መንፈሳዊውን አለም እያወቃችሁ ትሄዳላችሁ super natural የሆኑ ነገሮችን መለማመድ ትጀምራላቸሁ ከ ሁሉ በላይ ጌታ እየሱስን በግላችሁ እያወቃችሁት ትሄዳላችሁ ብዙ ብዙ ነገር ብቻ ይህንን የአድርጉ!

የተስማማ comment ላይ 1 ቁጥርን ይፃፍ ማድረግ ስትጀምሩ በህይወታችሁ የሚፈጠረውን ትንሽም ይሁን ትልቅ ለውጥ በዚህ አሳውቁን @Yeshewu

እወዳችኋለሁ መልካም ጊዜ!

@yeadonai1st
@yeadonai1st share
201 viewsADONIJAH_(ABI), edited  07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 09:04:43 አንተማ ተናግረህ ሳይሆንስ ከሚቀር፥
ይቀልሃል በጣም ፥
የስድስት ቀን ስራህ የተፈጸመበት ፥ሰማይና ምድር እንዳልነበር ሆኖ ፥
ጠፍቶ በዛው ቢቀር።

በ አዶኒ

@yeadonai1st join
277 viewsADONIJAH_(ABI), edited  06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 07:53:46 ሰፈራቹ ያለ ጠንቋይ ሲሞት መንፈሱ አንተ ላይ......

...የእግዚአብሔር ሰው ህመምህ አይሰማውም ሚስትህ ግን....

...ትሪው ላይ እንጀራ ቢጠፋ ሁሉም ነው የሚራቡት እና ባልሽን እንደ ጠላት ቆጥረሽ ገንዘቡን አታውድሚ አብራቹ እደጉ

ሚስትህ በማማሯ አትናደድ ውበቷ ላንተ ነው

apostle zelalem getachew

https://t.me/seven_spirits_tv_channel

You tube ላይ በምስል ይመልከቱ




251 viewsADONIJAH_(ABI), edited  04:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 08:11:08 በመላው ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ፈተናዎች እየተቃረቡ ነው

ታዲያ በዚህ ወቅት ተማሪዎችን እጅግ የሚያስጨንቁ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው

እንዴት አድርገን ለፈተናው እናጥና?

ያጠናነውንስ ላለመርሳት ምን ማድረግ አለብን?

የሚሉት ጥያቄዎች ናቸው።

የትምህርት ባለሙያዎችን፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን፣ የሥነ ምግብ ተመራማሪዎች፣ ውጤታማ ተማሪዎችን እንዲሁም የሥነ አእምሮ ባለሙያዎችን ይጠቅማሉ ያሏቸውን 12 ነጥቦች በ PDF እንደሚከተለው አቅርበንላቹሀል ተጠቀሙባቸው ሼር በማድረግም ሌሎች ተማሪዎች እንዲጠቀሙ የበኩላችሁን ድርሻ አበርክቱ ።

@yeadonai1st
281 viewsADONIJAH_(ABI), edited  05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 00:05:37
አንተስ ኢየሱስን የት አደረከው?
#Amazing

ህይወት ቀያሪ ምስክርነት

የእንደገና አምላክ

@yeadonai1st
@yeadonai1st
@yeadonai1st
311 viewsADONIJAH_(ABI), 21:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 23:05:29 ኢዮብ 5 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ “እኔ ብሆን ኖሮ፣ ወደ እግዚአብሔር በቀረብሁ፣ ጒዳዬንም በፊቱ በገለጽሁለት ነበር።
⁹ እርሱ፣ የማይመረመሩ ድንቅ ነገሮች፣ የማይቈጠሩም ታምራት ያደርጋል።
¹⁰ ምድሪቱን በዝናብ ያረሰርሳል፤ ሜዳውንም ውሃ ያጠጣል።
¹¹ የተዋረዱትን በከፍታ ቦታ ያስቀምጣል፤ ያዘኑትንም ወደ አስተማማኝ ስፍራ ያወጣቸዋል።
¹² እጃቸው ያሰቡትን እንዳይፈጽም፣ የተንኰለኞችን ዕቅድ ያከሽፋል።
¹³ ጠቢባንን በጥበባቸው ይይዛል፤ የተንኰለኞችንም ሤራ ያጠፋል።
476 viewsADONIJAH_(ABI), 20:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ