Get Mystery Box with random crypto!

በደረሰኝ መረጃ ወሎ አካባቢ በተለይ ደሴ ላይ በተፈናቃይ ተጨናንቃለች። ይህንን ተከትሎ በወቅታዊ ግ | Yasin Muhammed - Official Channel✔

በደረሰኝ መረጃ ወሎ አካባቢ በተለይ ደሴ ላይ በተፈናቃይ ተጨናንቃለች። ይህንን ተከትሎ በወቅታዊ ግርግር ምክንያት ግዜን ተገን አድርጋችሁ፤ ግዜን ጠብቃችሁ እቃዎችን በመደበቅና፣ ከልክ በላይ የምትሸጡ ነጋዴዎች አላህን ፍሩት
:
"ከነግዴዎች መጥፎ ነጋዴ ማለት ግዜን ጠብቆ ከልክ በላይ የሚሸጠው ነውና" እባካችሁ እርስ በርስ ተዛዝናችሁ ተገበያዩ።

ቢቻል ለሌላቸው ተሳሰቡ። ይህቺ ዱኒያ አትሞላም። እንደው መስሎን ነው እንጂ! በዚህ ክፉጊዜ ማዘን መተዛዘን ይጋባችኋል።

ከገንዘብ ደግሞ በላጩ በገዢውም በሻጩም መካከል ተወዳጅ የሆነው ነው ካልሆነ ግን ያገኘን እየመሰለን ማጣት ነው የሚሆነው።